መንፈሳዊ ሰው ፖለቲካ አያገባውምን?

መንፈሳዊ ሰው ፖለቲካ አያገባውምን?
የተወደዳችሁ ወገኖች የክርስትናና የፖለቲካ ግንኙነት ሰፊ በመሆኑ እንዲህ ባጭር የሚነገር አይደለም። ነገር ግን ለመነሻ ያህል ዛሬ በሀገራችን (በሌላ አገርም ቢሆን) እየደረሰ ካለው ችግር አንጻር የተሰማኝ ትንሽ ለመናገር ያህል ነው።
 
በተለይ በክርስትና ስለሌላው ሰው ችግር መናገር መንፈሳዊነትን ስለተላበሰ ሰብአዊነት መናገር እንጂ ስለፖለቲካ መናገር አይደለም። ስለፖለቲካም ቢሆን እኮ ከፖለቲካ ተጽዕኖ ውጭ የሆነ ሰው በአለም ላይ ማንም የለም በምክንኩስናም ቢሆን። ስለሌሎች ደህንነት ማሰብ ከፖለቲካም በላይ መንፈሳዊነት ነው። … በተለይ በዚህ ወቅት በሀገራችን ያለው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እጅግ አስጊ ሆኖ ወሬው ሁሉ በየቀኑ የሞት ብቻ በሆነበት ሰአት ፖለቲካ ነው ብሎ ዝም ማለት ምን ማለት ይሆን? … ዝምታ ካለማወቅ ካለመገንዘብ፥ ወይም ደግሞ እያወቁም ቢሆን በእኔ ላይ እስካልመጣ ድረስ እኔ ስለሌላው ምን-አገባኝነት፥ አሊያም ደግሞ በተደረገው ነገር ከመስማማት ከዚህ ከፍ ሲልም ከፍርሀት የሚመነጭ ካልሆነ በስተቀር ከየት ሊመጣ ይችል ይሆን?
 
በርግጥ እንጸልያለን እግዚአብሄር ሁሉንም ይቆጣጠራል << God is in Control >> ብለን እናምናለን። ነገርግን ሰው በሰው ፈቃድ ውስጥም ስላለ ለእግዚአብሄር (ለጸሎታችን) ብቻ የምንተወው ጉዳይ ብቻ አይደለም። መጽሀፍ ቅዱስ የሰዎች መንፈሳዊ ህይወት ታሪክ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካዊ የማህበራዊና የኢኮኖሚ መስተጋብር ታሪክ ጭምር ነው። ሰው መንፈስ ብቻ ቢሆን ኖሮ በስጋ በዚህች ምድር መኖር ባላስፈገውና እግዚአብሄርም ከመነሻው ሰውን ከአፈርና ከውሀ ባልፈጥረውና በምድር ኑር ባላለው ነበር። ወይም እግዚአብሄር ሰውን መንፈስ ብቻ አድርጎ በፈጥረው ነበር። ሰው መንፈሳዊ ቢሆንም በምድር ላይ በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ስር የወደቀ ነው።
 
ስለሆነም “የተገለጸ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል” (ምሳሌ 27፡5) እንዲል መጽሀፍ ቅዱስ ተጽእኖውን በተግሳጽ፥ በምክር ደግሞም በመግባባት በፍቅር እንድናሸንፈው እንጂ በሰው ልጆች ላይ ምንም ቢፈጠር ግድ የማይሰጠን ከሆነ መንፈሳውያን የሆንን አይመስለኝም። ሰው ሁሉ ፖለቲከኛ ነው ማለት ሳይሆን እንደጌታ ትዕዛዝ ሰው ሰውን እንደ እራሱ በእውነት የሚወድ ከሆነ ሰለሌላው ሁለንተናዊ /Holistic/ ደህንነት መጨነቅ አለበት ለማለት ነው። ጌታ << ሰርግ ቤት ከመሄድ ሀዘን ቤት መሄድ ይሻላል >> ሲል ምን ማለቱ ይሆን? እስከ ሞት የሚያደርሰው ችግራቸው ይሰማን ከማለቱ ውጭ።
 
ሰዎችን ከምንረዳባቸው መንገዶች አንዱ በሀሳብ ነው። ይህም በበሚያበረታታ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ወደ እውነት በሚያመጣ በተገለጠ ወቀሳ ጭምር ነው። ይህ ደግሞ መጽሀፍቅዱሳዊ ነው። መንግስት ስህተት ሲሰራ እንዲታረም መናገር ቁጭ ብሎ ከማየት ይበልጣል። በተለይም የሰዎችን ደህንነት ከእግዚአብሄር በታችና በራሱ ሰውኛ ድርሻ ለመጠበቅ ሀላፊነት የወሰደው መንግስት በስህተት ውስጥ ሲወድቅ ሰላምና መግባባት በህዝብና በመንግስት መካከል እንዲመጣ መጣር ያለበት ከማንም በላይ ክርስቲያን ነው። ምክንያቱም ይህም መጽሀፍቅዱሳዊ ስለሆነ ነው።
 
በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፍራዎች ሰዎች በየቀኑ ይሞታሉ። በቅርቡ በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት አደጋ መድረስ እጅግ ልብን የሚያሳዝን ከፍተኛ ሀዘን ነው። ቢሾፍቱ (ደብረዘት) ከተወለድኩባት ከተማ በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ትምህርት እስከምጨርስ ያደግሁባት ከተማ ስለሆነች ብቻ ሳይሆን ባንድ ጊዜ የዚህን ያህል ህዝብ በድንገት ያውም በሰው ሰራሽ አደጋ በማለቁ (የስጋ ዘመዶችም ሞተው ሊሆን ይችላል ገና አላረጋገጥንም) እጅግ እጅግ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል። … ችግሩ የዚህ አካባቢ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ ቀውስ ስለሆነ ከጸሎት በመለስ ዝም ልንል የሚያሰኝ ምንም ምክንያት ያለን አይመስለኝም። ስንት ሰው እስከሚያልቅ ነው ዝም ማለት ያለብን? ስለምን ዝም እንላለን? መፍትሄ በመጠቆም ህዝብንም መንግስትንም አንረዳም? እኛ እስካልተነካን ድረስ ከሆነ ይህስ ክርስቲያናዊነት መንፈሳዊነት ነውን? አይመስለኝም። ስለዚህ መስተካለል ያለበት እንዲስተካከል የሚሰማኝን ቅሬታ በሀሳብ እንኳን ለመርዳት የበኩሌን አልኩ፤ ቢያንስ ቅሬታዬን ገለጽኩ። ሌሎች ክርስቲያኖችም ስሌላው ሰው ችግር ዝም ቢሉ፥ የበኩላቸውን እርዳታ ባያደርጉ ደህንነታቸው ጥያቄ ውስጥ ባይገባም ምናልባትም መንፈሳዊ ግንኙነት /Fellowship/ እንዳይሰምር በማድረግ ተጽእኖ ይመጣ ይሆናል።
እግዚአብሄር ጸጋውንና ሰላሙን ያብዛልን !!!
 
(ክፍል – 2-) ይቀጥላል

         የቤተክርስቲያን መሰነጣጠቅና የእግዚአብሔር ህዝብ መበታተን መንስኤዎችና ጠቋሚ መፍትሔዎች   

በተለይ በውጭ ሀገራት ያሉት የኢትዮጵያውያንበወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት የፖለቲካ ፓርቲ ይመስል በየጊዜው የሚሰነጣጠቁበትና ምእመኑን መንጋ እንደሌለው እረኛ የሚበታተኑበት ምክንያት ምን ይሆን? … መፍትሄውስ ምን መሆን አለበት? የሚከተሉትን ዋና ዋና መንስኤዎችንና መፍትሔዎችን በመጠቆም ከታዛቢነትና ችግሮችን ከማውራት ወደ መፍትሔ ሀሳብ አቅራቢነት ልንሸጋገር ይገባናል።

እናንተ ምን ትላላችሁ? ” እኛ ምን አገባን መሪዎች ናቸው፥ እግዚአብሄር እንደስራቸው ይጠይቃቸው! ” በማለት ቤተክርስቲያን ወደ ቁልቁል ስትወርድ፥ ህዝበ ክርስቲያን አንድነት ሲያጣ በምንቸገረኝነት ወይም በግብዝነት፥ ከሚመላለሱት ውስጥ ናችሁን? … ወይስ ደግሞ “ቤተክርስቲያን በጎደለባት፥ ስህተት በሞላበት፥ አንፃር በመቆም በመንፈሳዊ አሰራር ማቅናት አለብን” ከሚሉት ውስጥ ናችሁ? … የታዘዝነው ግን በማስተውልና በፍቅር እንድናቀና ብቻ መሆኑን አንርሳ።

ክርስቶስ ኢየሱስን ማእከል መፅሐፍ ቅዱስንም መሰረት በማድረግ እሰራለሁ ብትልም፥ በስጋ ስራዎች እና መንፈሳዊ አመራር በማጣት ምክንያት የምትሰነጣጠቅ ቤተክርስቲያን የሚከተሉት ዝርዝር መገለጫዎችዋ ከሆኑ፥ ቤተክርስቲያን ተብላ ልትጠራ አይገባትምና ከወደቀችበት መነሳት አለባት።

 • – መንፈሳዊ ተልእኮዋን (Mission) የጣለች፥ (ማቴ. 28፥ 18-20 )
  – ወንጌልን የሸፈነች፥
  – የእግዚአብሔር ቃል በሙላት የማይሰበክባት፥
  – መንፈስ ቅዱስ የማይሰራባት፥
  – ፍቅር ያልሰፈነባት፥
  – ሰላም ያልሰፈነባት፥
  – ራእይ (Vision) የሌላት፥
  – በስጋዊ አመራር የምትመራ፥
  – መንፈሳዊ አመራር የሌላት፥
  – የመሪነት ጥሪና ስጦታ በሌላቸው የማትመራ፥
  – በስጋዊ አሰራር የምትመራ፥
  – ነፍሳት የማይድኑባት፥
  – መንፈሳዊ እድገት የሌለባት፥
  – በአሸዋ ላይ የተመሰረተች፥ /በአለት ላይ ያልቆመች/፥
  – ግብዝነት እና ማስመሰል የነገሰባት፥
  – እምነት እና ስምምነት የጠፋባት፥
  – የስጋ ስራዎችን፦ እነዚህም … ጥል፥ ክርክር፥ ቁጣ፥ ቅናት፥ አድመኝነትና መለያየት (ገላትያ 5 ፥ 22) በገፍ የምታፈራ፥
  – የመንፈስ ፍሬዎችን፦ እነዚህም … ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትእግስት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የዋሀት፥ ራስን መግዛት (ገላትያ 5 ፥ 18) የማታፈራ፥
  – ተተኪ ትውልድ የማታፈራ፥ /ወጣቶችና ህፃናት ተከታታይ በሳል መንፈሳዊ ትምህርት እውቀት የማያገኙበት፥ መንፈሳዊ ሰው /Role model/ በማየት የማያድጉበት፥
  – መንጋውን መመገብ፥ መጠበቅና ማሰማራት ያልቻለች፥
  – መንፈሳዊ ድርቀት እና መጫጫት የሞላባት፥
  – መንፈሳዊ አንድነት የሌላት፥
  – ይቅርታ ምህረት እና እርቅ የማትወድ
  – እንደ ምድራዊ የግል ንብረት የምትቆጠር፥
  – አገልጋይነት እንደ ስልጣን የሚቆጠርባት፥
  – የምክር አገልግሎት የሌለባት፥
  – እግዚአብሄር ርስቴ ያለው ምእመን የበላይ ውሳኔ ሰጭ ያልሆነባት፥
  – ምእመናን የቤተክርስቲያን እቅድና በጀት የማያፀድቁባት፥
  – የሂሳብ ምርመራ እና የእንቅስቃሴ ሪፓርት የማይደረግባት፥
  – ምእመናን ስለመሪዎች ጉዳይ የማይወያዩበትና ውሳኔ የማይሰጡባት፥
  – መሪዎች እና ምእመናን ልብ ለልብ የማይተዋወቁባትና የተራራቁባት/፥
  – አባላት በባለቤትነት ሳይሆን በባይተዋርነት የሚመላለሱባት፥
  – በአጭር፥ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ እቅዶችና እንዲሁም ስትራቴጅክ ፕላን በማውጣት የማትሰራ፥
  – በግልፅነትና በተጠያቂነት /Transparency & Accountability/ የማትሰራ፥
  – የጋራ አመራርና አስተዳደር /Collective Leadership/ የምትፈራ ወይም የሌላት፥
  – የአንድ ሰው አምባገነንነት /Dictator/ የነገሰባት፥
  – በአንድ ግለሰብ ፍላጎት እና ስሜት የምትመራ፥
  – በመዝሙር መሟሟቅ “አምልኮ” የምትኖር፥
  – ከመንፈሳዊ ህይወት ይልቅ በምእመናን ገንዘብ ላይ የምታተኩር፥
  – የመተዳደሪያ ደንብ /Bylaw/ እና የውስጥ አሰራር መመሪያ የሌላት፥
  – የፋይናንስ አጠቃቀምና አያያዝ ችግር ያለባት፥
  – ከመሪዎች ይልቅ ምእመናን በመንፈሳዊ መረዳት የቀድመባት፥
  – በፀጋም ሆነ በእውቀት ለማገልገል የሚችሉት የተገፉባት፥
  – ለተፍገመገሙት፥ ለወደቁትና ለጠፉት ደንታ የሌላት፥
  – ለአለም ብርሀን ያልሆነች፥
  – ላልዳኑት ማሰናከያ የሆነች፥
  – መንፈሳዊ አመራር በማጣት የእግዚአብሔር ህዝብ የሚበታተንበት፥
  – እየሄደች የማትሄድ /የማታድግ – የማትበዛ – የማትሰፋ/ ይልቁንም እያደር የምታንስ
  – ወዘተርፈ

(ክፍል – 2 -)
1ኛ/ … ቤተክርስቲያን ተልእኮዋን /Mission/ መጣል፦
የቤተክርስቲያን ተልእኮ የሚሆነው ” እንግዲህ ወደ አለም ሂዱ አህዛብን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው፥ … ” (ማቴ. 28 ፥18-20) የሚለው ሲሆን፥ ከላይ እንደተዘረዘረው ቤተክርስቲያን ይህንን ተልዕኮ ከማስፈፀም ውጭ የምትሰራ ከሆነ፥ ያለጥርጥር ተልእኮዋን በመጣል ስጋዊ አሰራር ውስጥ በመግባት መንጋው ይበታተንባታል።

ለማስረጃ ያህል በፔንሲልቬንያ የላንካስተር የገጠር ከተማ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ተልእኮዋን እንዴት እንደጣለች ወይም እንደ ሳተች በሚከተለው አጭር ገለፃ ላሳያችሁ። … በአካባቢው መኖር ከጀመርኩ ስምንት /8 /አመታት የሞላኝ ሲሆን፥ ከነባር ነዋሪዎች ምእመናን በሰበሰብኩት መረጃ መሠረት፥ በአካባቢው ተበታትነው የሚኖሩ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ኢየሱስ ስም በመሰባሰብ አንዲት ታናሽ የክርስቲያን ህብረት (Fellowship) በመጠንሰስ መጀመራቸውን እና ለተወሰኑ ጊዜያትም ማንም ሰው የበላይ እና የበታች ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ እየመራቸው በመልካም መንፈስ መመላለሳቸውን ይተርካሉ። (ይህንን ህብረት ለጀመሩት በሙሉ ትልቅ ምስጋናና ባርኮት ይገባቸዋል)

ነገር ግን ከቆይታ በኋላ የምእመናን ብዛትና የአስራትና መባ ገንዘብ መጠን ጠርቀምቀም ማለት ሲጀምር፥ ቤተክርስቲያን ከምእመናን የተውጣጣ መንፈሳዊ መሪዎች እንደሚያስፈልጋት ከመረዳትና ከመተግበር ይልቅ፥ በአገልግሎት ወጣ ብለው በሚታዩ ጥቂት ግለሰቦች መካከል የበላይነት ስልጣን ፋከክር ተጀመረ። ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበትን መንፈሳዊ አሰራር በመከተል ተጠሪነቱ ለጠቅላላው ምእመናንወይም ጉባኤ የሆነ የጋራ የሽማግሌዎች የስራ አመራር /Collective Leadership/ በመመስረት ይህንን መሰረታዊ የአመራር ችግር መፍታት ይገባ ነበር። የስራ አመራር አባላት ከመምረጥ ጋር አያይዞም ጠንካራ የመተዳደሪያ ደንብ እና የፋይናንስ መመሪያ በማውጣት አለመግባባትንና አለመተማመንን በማጥፋት፥ አንድነትን በመጠበቅ ረጅም መንገድ ለመጓዝ ይረዳ ነበር። ነገር ግን ይህ አልሆነም። ከዚህ የተነሳ በበላይነት ለመምራትና በተለይም የቤተክርስቲያን ገንዘብን ለመቆጣጠር በሚደረግ የስልጣን ሹክቻ ምክንያት፥ መንፈሳዊነት ለስጋዊነት ቦታውን ለቀቀ።

ከዚህም የተነሳ “…ጥል፤  ክርክር፤  ቁጣ፤  ቅናት፤  አድመኛነትና፤ መለያየት…” (ገላትያ 5 ፥ 22) የስጋ ስራዎች በመንሰራፋት ያች ታናሽ ህብረት /ቤተክርስቲያን/ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት ተሰነጠቀች። … ሁለቱ ግሩፖች በዋናነት መሰባሰባቸውን በቤተሰብ፥ በዘመድ አዝማድና በጓደኞች ዙሪያ በማድረግ ባላንጣ የነበሩትን ሁለት ሰዎች የየቡድናቸው መሪ አድርገው በመሰይም፥ የጎሪጥ እየተያዩ “ውሃ ቅዳ – ውሀ መልስ” ጨዋታ፥ በመዝሙር ሞቅታ ቀጠሉ። … ብዙም ሳይቆይ 1ኛው ተሰንጣቂ ቡድን እንደገና ለሁለት በመሰንጠቁ፥ ሌላ 3ኛ ተሰንጣቂ ግሩፕ ሲፈጠር እኔ በአካባቢው ለመኖር መጣሁ።

እንደተለመደውና አዲስ ሰው ወደ አካባቢው ሲመጣ እንደሚደረገው የአንደኛው ግሩፕ “ፓስተር” እኔ ወደ አካባቢው እንደምመጣ ከሚቀበለኝ ጓደኛዬ ሰምቶ ኖሮ፤ ከቀሪዎቹ ሁለት ግሩፖች ተሽቀዳድሞ ከጓደኛዬ ጋር ኤርፖርት ድረስ መጥቶ ተረከበኝ፥ በአባልነት ቆይቼ ሳስተውልም፥ እኔ የምፈልገው አስራት እንድከፈል ብቻ መሆኑን ከላይ በጠቀስኳቸው የቤተክርስቲያን መገለጫዎችና እዚህ ላይ ለመጥቀስ በማይመቹ ሌሎች መንገዶች ተረጋገጠልኝ። በአጭር አነጋገር አካል ሳይሆን አባል እንድሆን ብቻ ነበር የተፈለገው።

መሰረታዊ መፍትሔ ባለመፈጠሩ ምክንያት ከመጀመሪያውና ሁለተኛው መሰንጠቅ በኋላም እንደዚሁ ሌሎች ስምንት /8/ መሰነጣጠቆች /ባማካይ በአመት አንድ/ ቀጥሎ፥ አስራ አንድ (11) የተሰነጣጠቁ አንድ መቶ በማይሞሉ ምእመናን መካከል ይገኛሉ። “…በአንድነትና በፍቅር እንጂ 11 ቦታዎች ተከፋፍሎ ደርዘን እንኳን የማይሞሉ ሰዎችን ይዞ በጥላቻ መንፈስ ውስጥ መጓዝ ሀጢያት ነው፥ የትም አያደርስም፥ መንፈሳዊነትም አይደለም…” ያለው ቁጥሩ የማይናቅ ምእመናን ወደ ነጮች ቤተክርስቲያን በመመላለስ ላይ ይገኛል። በተፈጠረው የመካፋፈል ችግር ምክኒያት በእምነት ያልጸኑትና በተለይም በርካታ ወጣቶች በሚያሳዝንና በሚያስፈራ ሁኔታ በአለም መንገድ ላይ እያዘገሙ ይገኛሉ። ቤተክርስቲያን ከጌታ የተሰጣትን ተልእኮዋን ጣለች ማለት ከዚህ በላይ ይኖር ይሆን?

አንዲት ታናሽ ህብረት በጥቂት አመታት ውስጥ ለ11 ጊዜያት 11 ቦታዎች በምትሰነጣጠቅበት ጊዜ መንፈሳዊ ጤንነትዋ በማያጠራጥር ሁኔታ በሽተኛ መሆንዋን በማወቅ ለጥገና መነሳት መንፈሣዊነት ነው። በመሆኑም ፈውስዋን በይቅርታና በምህረት ከእግዚአብሔር ዘንድ ለመቀበል መመለስ እንዳለባት ማሳሰብና መስራት በወንጌል ማመን ነው። የቀድሞውን ፍቅር በህብረት በማደስ፥ የተበታተኑትን በአንድነት በመሰብሰብ፥ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት በሀይልና በስልጣን ለማገልገል፥ ላልዳኑት ደህንነትን ለማድረስ፥ ላልፀኑት መፅናትን ለማምጣት፥ ለወደቁት መነሳትን፥ ለታመሙት ፈውስን ለማምጣት፥ ለመባረክና ለሌሎችም ለበረከትም ለመሆን፥ ለእግዚአብሔር ክብር ለመኖር /ወንጌልን ለማስፋፋት/ የተበታተነው የላንካስተር ህዝበ ክርስቲያን እንደገና በመሰባሰብና አንድ ጠንካራ ቤተክርስቲያን መመስረት አለበት።

በአሁኑ ወቅት በፔንሲልቬንያ ላንካስተር የኦሮሞ ቤተክርስቲያንን ሳይጨምር ከአንድ መቶ ሀያ የማያንሱ /ልጆች ሳይቆጠሩ/ ትወልደ ኢትዮጵያና ኤርትራ የሆኑ የወንጌላውያን እምነት ምእመናን ሊኖሩ እንደሚችሉ ዳሰሳዊ ጥናት /Assessment/ ያረጋግጣል። መንፈሳዊ አመራር በማጣት የተበታተነ መንጋ፥ በአንድነት በማሰባሰብ ሁሉንም የሚያቅፍ አንዲት ጠንካራ ህብረት (ቤተክርስቲያን) ካልተመሰረተች በስተቀር፥ 11 ቦታዎች ቀርቶ፥ 2 ቦታ እንኳን ብትከፈል ፍሬ አልባ ደካማና አቅመቢስ ፥ ለእግአብሄር ክብር የማትኖር፥ ለሰዎችም ደህንነትና በረከት የማታመጣ ተልእኮዋን ለመወጣት የማትችል ከመሆን አታልፍም።

(ክፍል – 3 -)
2ኛ/ … መንፈሳዊ አመራር እጦት /Lack of Spiritual Leadership/፦
ቤተክርስቲያን በገዥነት አመራር /Authoritarian Leadership/ የምትመራ አይደለችም። ይህ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ መሪነቱን ለቆ ይሄዳል። ክርስቶስ ኢየሱስም ሆነ ሀዋርያትም ያስተማሩት ቤተክርስቲያን በአገልጋይ መሪዎች /Servant Leaders/ እንድትመራ ብቻ ነው። … አንዳንድ መንፈሳዊ ያልሆኑ ስጋዊ መሪዎች ግን፥ በአለም እንደሚደረገው በብልጣብልጥነት፥ ግሩፕ በማደራጀት፥ ወሬ በማናፈስ፥ በአምቻና በጋብቻ በመያያዝ፥ ደጋፊዎች በማብዛት፥ በማግለልና በሌሎች ሰውኛ ዘዴዎች በመጠቀም ቤተክርስቲያን የምትቆም መስሎቸው፥ በፀጋም ሆነ በእውቀት ለማስተማርም ሆነ ለማስተዳደር የበቁትን መንፈሳውያን ሰዎች በመግፋት ቤተክርስቲያንን ባዶ ያስቀራሉ።

በአሜሪካ ፓስተርነት በጥሪ (Calling by God) ወይም ስጦታ ባለው ፕሮፌሽናል ወይም በሁለቱም ሊሰየም ይቻላል። በጥሪ ከሆነ የቲዮሎጂ እውቀት ላይጠይቅ የሚችል ሲሆን፥ ፕሮፌሽናል ከሆነ ግን የቲዮሎጂ እውቀት ያስፈልጋል። ፕሮፌሽናልና ፓስተር በስራው ውጤት ካላመጣ ቤተክርስቲያን ልታሰናብተው ይቻላታል። ጥሪ ያለውም ሆነ ስጦታ ያለው ፕሮፌሽናል ፓስተር መንፈሳዊ ፍሬዎችን ማፍራት ይጠበቅበታል። ነገር ግን ያለመንፈሳዊ ፍሬዎች ለረጅም ጊዜያት መቆየት የስጋዊ አመራር ውጤት ካልሆነ ምንም ሊሆን አይችልም። በነጮቹ ቤተክርስቲያን ፍሬ የሌለው ፓስተር አሰናባች ሳይፈልግ በክብር ራሱ ይለቃል /Resign/ ያደርጋል። ያለ ፍሬ መቀጠል ቤተክርስቲያንን ሽባ ማድረግና ፍርድም በራስ ላይ መጋበዝ ነው። የመንፈሳዊ መሪነት ጥሪ ወይም ደግሞ ስጦታ የሌላቸው ፓስተሮች በተለይ ከአብሲኒያ የመጡት ፍሬ ማፍራት ሲያቅታቸው ወደ አንባገነንነት አመራር / Dictatorial Leadership/ሳይታወቃቸው ይቀየራሉ፥ ለአለም ብርሃን መሆን ሲገባቸው በጭለማ በመመላለስ ላልዳኑት ማሰናከያ ይሆናሉ፥ በዚህም የእግዚአብሔርን ስም ያሰድባሉ።

ፓስተር መሆን በአሜሪካ ሀገር እጅግ ቀላል ነው። አንድ ሰው እግዚአብሔርን ካልፈራ ቤተክርስቲያን በማቋቋም ስም 10 ሰዎችን ፒቲሽን አስፈርሞ፥ 7ሺ ዶላር የባንክ አካውንት አሳይቶ፥ ዶክትሪናቸውን በተቀበለበት የነጮች ቤተክርስቲያን ፓስተርነት /Ordination/ ሊሰጠው ይችላል። … በከበረው በክርስቶስ ደም የተገዛች ቤተክርስቲያንን የገቢ ምንጭ አድርጎ ከመክፈት የሚልቅ ሀጢያት ያለም አይመስለኝም። ከዚህ የተነሳ ብዙዎች ” … የፓስተር እከሌ ሱቅ … ” እያሉ መቀለድ ጀምረዋል። በልማድም “የፓስተር እከሌ ቸርች” እየተባለም በአንድ ግለሰብ ስም ቤተክርስቲያን እየተጠራች ነው። … እነ ፓስተር እከሌም ቤተክርስቲያን የግል ሌጋሲያቸውን የሚያሳርፉባት የግል ንብረታቸው እየመሰለቻቸው፥ የፈለገው አይነት ስጋዊ አሰራር ሞልቶ ቢፈስ፥ እንደ ኤሊ ልጆች ልጆቻቸውም በሀጢያት ቢጨማለቁም፥ እግዚአብሔር አንድ ቀን በድንገት ከወንበራቸው ላይ እስከሚገለብጣቸው ድረስ፥ እያዩ የማያዩ፥ ማስተዋል የጎደላቸው በመሆን፥ ስልጣንና ገንዘብ አደንዝዞአቸዋል። ትንሽ የሚያንገዳግዳቸው የሰው ንፋስ በብዙ ነፍሶአል። የሚቀረውና ከዚህ በኋላ የሚመጣው ሀይለኛው የእግዚአብሔር ንፋስ ብቻ ነው።

/አንድ ቲያትር ላይ የንጉሥነት ዋና ገፀ ባህርይ የሚጫወት ተዋናይ “… ንጉስነት እንጀራዬ ነው …” በማለት ስልጣኑን ለማስጠበቅ፥ ሰዎችን ማሰርም ሆነ መግደል ወይም ከህግ በላይ መሆን የውዴታ ግዴታው እንደሆነ መጥቀሱ ትዝ ይለኛል። … እንደዚሁም ሁሉ በዘመናችን በርካታ ፓስተሮች የእግዚአብሄርን ህዝብ ለመምራት ወይም ለእረኛነት /መጋቢነት/ የሚያበቃ ጥሪ ሳይኖራቸው፥ ወንጌልን ለኑሮ መተዳደሪያ/መደጎሚያ በማድረግ፥ ” ፓስተርነት እንጀራዬ ነው ” በሚል መንፈሳዊና ስጋዊነት እሳቤ፥ (Mixed Motive) በመዝሙር በመሟሟቅና በሳምንታዊ እድር መሳይ ግንኙነት፥ መንፈሳዊ ፍሬዎች አልባ ህይወት የሚጓዙና የሚያስጉዙ ሆነው በመገኘታቸው፥ እግዚአብሔር ርስቴ ያለውን ህዝብ በመናቅ፥ ለእግዚአብሄርም ባለመቅናት በጥፋት ጎዳና ላይ ይገኛሉ። ወገኖቼ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በጥፋት ጎዳና ሲያዘግሙ፥ በይሉኝታና በምንአገባኝነት ደግሞም በግብዝነት መቀመጥ ፈፅሞ አላስቻለኝም።

የላንካስተር ቤተክርስቲያን ከመንፈሳዊ አመራር እጦት የተነሣ በውድቀት ጎዳና ላይ ነች። የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሌለ ጥበብና ማስተዋል ጠፍቶአል። አንዲት ታናሽ ቤተክርስቲያን 11 ቦታዎች ተከፋፍላ፥ እያንዳንዱ ክፍልፋይ ደርዘን የማይሞሉ አባላትን ቁጥር ዘርዝር ቢባል፥ የመጀመሪያው ቤተሰብ፥ 2ኛው ቤተዘመድ፥ 3ኛው የቅርብ ጓደኞች፥ 4ኛው ማህበራዊ ህይወት ፍለጋ የሚመላለስ፥ ቀሪው ደግሞ ” … ምን መሄጃ አለን ታዲያ! መንፈሳዊ ህይወትና አገልግሎትማ ኢትዮጵያ ቀረ … ” በማለት አማራጭ በማጣት የሚመላለስ ነው። እንዲህ አይነት ቤተክርስቲያን ወይም (Fellowship) ሳይሆን የእሁድ ሰንበቴ ማህበር /Swallow ship/ በማለት የሚቀለድበት ነው።

መፍትሔ ሀሳብ፦
የላንካስተር ቤተክርስቲያን ዋናው ችግር መንፈሳዊ አመራር የማጣት ችግር ነው። የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አመራር በጥቅሉ በሶስት መክፈል ይቻላል። 1ኛ/ የሽማግሌዎች /Elders/ የጋራ አመራር ወይም የስራ አመራር ቦርድ /Collective Leadership/ 2ኛ/ የፓስተር አመራር /Pastoral Leadership/ 3ኛ/ ሁለቱንም የሚያቅፍ ጣምራ አመራር አይነቶች ናቸው።ቤተክርስቲያን በየትኛውም አመራር አይነት ትመራ መንፈሳዊ ፍሬዎችን ማፍራት፥ ወንጌልን ማስፋፋት ህልውናዋ ነው። ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ፍሬዎችን በማፍራት፥ መብዛት፥ መስፋፋት፥ መባረክና ለበረከት በመሆን ፈንታ፥ በስጋ ስራዎች እየተሰነጠቀች፥ በመንፈስ እየሞተች፥ ምእመናንን እየበታተነች የምትሔድ ከሆነ፥ ችግሩ ምንድነው በማለት ቆም ብላ አባላትን በግልፅነት በማወያየት መፍትሔ መፈለግ አለባት።

በላንካስተር ቤተክርስቲያን የፓስተር አመራር እንዳልሰራ በግልፅ ስለተረጋገጠ፥ በጋራ አመራር / collective Leadership/ መለወጥ /መተካት/ አለበት። እንዴት? …1ኛ/ በቅድሚያ 11ዱ የተበታተኑ ህብረቶች አንድ አንድ ተወካይ በማዋጣት ጠንካራ ህብረት መፍጠር አለባቸው። … 2ኛ/ ህብረቱ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ጠቅላላ ምእመኑን ሰብስባ በመጥራት፥ የንስሀና እውነተኛ የልብ እርቅ ጊዜ ማድረግ፤ … 3ኛ / 11ዱ ተወካዮች ጠንካራ አንድነት ያላት አንዲት ቤተክርስቲያን በውህደት ለመመስረት መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን ለመጀመር፥ ከያንዳንዱ ግሩፕ አንድ አንድ ሰው የያዘ 11 አባላት ያሉት የጋራ አመራሮች በመሰየም፥ ቋሚ የፆም የፀሎትና የጋራ ህብረት ጊዜ በመወሰን መንቀሳቀስ አለበት። የ11ዱ ተወካዮች ዋነኛ ስራ በሂደት ውህደት ሊያመጡ የሚችሉ ዝርዝር ስራዎችን መንደፍ ነው። ጠቅላላ ምእመናን ወይም ጉባዔውን የቤተክርስቲያኗ የመጨረሻው ከፍተኛው ውሳኔ ሰጭ አካል አድርጎ በመሰየም፥ እያንዳንዱን ግሩፕ የሚወክል አስራ አንድ አባላት ያሉት አንድ የስራ አመራር ቦርድ (Collective Leadership) በመምረጥ እንዲመራ በማድረግ፥ 11ዱ የጋራ ስራ አመራር ቦርድ አባላት ያለ ደሞዝ በትርፍ ጊዜ የሚያገለግሉ ዝርዝር ሀላፊነት ያላቸው አባላት እንዲኖሩት በማድረግ ስራውን መጀመር።

 • – ሰብሳቢ፥
  – ምክትል ሰብሳቢ፥
  – ፀሐፊ፥
  – የአስተዳደርና የፋይናንስ ዘርፍ ተጠሪ
  – መንፈሳዊ ዘርፍ (3 ፓስተሮች)
  – የምክር አገልግሎት ዘርፍ ተጠሪ (ፓስተር)
  – የወጣቶች ዘርፍ ተጠሪ (ፓስተር )
  – የማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ተጠሪ (ፓስተር)
  – የአምልኮና የዝማሬ ዘርፍ ተጠሪ (ፓስተር )
  – የሴቶች አገልግሎት ዘርፍ ተጠሪ (ፓስተር)
  – ወዘተ

በዚህ መሰረት ቤተክርስቲያን በአንድነት ብትሰራ እስከ ስምንት /8/ ፓስተሮች ስለሚያስፈልጋት ሰፊ የአገልግሎት ዘርፍ እንዲኖር ያደርጋል። ይህም የጋራ አመራር /Collective Leadership/ አደረጃጀትን እንደመከተሉ የፍላጎት/ጥቅም ግጭትንና /Conflict of Interest/ አለመተማመንን በማጥፋት መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት ይስቻላል። እንደዚሁም ፓስተሮችን ከቤተክርስቲያን የፋይናንስ አስተዳደር ስራዎች ነፃ በማድረግ፥ መንፈሳዊ ሀላፊነት ላይ ብቻ በማተኮር ፍሬ እንዲያፈሩ የሚያስችል አሰራር ነው። ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ባለሙያዎች እንደ የሂሳብ ሠራተኛ፥ ሴክረተሪ ፀሐፊና የፅዳት ሠራተኛ ወዘተ ቤተክርስቲያን በቅጥር ልታሰራ ትችላለች።

(ክፍል – 4 -)
3ኛ/ … የገንዘብ አጠቃቀም ችግር /Financial mismanagement/፦
ሰዎች በሚሰሩበት በማንኛውም ሕብረት ውስጥ የሰውና የገንዘብ እንቅስቃሴ እስካለ ድረስ፥ የገንዘብ አጠቃቀም ህጋዊ ስርአት እስካልተዘረጋለት ድረስ፥ ገንዘብ የአለመግባባት መንስኤ ሆኖ ይቀጥላል። በተለይም ይህ ችግር በክርስቲያኖችበመካከል ሲከሰት ከማሳፈር በላይ ነው። የሚገርመው “…ገንዘብ መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነው…” (1ኛ ጢሞ 6፥10) በማለት መፅሀፍ ቅዱስ ካስተማረን በኋላ አስተውሎ ለመስራት ለምን እንደምንዘገይ ነው። … ከዚህ በተጨማሪም የፋይናንስ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ማንኛውም ተቋም (ቤተክርስቲያንን ጭምር) ተአማኒነትን ለማግኘት በግልጽነትና በተጠያቂነት (Transparency & Accountability) መስራት ብቸኛ አማራጭ ነው። ይህ ካልሆነ ግን በተለይ ቤተክርስቲያን እንደ አለማዊ ድርጅት በሙስና (corruption) ውስጥ በቀላሉ በመግባት ውድቀትዋን ታፋጥናለች። ለዚህም ጠቋሚው በቤተክርስቲያን ውስጥ ዝርክርክ የገንዘብ አያያዝ (Financial mismanagement) መከሰቱና ከዚህም የተነሣ በመንፈስ ሽባ መሆንዋ ነው።

በአመራር ችግር ምክንያት ስምምነት በማጣት 3 ሶስት ቦታዎች የተከፈሉትንና ሁለቱ በፓስተሮች አንዲትዋ ደግሞ በጋራ (ሽማግሌዎች) አመራር /Collective Leadership / የሚመሩቱ ወስደን እንኳን እንደ ምሳሌ ብናይ፥ በአንድነት ለመስራት ባልወደዱት መጠን የእግዚአብሔርን ገንዘብ ሶስት ቦታዎች በመከፋፈል ምን ያህል እንዳባከኑት /Mismanage/ እንይ። በፓስተር የሚመሩት ሁለቱ ደርዘን እንኳን የሚሞላ ምእመናን ሳይኖራቸው 300 (ከሶስት መቶ) በላይ መቀመጫዎች ያላቸው ሁለት ቤተክርስቲያን ህንጻ ገዝተው ሞርጌጅ መክፈል አቅቶአቸው ጥዋትም ማታም አስራት ክፈል፥ ፈንድ ሬይዚንግ ወዘተ እያሉ ለማይሞላ ቋት ምእመኑን ያስጨንቃሉ። ነገር ግን የአንደኛው ቤተክርስቲያን ህንፃ ተሸጦ ወደ አንዱ በመጠቃለል (የዶክትሪን እና የራእይ ወዘተ ልዩነት ስለሌላቸው) ከሞርጌጅ እዳ ነፃ በመሆን፥ የአስራትና የመባ ገቢዎችን ለወንጌል ማስፋፋት ስራ በዋለ ነበር። በዚህ ምክንያት ላለፉት በርካታ አመታት የደረሰውን በሰውም በገንዘብም ለመገመት አያዳግትም። ሌላው የሚገርመው ደግሞ 3ኛዋ ተሰንጣቂ ቤተክርስቲያን ተሰንጥቃ ከወጣችበት ካለፉት 7 አመታት ጀምሮ ከነጮች ቤተክርስቲያን ለተከራየችው የማምለኪያ ቤት በአመት ባማካይ 7,200 (ሰባትሺ ሁለት መቶ) ዶላር በመክፈል ባለፉት 7 ሰባት አመታት ውስጥ 50,000 (ከሀምሳ ሺ) ዶላር በላይ በማውጣትዋ ሌላው የእግዚአብሔር ገንዘብ ብክነት መገለጫ ነው። በቅድሚያ መሰንጠቅ ባይኖር ኑሮ ይህንን ያህል ለኪራይ ባልወጣ፥ በመቀጠልም መሰንጠቁ ተቀባይነት ያለው ቢሆን እንኳን ከነጮች ላይ ሳይሆን ከሁለት አንደኛው በፓስተር ከሚመሩት የሀበሻ ቤተክርስቲያናት ላይ ቢሆን ኖሮ፥ ሞርጌጅ ለመክፈል የሚንገዳገዱትን የሀበሻ ቤተክርስቲያን እግረመንገዳቸውንም ቢሆን በደጎሙት ነበር። ቅንነት ያለበትን አሰራር አለመከተል ከመንፈሳዊነት ችግርም በላይ የባህርይ ችግር ይመስላል። ባህርያችንንም ቢሆን የሚለወጠው መንፈሣዊነት ነበር።

የቤተክርስቲያን ገንዘብ በግልፅነት እና በተጠያቂነት መስራት በተመለከተ፥ ሀዋርያው ጳውሎስ በአግልግሎት ዘመኑ ችግር ላይ ለወደቀች አንዲት ህብረት የእርዳታ ገንዘብ እንዲያደርስላቸው በጠየቁት ጊዜ፥ ስለምን “… ተጨማሪ ሰዎች ስጡኝና ገንዘቡን አድርስላችኋለሁ… ” ያለ ይመስለን ይሆን? …ጳውሎስ በገንዘብ ጉዳይ ስለማይታመን ይሆን? በፍጹም አይደለም። ነገርግን ገንዘብን በተመለከተ ለሰዎች አእምሮ ጥንቃቄ በማድረግ መስራት እንደሚገባቸውና እንዲሁም ግልጽነትንና ተጠያቂነትን /Transparency & Accountability/ ያለበት አሰራር መስፈን ያለበት መሆኑን ሊያስተምራቸው ፈልጎ ነው እንጂ። … ታዲያ እኛ ከጳውሎስ የበለጠ ታማኝ ስለሆንን ይሆን ገንዘብን በተመለከተ ለሰዎች አእምሮ ባለመጠንቀቅ ደግሞም ግልጽነት የጎደለው አሰራር የምንሰራው?

ይህን በተመለከተ ለማደርገው ዳሰሳዊ ጥናት /Assessment/ ይረዳ ዘንድ አንዳንድ መሪዎችን ለማነጋገር ሞክሬ ነበር። … አንደኛው ፓስተር የሰጠኝን መልስ ዳሰሳዊ ጥናት የማያስፈልገው ቀጥተኛ ምላሽ ነው። … ሳላጋንንና እንዲያውም ንዴቱን አለሳልሼ ሳስቀምጥ እንዲህ ነበር ያለው። ” … ስለ አስራት ገቢ ማንም ሊጠይቀን አይገባም፥ አይችልምም፥… አስራት የእኛ የፓስተሮች ነው፤ … ምክንያቱም እኛ ሌዋውያን ነን፥ … በብሉይ ኪዳን ጊዜ የሌዊ ነገድ ከ12 የእስራኤል ነገዶች አንደኛው ሲሆን የክህነት አገልግሎት ላይ ስለተሰማራ ሌሎቹ 11ዱ ነገዶች የአስራት ግብር እየገበሩለት ነበር የሚኖረው” አለኝ።

ይህ አባባል ፓስተሩ በቤተክርስቲያን ገቢ ላይ ኑሮውን የመሰረተ አይስመስልበትምን? … አስቀድሞም የእረኛነት/የመጋቢነት/ ጥሪ ካለመኖሩ በተጨማሪ አገልግሎትን በገንዘብ እየተመኑ መንቀሳቀስ እንዴት ነው መንፈሳዊ ፍሬዎችን ለማፍራት የሚያስችለው? … ፓስተሩ ይህን አባባል እንኳን ለህዝብ መናገር ቀርቶ በልቡ እንኳን ማሰብ አልነበረበትም፥ ” በአእምሮው ብልጭ ቢልበትእንኳን ሠይጣን ያመጣው ሀሳብ ብሎ መገሰፅ እንጂ፥ እግዚአብሔር ቀርቶ ሰው እንኳን የሚጠየፈው የስንፍና ንግግር መናገር የለበትም። (በሌላ በኩል መንፈሳዊ ፍሬዎች በሌሉበት አስራት ክፈሉ ደግሞም ለዚህና ለዚያ መዋጮ አውጡ እያሉ ማስጭነቅ ብልጠት እንጂ መንፈሣዊነት አይደለም እያለ ነው ህዝበ ክርስቲያን። በተጨማሪም የደረጀ ከበደን 9 ቁጥር አልበም በመጥቀስ “የወንጌል ሰራተኞች ሳይሆን የወንጌል ተጧሪዎች /ጡረተኞች/ ይሆኑ እንዴ?” በማለት አስራት ከመክፈል የተቆጠቡ ብዙ ናቸው) “ስለ አስራት ማንም ሊጠይቀን አይችልም፥ እኛ ሌዋውያን ነንና” … በማለት ብሉይ ኪዳንን ከአዲስ ኪዳን ጋር በማነጻጸር የቀረበው ሎጂክ በእውነት በአዲስ ኪዳን ዘመን የሚሰራ ነውን? … ወንጌልን ክፍያ በመጠየቅ ለማገልገል ነው እንዴ የተጠራነው? (በደሞዝተኛነት የሚያገለግሉ ፕሮፌሽናል ፓስተሮች መኖራቸው ሳይዘነጋ) … ሃዋርያት እና ወንጌላውያን አገልግሎትን በገንዘብ ይለወጡ ነበርን? … ሀዋርያው ጳውሎስ “… የማንን ገንዘብ ወስጃለሁ? የማንኛችሁስ እዳ አለብኝ?…” በማለት ሲናገር ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ወንጌል በክፍያ አላገለገልሁም ከማለት በስተቀር።

አንድ ጓደኛዬ ” … ገንዘብን ከቤተክርስቲያን ውስጥ ቢወጣ አንድም ሰው ፓስተር ለመሆን አይፈልግም ነበር … ” ያለው ነገር ከአባባልነት አልፎ ትክክል እየሆነ መጥቷል።… እኔ ደግሞ ” … ፓስተርን ከመንፈሳዊነት እንጂ ከገንዘብ አስተዳደሪነት ነጻ ማውጣት ቢቻል ችግር ይፈታል …” እላለሁ። … ይህም ፓስተርን የገቢ ገንዘብ ተቆጣጣሪና የወጪ ቼክ ላይ ፈራሚ እንዳይሆን በማድረግ፥ መንፈሳዊ አገልግሎቱ ላይ እንዳያተኮር ጫና መፍጠር ነውና፥ ፓስተሩ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ከሆነ፥ የሚያስፈልገውን መሰረታዊ ፍላጎቱን በሟሟላት፥ ሙሉ ጊዜውን በወንጌል ላይ እንዲያደርግ ማድረግ የጥቅም ግጭትን በማስወገድ መንፈሳዊ ፍሬዎች/ውጤት ያስገኛል።

መፅሐፍ ቅዱስ ” … አንድ ባሪያ ለሁለት ጌታ መገዛት አይችልም፥ (አንድ ሰው ለእግዚአብሔርም ለገንዘብም መገዛት አይቻልም) … ” የሚለው መንፈሳዊ መመሪያ በላንካስተር አካባቢ በተግባር መታየቱ ማረጋገጫው 1ኛው/ መንፈሳዊ ፍሬዎችን ለማፍራት አለመቻል፥ 2ኘው/ ስጋዊ ስራዎች መንሰራፋት፥ 3ኛ/ በገንዘብ ምክንያት የጥቅም ግጭት መፈጠሩና የአያያዝና የአጠቃቀም ችግር መኖሩ፥ (በአንድትዋ ቤተክርስቲያን ገንዘብ መሰረቅም ተከስቶአል) 4ኛው/ በዋናነት የቤተክርስቲያን መሰነጣጠቅና የእግዚአብሔርን ህዝብም መበታተን አንዱ መንስዔ ገንዘብ መሆኑ ነው።

መፍትሄ፦

 1. ቤተክርስቲያን የምትመራበት የፋይናንስ መመሪያ ፖሊሲ ማውጣት ነው።
 2. ፓስተሮችን የመንፈሳዊ ዘርፍ ሀላፊ ብቻ በማድረግ ከፋይናንስ ሃላፊነት መለየት።
 3. የፋይናንስ ሀላፊ ከከስራ አመራር ቦርድ ውስጥ መሰየምና ተጠሪነቱን /accountability/ ለስራ አመራር ቦርዱ ማድረግ፥
 4.  ዝርዝር ስራዎችን በቅጥር ሂሳብ ሠራተኛ (Accountant) ማስራት
 5. ገንዘብ እንዴት፥ ለምንና መቼ እንደሚወጣ /Financial Plan & Budget / የፋይናንስ እቅድ/በጀት በማዘጋጀት በመስራት ግልፅነትን /transparency/ ማጋገጥ፥
 6. ለጠቅላላ ምእመናን ስብሰባ (ጠቅላላ ጉባኤ) የፋይናንስና የኦዲት ሪፖርት በየግዜው ማቅረብም ተጠያቂነትን (Accountability) ያረጋግጣል።

(ክፍል – 5 -)
4ኛ/ … ራእይ /Vision/ የማጣት ችግር፦
መፅሐፍ ቅዱስ “ራእይ የሌለው ህዝብ መረን ነው” (ምሳሌ 29፥ 18) እንደሚል ቤተክርስቲያን ራእይ አልባ ልትሆን የምትችልበት ምክንያት አንድም ራእይ ያለው መንፈሳዊ አመራር በማጣትዋ ነው፤ አሊያም ደግሞ ራእይ ምን እንደሆነ ካለማወቅ የሚመጣ ጉድለት ነው። ራእይ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቤተክርስቲያን (ከረጅም ጊዜ እቅድና እስትራቴጂ አንፃር) ከየት ተንስታ የት መድረስ እንደምትፈልግ የእድገት ህልም ነው። ራእይ በ10 ወይም 20 አመታት ውስጥ እውን ሊሆን የሚችል የጠንካራ ትጋት ውጤት ነው። … ቤተክርስቲያን ተልእኮዋን ካወቀች፥ ምን መቼ እንዴት እንደምትሰራ የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅድ ያስፈልጋታል፥ ራእይዋ ደግሞ እቅድዋን የተንተራሰ ሊሆን ይገባል። በራእይ ልዩነት ምክንያት አንዲት ቤተክርስቲያን በግልፅ በስምምነት በፍቅር ልትከፈል ብትችልም እንደ መሰነጣጠቅ የሚታይም አይመስለኝም። … ለምሳሌ አንድ ወገን Mega church (5 እስከ 10 ሺ ሰዎች የሚይዝ ትልቅ ቤተክርስቲያን) መስራት ነው ራእያችን ቢልና ሌላኛው ወገን ደግሞ፥ የለም፥ 1ሺ ሰዎች የሚይዝ 5 ቤተክርስቲያናት መስራት ነው የሚያስፈልገን ቢል፤ ይህ የራእይ ልዩነት ቤተክርስቲያንን በስምምነትና በፍቅር የሚለያይ ቢሆን ቤተክርስቲያን ተሰነጠቀች ሊባል የሚያስችል አይደለም።

ዋናው ነገር መፅሀፍ ቅዱስ ራእይ የሌለው ህዝብ መረን (ልቅ) ነው በማለት ካስተማረን፥ ቤተክርስቲያንን የሚያህል የምድርም የሰማይም ተቋም፥ ራእይ /Vision/ ከሌላት አሰራርዋ ሁሉ ልቅ ስለሚሆን፥ በሰው ሀይል፥ በጊዜና፥ በፋይናንስ አጠቃቀም ብኩን በመሆን ውጤት ሳታመጣ የትም ሳትደርስ በከንቱ ትቀራለች። ከዚህ የተነሣ የላንካስተር ቤተክርስቲያን ራእይ ስላልነበራትና በአጭር ጊዜም ይሁን በረጅም ጊዜ እቅድም ስላልተመራች፥ ወደ ሃያ በተጠጋ የእድሜ ዘመንዋን ምንም አይነት መንፈሳዊ ውጤት ሳታመጣ፥ የስራ ጊዜዋን፥ የምእመናን የሰው ሀይልዋንና የፋይናንስ አቅምዋን በከንቱ በማባከን አጥፍቶ ማሳያ ሆናለች።

መፍትሄ ፦
1ኛ/ የተበታተኑት መሪዎች ከተኩስ አቁም ስምምነት /No War No Peace/ በመውጣት፥ ጠቅላላ ምእመናንን እና ጠቅላላ መሪዎችን በሙሉ ያቀፈ የልብ እርቅ በማድረግ አንዲት ጠንካራ ቤተክርስቲያን ለመመስረት፥ በእውነተኛ ፍቅር መነሳት ያስፈልጋል። ለዚህም ወደ እግዚአብሔር በመመለስ፥ ሁሉንም የተከፋፈሉ ግሩፖች ምእመናንና ከግሩፕ ውጭ ተበታትነው ያሉትን ምእመናን ሁሉንም ያቀፈ አጠቃላይ ስብሰባ በመጥራት እውን ለማድረግ አሁንም ተስፋ አለ። የልብ ፈቃድ ከሰዎች ከመጣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለመልካም ነገር ምንግዜም በደጅ ነው።

ማጠቃለያ
ይህ ፅሁፍ በላንካስተር ባለችውና ተሰነጣጥቃ በተበታተነችው ቤተክርስቲያን ላይ ከማድርገው ዳሰሳዊ ጥናት (Assessment) ላይ የተቀነጨበ ሲሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የጥናቱ ሙሉ ውጤት ወደፊት ይወጣል። … በርግጥ ይህ ሰው ሰራሽ የቤተክርስቲያን የውስጥ ችግር ተከስቷልን? … ወደ ፔንሲልቬንያ ስቴት ላንካስተር ከተማ ብቅ በማለት ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ማህበረሰብ አባላትና የተበታተኑትን ደቃቃ ቤተክርስቲያናትንና ህብረቶችን በመጎብኘት መረዳት ይቻላል። … በሌሎች አካባቢዎችም ይህን መሰል የቤተክርስቲያን የውስጥ ችግር ሊከሰት እንደሚችል ስለሚታመን እንደ እግዚአብሔር ልጅነታችን ከሁላችንም አስተዋፅኦ ይጠበቃል። ስለሆነም በምንአገባኝነትና በምንቸገረኛነት ከፍ ሲልም በይሉኝታና በግብዝነት ወይም ባለማወቅ ወገኖቻችን በጥፋት ጎዳና ላይ ሲያዘግሙ ዝም አንበል።

በፍርድ /በህግ/ ቃል ብንጀምር እንኳን በፍቅር ቃል በምህረት/በወንጌል መመለስ እንዳለብን ጌታ አስተምሮናልና፥ በፅሁፌ ጠንከር ባለ የፍርድ ቃል የተናገርኩኋችሁትንና፥ በዚህም ቅር የምትሰኙትን በጌታ ወገኖቼን በሙሉ በጌታ ፍቅርና ቸርነት ታላቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ። የፅሁፌ አላማ ለጌታ ቤት በመቅናት ነው እንጂ፥ ስም ለማጥፋት ወይም ሌላ ተልእኮና ፍላጎት (motive) ኖሮኝ አይደለም። ነገር ግን ቤተክርስቲያን የጋራ ቤታችን ስለሆነች ብቻ ነው በትዝብትና በግብዝነት ለመመላለስ ስላላስቻለኝ ይህንን ጥናታዊ እይታ ከመፍትሄ ሀሳብ ጋር ለማስተላለፍ ግድ ሆነብኝ። ራሴንም ከደሙ ንፁህ ሳላደርግ ሁላችንም ክርስቲያናዊ ግዴታችንን መወጣት እንደለብን አሳስባለሁ።

አስተያየት ጥያቄና ትችት ካላችሁ፦ … 215-626-6342 ስልክ በመምታት ወይም ደግሞ፡ danruth2000@gmail.comኢሜይል በማድረግ ልታገኙኝ ትችላላችሁ።

የክርስቶስ ምህረት እና ፀጋው አቁሞናል! ሰላሙንና ፍቅሩን ያብዛልን

ከተመሰረተው ውጭ ሌላ መሰረት አለን?

ሰላም የሀገሬ ሰዎች እንዴት ሰነበታችሁ? አባ ወልደትንሳኤ አያልነህ የተባሉ የኦርቶዶክስ መምህር “የአዲስ ኪዳን ታቦት አሁን አድን” በሚል ርእስ የክርስትና  ማእከል የሆነውን ክርስቶስ ኢየሱስን የሚያሳይ መንፈሳዊ ትምህርት አቀረቡ፥ ሀብታሙ ታደሰ የተባለ ወንድማችን ደግሞ ስለ አባ ወልደትንሳኤ ትምህርት ከመፅሐፍ ቅዱስ ወይም ከክርስትና አስተምህሮ ውጭ አስተያየት ሰጠ፥ ነገሩ እንዲህ ነው። አባ ወልደትንሳኤ በክርስቶስ አዳኝነት ላይ በማተኮር፥ ስለብሉይ ኪዳን ታቦት ምንነትና ተምሳሌትነት፥ ስለ አዲስ ኪዳን ታቦት ምንነትና ስራ ወዘተ በመዘርዘር የጻድቃንና የመላእክት አማላጅነትን በመስቀሉ ስራ ወይም በደህንነት ላይ እንደተጨማሪ ድጋፍ ሳይጠቅሱ፥ ደህንነት የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ነው ያስተማሩት። አስተያየት ሰጭው ወንድማችን ግን ከመፅሐፍ ቅዱስ ላይ በርካታ ጥቅሶችን ቢጠቅስም፥ ሀይማኖታዊ ስርአትን በመንተራስ፥ በተለይም የቅዱሳንና የድንግል ማርያም አማላጅነትን ከወንጌል ጋር በመቀየጥ የደህንነት ወንጌልን የሚሸፍን ፅሁፍ አስነበበን። በወንጌል ላይ ተቀጥላ በመጨመር በክርስቶስ ስራ ብቻ የተገኘውን የደህንነት ወንጌል “በቅዱሳንና በድንግል ማርያም አማላጅነትና ድጋፍ ካልሆነ በስተቀር ደህንነት አናገኝም” አይነት ፅሁፍ፥ ወንጌልን ከመሸፈንም በላይ ወንጌልን ማቅለል/ማቃለል ሆኖ ሰለአገኘሁት፥ ለእርሱም ሆኖ ለሌሎች ወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ይህችን ምላሽ የግድ መፃፍ እንዳለብኝ ተሰማኝ። የናንተንም አስተያየት የመምህሩን ቪዲዮ ከተመለከታችሁ በኋላ ብትሰጡ ብዙ መማማር ይሆንልናል።

አማላጅነት እንዴትና በማን?
ወንድማችን ሀብታሙ ታደሰ የክርስቶስን የደህንነት ወንጌል በቅዱሳንና በድንግል ማርያም አማላጅነት ከደገፈበት ጥቅሶች መካከል የሚከተለው አንዱ ነው፥ ” የአብ ልጅ ለመሆንም መንገዱ አንድ ነው፥ እሱም ክርስቶስን ማመን፥ ለዚህም ነው መንገዱ እኔ ነኝ፥ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ” ካለ በኋላ ወንድማችን ተሳስቶ ለማሳሳት የሞከረው፥ ” ይህ ማለት ግን የቅዱሳን ምልጃ፥ የእመቤታችን አማላጅነት አያስፈልግም ማለት አይደለም ” በማለት ነው። በዚህም ወንድማችን በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ያልተጻፈ ቃል በመጨመር የእግዚአብሄርን ቃል የሚጣረስ ህፀፅ ፅፏል፥ ይህም የክርስቶስን ንፁህ ወንጌል በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በመበረዝ ሰዎችን ከደህንነትን መንገድ ለማሳት መታተር መሆኑን ያሳያል። አማላጅነትን በተመለከተ የሚያደነግር ትምህርት በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ አልተጻፈም። ይኸውም ከእኛ በፊትም ይሁን በዚህ ዘመን ያሉት ቅዱሳን በአፀደ ስጋ (በህይወት) እስካሉ ድረስ እንጂ፥ ከሞቱ በኋላ ሊያማልዱ እንደማይችሉ መሆኑ ይታወቃል። እንደዚሁም መናፍስት የሆኑት የእግዚአብሔር መላእክትም ቢሆኑ፥ ከእግዚአብሔር ወደ ሰዎች እንጂ (መልአኩ ገብርኤል ለቅድስት ማርያምና ለዳንኤል መልእክት እንዳመጣው) ከሰዎች ወደ እግዚአብሔር ምልጃና ፀሎት ወይም መልዕክት መላእክት ሲወስዱ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ አንድም ስፍራ ስላልተጠቀሰ መላእክት አማላጅ አይደሉም ማለት ነው። ጻድቃንና ሰማእታትን በተመለከተም ከአፀደ ስጋ ከተለዩ በኋላ (ከሞቱ በኋላ) እንደሚያማልዱ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሳይጠቀስ፥ ወንድማችን ከየት አምጥቶ ነው ያማልዳሉ ብሎ የሚጠቅሰው? ይህ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ መጨመርና መቀነስ አይደለምን? (የዮሀንስ ራእይ መፅሐፍን ማንበብ ምላሽ ይሰጣል) ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቅዱሳን በህይወት ሳሉ ምልጃና የክርስቶስ በአብ ቀኝ ስለእኛ ማማለድ በፍፁም አንድ አይደሉም፤ የተለያዩ ናቸው። ይኽውም መፅሀፍ ቅዱስ “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” (ዕብ 7፥25) እንደዚሁም “የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” (ሮሜ 8፥34) እንደሚል፥ የክርስትና ዋናው ቁልፍና መሰረቱ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ከፈፀመው የደህንነት ስራ የተነሳ፥ አማላጃችን ክርስቶስ እንጂ መላእክትና ጻድቃን እንደሆኑ መፅሀፍ ቅዱሳችን ፈፅሞ አያስተምርም።

ኦርቶዶክሳዊነት እና ክርስትና
ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባህላዊ ስርአቶችና እሴቶች ከወንጌልና ከደህንነት ጋር ሳልደባልቅ ትልቅ አክብሮት አለኝ።… በመሆኑም መልካም ባልሆነና ባልተገባ ንግግር ጥንታዊቷን እናት ቤተክርስቲያን ልናገር ፈፅሞ አይገባኝም፥ አልችልምም። ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ክርስትናን ለዘመናት በተጋድሎ ጠብቃ ያቆየች፤ ኢትዮጵያዊ የሆነ የፅሁፍ ፊደልና የዘመን መቁጠሪያ (ካሌንደር) በመስጠት የራሳቸው የፅሁፍ ቋንቋና የዘመን መቁጠሪያ ካሌንደር ካላቸው እጅግ ጥቂት የአለም ሀገራት መካከል እንድሆን ያስቻለችን፥ ወዘተርፈ በመሆኑ ሁሉም ሰው ሊያከብራት ይገባል። … ከዚህ በተጨማሪም እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያንን በስነምግባር ኮትኩታ ያሳደገችና ያስተማረች በመሆንዋ ውለታዋን ቢያንስ በማክበር መግለጽ ይገባል። በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያገኘሁት በስነምግባር መታነፅ ለእኔ ከልጅነት ትዝታ በላይ ነው። …ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ ሀይማኖት የሚያድን ባለመሆኑ፥ ምንም እንኳን አያቴ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንቱ የተባሉ ትላቅ ሰው የነበሩ ቢሆንም፤ ወንድሜና ሌሎች ቤተሰዎቻችንም ዲያቆናትና አገልጋዮች የነበሩ ቢሆንም (ደህንነት በውርስ ቢገኝ ጥሩና ቀላል ነበር) ለሰዎች ደህንነት ምንም ፋይዳ በሌለው የጻድቃን የመላእክትና የማርያም አማላጅነትን፤ እንዲሁም ተቀፅላ አዋልድ መፃህፍትን፥ ገድላትና ድርሳናትን በመተው፥ አባ እንዳስተማሩት የአዲስ ኪዳን ታቦታችንና አዳኛችን ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው ብዬ በማመን እኖራለሁ። “ፃድቅ ግን በእምነት ይኖራል” (ዕብ 10 ፥ 38) ተብሎ እንደተፃፈ። በዚህም የክርስትና ሀይማኖቴን ወይም እምነቴን በማጥበቅ ያዝኩ እንጂ ሀይማኖቴን መቀየሬ አይደለም። ሀይማኖትን መቀየር ከእስላምና ወደ ክርስትና ወይም vise versa መለወጥ እንጂ ከኦርቶዶክስ ወደ ፕሮቴስታንት ወይም ከካቶሊክ ወደ ኦርቶዶክስ ወዘተ መግባት አይደለምና።

ደህንነት በማንና እንዴት?
ኦርቶዶክሳውያን ደህንነት ለማግኘት ወይም ክርስቶስን የግል አዳኝ አድርገው ለመቀበል የግድ ወደ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን እየመጡ እጃቸውን ወደ ላይ እየሰቀሉ ጌታን ተቀበሉ ሊባሉ እንደማይገባቸውም አምናለሁ። እዚያው ባሉበት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆነው ደህንነትን ሊያገኙ ይችላሉ። እንደ አባ ወልደትንሳኤ የመሳሰሉ በሳልና የወንጌልን እውነት በትክክል የሚያስተምሩ ታላላቅ መምህራን መኖራቸው እየታየ ስለሆነም በርቱ ህይወት ያለበትን መንገድ ያዙ ማለት ብቻ ነው የሚገባን። … ከወንጌል ትምህርት አንፃር የዛሬዋ ኦርቶዶክስ እንደ ጥንትዋ ኦርቶዶክስ አይደለችም። በተለይ ከአፄ ዘርአያእቆብ ዘመን በኋላ ነው የኦርቶዶክስ ክርስትና ተበርዞ ባህል የነገሰበት፤ ወንጌል ያለ ፃድቃንና ያለ መላእክት አማላጅነት እንደማይሰራ ሆኖ የተቀየጠው። ይህ ቅይጥ ሃይማኖት የዘላለም ህይወት አይሰጥምና ወደ ቀድሞው ንጹህ ወንጌል በመመለስ አዲስ ህይወት /ደህንነት/ ማግኘት ይገባል። ይህም ሀይማኖትን መቀየር ሳይሆን ማጠንከር ወንጌልን አጥብቆ መያዝ ነውና። … በተለይም ተስፋ ገብረስላሴ ዘብሄር ቡልጋ እና የመሳሰሉት የህትመት ቢዝነስ ከማስፋፋት አንጻር ጽፈው ያሰራጩት ኢ-መፅሀፍ ቅዱሳዊ የድርሳናትና የገድላት ሰው ሰራሽ መፃህፍቶች/ትምህርቶች አርነት በመውጣት (አንዳንዶቹ ሰይጣንን በድግምት መሳብ የሚያስተምሩ ናቸው) የእግዚአብሔርን ቃል መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ ማጥናት ህይወት ይሰጣል፤ … “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም ” (ዮሐ 1፥3) ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻውን ለደህንነታችን በቂ በመሆን ስራውን ጨርሶ ተፈፀመ ስላለ፥ የመላእክትና የጻድቃን እርዳታ ወይም ተቀጽላነት እንደሚያስፈልገን በመጽህፍ ቅዱስ ላይ አልተገለፀም።

መሰረት ማነው?
ከተመሰረተልን መሰረት ይኽውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ውጭ ሌላ መሰረት ልንመሰርት እንደማንችል መጽሀፍ ቅዱስ በግልጽና በቀጥታ ያስተምራል፥ እንዲህ በማለት “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (1ኛ ቆሮ 3፥11) ክርስትና በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ስራ ደህንነት ያገኘንበት መተኪያ የሌለው ሰማያዊ ስራ ስለሆነ ከመስቀሉ ስራ ላይ ተደርቦ ደህንነታችንን የሚያረጋግጥ የቅዱሳንም ሆነ የመላእክት ሌላ ተጨማሪ ስራ የለም። የጻድቃንንና የመላእክትን በአላትና ውዳሴ በመውደድ ተጨማሪ ወይም አጋዥ የደህንነት መንገድ አድርገን መውሰድ አንችልም። ክርስትና በክርስቶስ ብቻ የተሰራውን የሰማዩን ቤት ለመውረስ በምድር ሳለን እለት እለት የምንሰራበት (“ሰ” ይጠብቃል) በመንፈስም ክርስቶስን ወደ መምሰል የምናድግበት እንጂ የመላእክት እና የፃድቃን አገልግሎት እያነገስን የምንኖርበት ህይወት አይደለም። በመሆኑም መንፈሳዊ ትምህርቶቻችን በሙሉ መሰረታቸው መጽሀፍ ቅዱሳዊ (Bible Based) ማእከላቸው ደግሞ የክርስቶስ ኢየሱስን አዳኝነት ብቻ የሚያሳዩ (Jesus Centered) ከመሆን በስተቀር ሌላ ትምህርት ማስገባት መናፍቅነት ነው። ምድራዊ ሃይማኖታዊ ስርዓትንና የፃድቃንና የመላእክት አማላጅነት ከመስቀሉ የወንጌል ደህንነት ስራ ጋር በመደባለቅ ማምለክ ዘላለማዊ ህይወት አያስገኝም። ይህንን በማድረግም መንፈሳዊ ጉድለት እንጂ ህይወትን አይሰጠንምና።

ትምክህት በማን?
ሀይማኖታችን ቀጥተኛ /ኦሮቶዶክስ/ ከሆነ ስብከታችን ለዳንበት ለወንጌል እንጂ ለመላእክትና ለቅዱሳን አይሆንም። ሰው ሰራሽና አሳች የሆኑትን የአዋልድ፥ የድርሳናትና የገድላት መፃህፍት ትምህርቶችን ሳንጨምር፤ የእግዚአብሄር ቃል ንፁህ ወንጌልን ሳንበርዝ፥ ፃድቃንና መላእክትን ተቀፅላነት ወይም አማላጅነት ሳናስገባ ብቻ ነው እምነታችን ወይም ሀይማኖታችን ቀጥተኛ ወይም ኦርቶዶክስ ሊሆን የሚችለው። “ወደ አለም ሂዱ አህዛብን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው” ተብሎ የተፃፈው ለሚጠፋት ሰዎች ነፍስ ግድ ብሎን እንድንመሰክር የታዘዝነው ሰለክርስቶስ እንጂ ስለመላእክትና ስለጻድቃን ተጨማሪነት/አማላጅነት/ አይደለም። “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ” (ገላትያ 6፥14 ) ተብሎ እንደተጻፈልን፥ ትምክህታችን ክርስቶስ ኢየሱስ እንጂ መላእክትና ጻድቃን አይደሉም። እንደዚሁም በ1ኛ ዮሐንስ መልእክት ቁጥር 21 ላይ “ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” እንደሚል በሰማይም በምድርም ጠበቃችን እርሱ ስለሆነ ትምክህታችን እግዚአብሄር ብቻ ነው። ስለሆነም ኦርቶዶክሳውያን እንሁን ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ወይም ደግሞ ካቶሊካውያን ከክርስቶስ ትምክህት በበስተቀር ጻድቃንም ይሁኑ መላእክት ወይም ታቦታት ትምክህቶቻችን ከሆኑ ጣኦቶቻችን ናቸው። ይህ ከተመሰረተው ውጭ ሌላ መሰረት መመስረት ነውና።

ቃለ ህይወት ያሰማልን !
እግዚአብሄር ማስተዋልን ይጨምርልን !
ሰላም ለኩሉኩሙ !

The Need for Economic Equality in the United States of America

 The Need for Economic Equality in the United States of America

(Originally Submitted to the Sociology Department of HACC, USA)  

                                                             (by Yosef Degefi & Kathleen Dissler)

                      A Review of the Literature

Among the many inequalities in the United States of America, it would appear that they are shrinking or the tables are turning to a more level playing field. Racial, Gender, and Religious inequalities are all examples that most people would generally say are lessoning. As a whole, it would appear that the United States has come a long way in the past 50 years. However, there is one inequality that does not seem to be shrinking and in fact is growing Kelly (2008). This inequality is in regard to our income and assets. It is economic inequality. The Occupy Wall Street Movement rally helped bring attention to this subject but it has been happening for quite some time now, unbeknownst to most of the citizens. People are beginning to rise up and say that there is something wrong. It would behoove us to listen. Things like poverty, unemployment, and debt will only get worse if we don’t do something. Right now, the United States stands at a crossroads Stieglitz (2012). We can continue in this pattern and we will turn into what economists call a ‘dual economy’. The haves and the have-nots will live side by side in completely different worlds, like many developing countries. The rich will live inside gated communities, with their luxury homes, private schools, and top-notch medical care. Meanwhile, on the outside of that same gated community, the have-nots will live, struggling to make ends meet and riddled with anxiety over the future of their children. The other option is a brighter one. Freeman (1999) underlined the following points, that America has cause for concern due to the growing or widening income gap between the poor and the rich, which causes not only an economic inequality, but also distressed society in the most advanced and democratic nation of the world.

Behind the business cycle lies a two-decade-long trend toward widening inequalities of wages, of fringe benefits like pensions and health care, and of wealth. It is a new inequality. We are becoming the two-tiered society. In the top an expanding numbers of well-educated managerial, professional, and technical workers who spend most of their day identifying and solving problems-often utilizing new computer technologies-and sell their symbolic and analytic insights to an ever widening market, often spanning the globe. In the bottom, an expanding number of relatively poorly educated women and men, who provide an array of in-person services-retail, restaurant, hospital, custodial, child care, security, and other forms of tending. Should you care? If the poorer member of our society were gaining only a bit of ground while the richer were gaining far more, you might still have cause for concern. (p. viii).

Freeman lay emphasis on that America has cause for concern for the reduction of economic inequality. In spite of the growing income for the rich, the working class remains underprivileged, deprived or may be gaining only a bit of ground. The gap between the rich and the poor will not be annihilated, but it will be narrowed significantly. The United States could become the land of opportunity again, like it once was. As a result, the need for the change is crucial. America requires making compulsory changes on the economic inequality for the safety and security of its citizens.

It is our theory that the main cause for the growing income inequality in the USA is that the government policies favors the rich, giving them unfair advantage and further polarizing the two ends of the spectrum. In this research paper, we will ascertain if this is true and respond to the following questions:

What is the history of economic inequality in the United States?

What is causing economic inequality, the polarizing trend to continue?

What are the consequences of the economic inequality?

How is this affecting citizen today? What groups are in relation to this event?

What are solutions to the growing economic inequality? Can it be stopped, fixed?

Answering these questions and understanding the issues will highlight the complexity of this problem and underscore the need for an urgent solution. What is the history of economic inequality in the United States? Economic inequality or the income gap is nothing new in the United States. Will ford I. King was the first person to study this when he wrote, “The Wealth & Income of the People of the United States” in 1915. His publication was novel because income information was not officially studied or evaluated until the 1930’s. One reason for this was because at that time, wealth was not determined by how much money you had. Wealth was determined by the amount of property owned since people lived off the land. In King’s book, he noted that even in 1910 the richest 1% possessed about 15-18% of the nation’s income (eventually prompting the modern income tax). These figures only continued to rise until the stock market crashed in 1929. In 1928 the 1% held 24% of the nation’s wealth and during the 1920’s the bottom 95% saw their income drop from 72% to 64%. Most people did not worry about this because so-called ‘financial experts’ were telling the people not to worry about it (sound familiar?). The next year the stock market collapsed. King had some ideas on how the problem could be solved, though some were pretty extreme. Among them, he believed in implementing population control among the poor, and limiting immigration. He did not believe in redistribution. He felt that the top income tax rates were too high and that the capital gains & corporate tax shouldn’t exist. He also felt that having a minimum wage was ‘dangerous’ Noah (2012).

The next notable economist to study these things was Simon Kuznets, (inventor of the measurement of GDP – Gross Domestic Product). He and King did not see eye to eye on many of the issues. Kuznets believed that as society became more advanced, income would become more equal. His hypothesis proved to be true for a short time, during a period known as the Golden years. What Kuznets did not predict was that his original hypothesis would not hold true after the Golden Years and by the 1980’s they were long gone. Economic inequality was again beginning to increase with the top 10% holding 41% of the income Noah (2012).

The Golden Age refers to a span of about 50 years during which the economy flourished and economic inequality equalized. Among many things, credit for the Golden Age has been given to “the National Industrial Recovery Act (1933), which created a federal minimum wage… and a maximum work-week…” World War II is also often cited as a means of the economy equalizing during this time. Although the rich were getting richer, it was not disproportionate to everybody else Noah (2012). By the 1980’s the Golden Age was officially over. In hindsight, median incomes were stagnating in the 1970’s and then “the Arab members of the Organization of Arab Petroleum Exporting Countries retaliated against U.S. support for Israel… by imposing an embargo that quadrupled the price of oil…” This immediately caused a 16 month recession. When it was over, median incomes did not increase, like they were predicted to. During the late 1980’s and early 1990’s the economy did grow, but a staggering 80% of the income increase went to the top 1%. And even though productivity increased 20%, median incomes did not increase Noah (2012).

Today, Uruguay, Nicaragua, Guyana, & Venezuela (all part of Latin America – which has been described as ‘failed societies’ because of their poverty levels) all have greater income distribution equality than the USA. In fact, we are more on par with Argentina. And while their economies continue to equalize, ours continues to become more polarized. So how did we get here and why haven’t people seemed to notice or care? Americans continue to have the enduring belief in upward mobility and American exceptional-ism. They believe that if any child really wanted to they could grow up and be president and this defines the American dream. We are still holding on to our ‘rags to riches’ stories, desperately hoping that we’ll be next. This is why people continue to not take heed warning signs or understand the problem with economic inequality.

What is causing economic inequality, the polarizing trend to continue? The primary things that affects the income of the majority is, the failure policies of the government, like tax cut for the rich in the name of job creation and out sourcing or shipping the job abroad looking for cheap labor. These two policies alone have made big impact on the income of the working class. The income losses further causes for the increase of unavailability of access for the improving of the livelihood of the people that result in the increases of poverty. Freeman (1999) argues that the government policy failure causes new inequality which resulted in increased poverty.

Income inequality has skyrocketed. In 1979, for example, on an hourly basis, the top docile of men earned four times what the bottom docile earned; by 1993 they were earning five times as much. This rise in inequality occurred in in the context of general wage stagnation: the median male worker, for example, earns about 13 percent less than the median male 15 years ago-despite his being older and having more education…Inequality in earnings has led to inequality family income. Virtually all of the past decade’s economic growth has gone to the upper 5% of families.  Since the early 1970’s, while the income of the top 1% of household has doubled, family and household incomes have stagnated or declined for the 80% of the population (p. 7).

According to Freeman (1999), the big losses in the income distribution for the people at the lower level have resulted in the greater than before poverty. That is Americans living in poverty rise by 4 percent. “Heavy income losses at the bottom of the distribution have resulted in increased poverty. The share of Americans living in poverty rose from 11.2 percent in the 1974 to 15.1 percent in 1993, and the ‘poverty deficit’ or amount of money needed to lift all to the poverty line-doubled in real term” (p.7-8). He further argues that, in spite of employment progression, earning is deteriorating for the majority, because the distribution is imbalanced, “we have had job growth and income has declined for many and been spread more unevenly” (p.10). “In sum, current strategies run the gamut from inadequate to shame. There is no reason to believe that they will solve the new inequality problem” (p.11). In consequence, the government policies and strategies are not helping to eradicate poverty in the lower majority class, instead, it favors the “haves” not the “have not”.

What are the consequences of the economic inequality? How is this affecting citizen today? What groups are in relation to this event? The main worry of the increasing of the economic inequality in America is that the intensification of poverty or the growing of economic insecurity that so many American feel. Stiglitz (2012) contends that the increase of economic inequality has consequential of class warfare.

The slogan “we are 99 percent” may have marked an important turning point in the debate about inequality in the United States….Those in the 99% are continuing with “we’re all middle class” tradition, with one sight modification: they recognize that we are actually not all moving up together. The vast majority are suffering together, and the very top – 1 percent – is living different life. The “99 percent” marks an attempt to forge a new coalition-a new sense of national identity, based not on fiction of a universal middle class but on the reality of the economic divides with in our economy and our society (p. xvi)

For years there ware transactions between the top and the rest of the society that the majority gets share in job opportunities and the like, even when the top get bigger share, however now a days, because of economic insecurity and the strengthening of poverty, this agreement has come apart. Stiglitz (2012) further argues that, “Widely unequal societies do not function efficiently, and their economies are neither stable nor sustainable in the long term. When interest group holds too much power, it succeeds in getting policies that benefit itself, rather than policies that would benefit society as a whole” (p. 83). The more the gap between the rich and the poor is widening the more the society is dysfunctional. The Washington Post in its January 2013 edition shows that, the growth in the levels of the working poor matches with the continued growth in income inequality.

Nearly a third of the nation’s working families earn salaries so low that they struggle to pay for their necessities. “Although many people are returning to work, they are often taking jobs with lower wages and less job security, compared with the middle-class jobs they held before the downturn,” according to a report released Tuesday by the Working Poor Families Project, a national initiative aimed at fostering state policies to help low-income working families. With the nation’s economy in recovery, more than 70% of low-income families and half of all poor families were working by 2011. But they did not earn enough to cover their basic living expenses.

The Washington Post stress that, the level of the working poor has grown, despite the fact that many people are returning to work. And also due to the escalation of the living cost, the incomes do not enough to cover the basic needs of the poor families. As a result, it is clear that the middle class and the working poor people citizen are highly affected by the big income gap that comes due to unfair economic distribution. The majority of the society, the bottom multitudes is extremely impacted by the lack government economic policy that treats all citizens equally and fairly.

What are solutions to the growing economic inequality? Can it be stopped, or fixed? In the free market economic society, the capitalist system of democratically elected administration, it seems that the government has no right to decide “who gets what?” However, the government has many mechanisms to maintain the social and economic wellbeing, equality of its citizens. One of these is fair distribution economy to all citizens, by means of tax increase on giant corporations and supper rich, by increasing the minimum wages for the working poor, by educating and nurturing the new generation, by developing infrastructures facilities, by offering affordable health insurance for hard working people etc. Kelly (2008) argues that the government has power to impact the economic domain, “Now as much as ever, government is pervasive. Regardless of values like liberty and freedom and limited government, the state influences numerous aspects of life” (p. 23). Moreover, Freeman (1999) states the following points in his “Five Strategies for Raising the Bottom (And Relieving Inequality) title, “I believe our goal should be to increase the earnings and living standards of those at the bottom – thereby diminishing inequality by improving their position relative to better – off – rather than level down those who are prospering without lifting up the poor” (p. 11). The author further argues that America needs income redistribution from those who have been favored a lot for decades, “America a raise, with the biggest part going to low-paid workers. The result will in fact be a substantial income redistribution from those who have gained so much in the past 15 to 20 years, not a redistribution for its own sake, but, for its result in improving the living standard of  those now at or near the bottom” (p. 12). This is all about making the macroeconomic system working better for benefit of all citizens, not just for 1 percent, functioning effectively and responsibly.

Economic inequality can be stopped, or fixed through government programs and policies, when society is dysfunction or bad social outcome is observed. Good governance is capable in making out different economic circumstances, for instance, more tax increases on the upper top economic class, when the operations of market not result for the better outcome or social wellbeing of the society. Rising minimum wages, encouraging the growth of union organization in improving the position of low wage workers, making affordable college fees to enhance advancement for younger generation and investment in children etc. could be among the major actions that government could take for the safety and security of its citizens. With regard to supplementing market wages freeman (1999) summarizes the following statement. “Any scheme to address the problem of the current poor, including the working poor, and of those who even in an ideal future will run into economic difficulties, requires supplementing market wages” (p. 20). With reference to investing in children, Freeman and Hartmann (1999) study demonstrates that the need for shift resource through inventing in children. “A much investing in children-free universally available child care, more health care, and income support when needed is warranted, … for many reasons. Paid family leave for working parents is another way to shift resources to the benefit of the young” (p. 37).   

References

Fletcher, M. A. (2013, January 16). Ranks of Working Poor Increasing Despite Signs of Recovering Economy. The Washington Post. ProQuest LLC.  Feb 19, 2013.

Freeman, B. (1999). The new inequality: Creating solutions for poor America. Boston: Beacon Press.

Fraser, S. & Gerstle, G., (2005). Ruling America. A History of Wealth and Power in a Democracy. Harvard University Press.

Inhaber, H. & Carroll, S. L. (1992). How rich is too rich?. Income and wealth in America. New York: Praeger.

Kelly, N. J. (2011). The politics of income inequality in the United States. Cambridge: Cambridge University Press.

Noah, T. (2012). The great divergence: America’s growing inequality crisis and what we can do about it. New York, NY: Bloomsbury.

Shipler, D. K. (2004). The working poor: Invisible in America. New York: Alfred A. Knopf.

Stiglitz, J. E. (2012). The price of inequality: [How today divided society is endangers our future]. New York: W.W. Norton & Co.

Stricker, F. (2007). Why America lost the war on poverty– and how to win it. Chapel Hill: University of North Carolina Press.

Winne, M. (2008). Closing the food gap: Resetting the table in the land of plenty. Boston: Beacon Press.

Nelson Mandela, the Iron willed leader who beaten apartheid and brought Freedom and Equality for his Nation, Undeniably failed in fighting Economic Inequality among his Citizens:

Nelson Mandela, the Iron willed leader who beaten apartheid to bring Freedom and Equality, undeniably failed in fighting Economic Inequality:
(Yosef Worku Degefe)

Nilson Rolihlahla Mandela was born on 18 July 1918 in Qunu, South Africa. Son of a tribal chief, he studied law and became one of the South Africa’s first black lawyers. In the 1950s he was elected as a leader of the youth wing of ANC (African National Congress) liberation movement. The country’s white minority rulers’ prohibition of ANC in 1960, Mandela turns into conviction that armed struggle was inevitable. Inspired by the African freedom fighters from colonization and also Cuba’s revolution, he organized a military underground movement that engaged in overthrowing the South African apartheid regime.

Military Training in Ethiopia
In 1962 Mandela had an underground military leadership training in the only non-colonized African nation, Ethiopia. The alive evidence, eye wetness, Colonel Fekadu Wakene, high ranking Ethiopian Military training commander taught Nelson Mandela guerrilla warfare. However, soon after Mandela finished his military leadership training and back to his homeland, he got arrested and sentenced to life imprisonment for high treason and conspiracy against the South African apartheid regime. From 1964 to 1982 he was confined to the notorious prison called Robben Island together with several other resistance leaders. He was then moved to prison on the mainland until he was released in 1990. During his imprisonment for 27 years, Mandela became a uniting point for all Africans and the world’s most famous political prisoner. Mandela won the world Nobel Peace Prize sharing with the man who had released him from prison, the last apartheid President, Frederik Willem De-Klerk. Both these men won Nobel Peace price for the reason that they agreed to resolve the social conflict on a peaceful transition to majority rule, restore justice, and equality for all through setting a constitutional democratic leadership in South Africa, but, not for Economic Equality.

Believe in People Power
Mandela is uniquely special in his leadership philosophy unlike most African leaders. He does not turn out to be a dictator or even semi authoritarian ruler. Instead he turned out to be an unpretentious democratic leader. Soon after he took power he choose not to taking revenge on the apartheid regime oppressors, the white minority and put another chaos or damage on his nation. Throughout his term of presidency he keeps integrity leadership characteristic of transparency and accountability. Most importantly, Mandela has shown to the world that he is a leader who believes in people power. He Knows that how to use the strength of people. As a result, recognizing, understanding and engaging the strength of people gave him unwavering power. More over, Mandela is an effective sociopolitical leader who choose servant leadership style that empower him building good relationship with empathy and connectedness with people. Because of this people don’t hate to call him their leader. Acquiring conceptual and interpersonal leadership skills from his law school, from vast reading while he was still in prison and through building good social interaction with many and different people around the world make him great world figure.

Distinguished Leader
Nelson Mandela has a distinguished quality of trait, capacity, and skill in leadership. Among other facets of his leadership characters, his forgiving nature is one of his most acclaimed personality traits. Mandela forgive the oppressor, the white minority ruler and work in unity in the racially despaired communities of South Africa. He loves people, not position or power. Mandela once said that “None of us Acting Alone can Achieve Success”. He never has shown negative leadership attributes like, ruthlessness or cruelty, asocial, egocentric, non-cooperative or in general dictatorial leadership behavior. This is because he chooses people over power. As a result, left a great legacy that lives forever. Trustworthiness or honesty, unprejudiced, dynamic or vibrant, motivator, great communicator, authenticity, and farsightedness are among Mandela’s positive leadership attributes. He is a compromiser and a win-win problem solver. Mandela’s optimism comes from his humanistic nature. Thus, he has played a great role in diminishing extremism in South Africa. One of the most crucial, great lessons that Nelson Mandela teach for the disturbed world is that how to resolve social conflict. Mandela deeply understands that social conflict requires fundamental resolution, not political games or sabotages. Being a charismatic leader with a great personality and a strong will help Mandela work for the values that he desires others to adapt. In addition, Mandela inspires people with his eloquent speeches and his books that put an enormous impact on people even outside his area.

President Obama in his speech at Mandela’s funeral challenged the world leaders by saying that, how well have leaders applied lesson from Mandela in their own leadership style? Mandela is also an intelligent leader, good perceptual skills and reasoning ability. Therefore, as a good leader he knows that there are limits to what he can do, and thus he pay attention to what others says about his leadership. What is more about Mandela’s leadership ability, he set up a vision to reach, a goal to achieve and activities to perform with the people, for the people. He is a visionary leader with great moral courage. He had a clear vision for his country he loved most and wanted to live in. He creates a compelling vision that challenges and changes his and other people behaviors. He delivers a picture of the future of South Africa as his vision.

Conflict Resolution
Mandela struggles based on his core values such as Freedom, Justice and Equality for all. He faces a tremendous amount of challenges, but his farsightedness, endurance and trust in people help him out in handling conflicts and find resolution. In addition, Mandela sociability or outgoing personality highly help him establishing pleasant relationship with people including outside his party, supposed to be his enemies. In 1985 Mandela was offered freedom by Peter Botha, the then South Africa’s apartheid ruler if Mandela would renounce his fight against the apartheid regime and he refused. He feels strong and positive in his aim and stands and is certain about what he is doing. Later, during his negotiation with apartheid rulers Mandela follows the most important conflict resolution approaches. These are Compromising and Collaborating styles of approaching conflict.

Mandela has no “us” and “they” or … “I am right” and “you are wrong ” mentality, a mind set up dangerous in personal as well as in societal interactions among tribes, religious institutions and among Nations in the world at large. In his argument with the last South African Apartheid leader, Mandela seek a position in which both party, Mandela’s ANC & Apartheid can accept. Mandela is also an ethical leader who has a characters of Respect, Fairness, Caring, Responsibility and Citizenship. Moreover, his actions depicts that he follows Servant-Leadership style. Servant leader does not make people serve him, instead he serves people and brings Justice for all. For this reason, Mandela achieves astonishingly excellent outcomes. Mandela was the right person at the right position in the South African context. He shows morality in his leadership, he never abuse power, he was free of corruption, and he never played political sabotages for his interest. Nelson Mandela fought for Justice, Equality, and Freedom and most importantly he struggled against apartheid or a racial segregation policy in South Africa and he won.

The Failed Leader
With blacks constituting more than 80% of South African population, the magnitude of black poverty is greater in South African than any country in the world. IMF report declares that, “South Africa is notorious for having gross income inequality. Its ‘GINI’ coefficient – a standard for measuring income inequality – is one of the highest in the world. The World Bank computed it at 63.1 in 2009, with zero being absolute equality and 100 absolute inequality”. Thus, It is odd to say that Mandela was not able to understand that the unhealthy side effect of economic inequality which creates social disparity or unrest in Africa. IMF discovers that economic inequality brings damaging to the economic growth. Its up to the nations to mange it. As a result, Nelson Mandela is a leader who failed to fight for Economic Equality not only in South Africa, but also in the African content. Mandela has never tried to fight for Economic Equality. He did take no measure at all to solve income inequality crisis among his fellow citizens. It does not seems at all that Mandela did not know the need for Economic Equality. What really made Mandela carless with regard to change in Economic Equality.

Economic Inequality and Corruption
According to IMF, the US is the second largest Income In-equality nation next to South Africa. Apart from political considerations, narrowing down the gap of the economic inequality among people helps nations for consistent economic and social development which ultimately create non violent generation or society. Head of states of the world have failed to understand that fighting for political power or religious freedom has an implied meaning for fighting for Economic Equality. America is the world’s power not because of its population, (accounts 5% of world population.) but because it has very strong economy. Money mater most. People or individuals Economic Power should not be under estimated. Minimum wage is unfairly poor in the US. Low wage workers are not paid what they deserve. Many believe that the main causes of the Baltimore riot is not racial, but economical, Economic disparity. Race was the cover up, deep inside the soul of the people, there demands for economic equality. Poverty is the worst of all enemies of the people. Nations of the world need to fight for economic equality for in every corner of the world people are desperately looking for food and homes to live in. Economic Equality is a determinant factor that need to be addressed in all over the Nations including special focus on black poverty in the US.

Seeing the Iron willed leader who won the fighting for freedom and Equality, has failed fighting for Economic Equality is absurd, laughably foolish, and senseless. Black people in today’s South Africa, cause they are desperate in their economic status, they fight back in Xenophobia. They are fighting foreigners living in South Africa as it is seen in a mass riot and killing people in April 2015. Defending Mandela’s legacy South Africa and other nations over the world who are anxious about Economic Inequality, Get up and narrow down this gap. Leader of nations fight political and economic corruption. Rich people be fair, distribute your wealth to the poor wisely, like through education, health care etc. World leaders of G8 or G20 or IMF, World Bank etc. think critically act wisely and genuinely to bring a change. Believe in people not in power. If not our world may face another chaos, revolution. People may rise for revolution demanding economic equality which may mightier than the famous industrial or the socialist (communist) revolutions. I believe that the next social unrest around the world would not be about politics or religion, but it is all about economic inequality.

Our world is falling apart due to Economic Inequality. If World war III starts, it couldn’t be for some other cases, but for Economic Inequality. Who am I to say this? Am not a Politician, a Religious fanatic man, or a Technocrat, an Economist, or Social reformer, or a Revolutionist etc., but I am an ordinary world citizen, community concerned guy. I am just demanding fairness from the world super rich to come down and narrow the income gap. Otherwise, we cannot clean up the world mess easily. Let us be fair in life. Let us truth and facts lead us to the reality, not politics, not religious belief, etc. but Economic Equality, Economic Equality, and Economic Equality. No more no less. Let us think and act about this hot societal issue. TIME Magazine put it in an excellent way how income inequality is a threat for National (good example, Nigeria) and Global security, “Poverty and lack of Education have allowed Boko-Haram to recruit disenfranchised young muslims”. Narrowing income inequality and eradicating corruption are the two wicked, abominable. To up bring economic equality among Nations and people corruption should also be diminished. For instance, Nigeria’s new President seeks help from Obama on finding and returning the $150 billion dollars embezzled by Nigerian ex- treasury officials, according to Time Magazine July, 2015.

Work Cited
Peter G. Northouse. Introduction to leadership: concepts and practice. West Michigan University. SAGE Publications, Inc. Third edition. 2015.

John Campbell. Ralph Bunche Senior Fellow for Africa Policy Studies. Council on Foreign Relations (CFR). http://www.cfr.org. Web. May 06, 2015.

Nobel Media AB 2014. “Nelson Mandela-Facts”. Nobelprize.org. 05 May 2015.http://www.nobelprize.org/nobel_prizes/peace/laureates/1993/mandela-facts.

Todorov, Tzvetan. “Mandela’s Example”. Salmagundi.184 (2014): 5, 8,208. ProQuest. Web. 6 May 2015.

Penny Dale. BBC News Africa/World Politic, Addis Ababa. The man who taught Mandela to be a soldier. Web. May 06 2015.

International Monetary Fund: Research Department. Redistribution, Inequality, and Growth. Jonathan D. Ostry, Andrew Berg, Charalambos G. Tsangarides. http://www.imf.org. Web. May 06, 2015. 

ብሄራዊ መግባባት

ይድረስ ኢትዮጵያውያን! ይድረስ  ለገዢው ፓርቲ! ይድረስ  ለተቀዋሚ ፓርቲዎች በሙሉ!                                                                                    

            “ቤት በጥበብ ይሰራል፥ በማስተዋልም ይጸናል፥”     (ዮሴፍ ወርቁ ደግፌ)

ቤት በጥበብ እንጂ በጠብ እንደማይሰራ፥ በማስተዋል እንጂ በስሜታዊነት እንደማይጸና፥ መፅሀፍ ቅዱስ በመፅሀፈ ምሳሌ ምዕ.24 ቁ.3 ላይ ያስተምራል፤ … ‘ቤት በጥበብ ይሰራል’ በሚልበት ጊዜ ሰዎች በስምምነት በጋራ የሚመሰርቷቸውን ቤተሰባዊ፤ መንፈሳዊ፤ ሀገራዊና፥ የተለያዩ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ህብረቶችንና ተቋማትንም ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፤ … የጋራ ቤትን በጋራ ለመገንባት ራእይ ማውጣት፥ አላማን መንደፍ፥ ግቦችን መተለም የሚያስፈልግ ሲሆን፤ … በጋራ ስራው ወቅት በሰዎች መካከል የአመለካከት ልዩነት ሊፈጠር ይችላል፤ … የአመለካከት ልዩነቶች አላማንና ግብን የማያስቱ እስከሆነ ድረስ፥ በመቻቻልና በመደራደር መስራት/Compromising/ በመንፈሳዊው መረዳት ጥበብና ማስተዋል ሲሆን በአለም እውቀት ደግሞ ስልጡንነትና ዲሞክራሲዊ አሰራርን ያመለክታል። … በተቃራኒ ሀሳቦች ክርክርና ድርድር የዳበረ ውይይት … በሳል ውሳኔን በማመንጨት፤ … መተማመንን በማዳበር፤ … ህብረትን አንድነትን በማጠናከር፤ እንዲሁም አሰራርን በማሻሻል ይረዳል፤ … የአመለካከት ልዩነትን አቻችሎ መስራት ማህበራዊ/የአብሮነት ውዴታ ግዴታም ነው።

የባህርይ ጥናት ሳይኮሎጂስት/Behavior psychologist/ ካናዳዊ አልበርት ባንዱራ ባደረገው የማህበራዊ ባህርይ ጥናት/Social Behavior study/ ሰዎች ከሚያደረጉዋቸው 20 ውይይቶች 17ቱ (85%) የሚቃረኑ ሃሳብዎች (negatives communications) እንደሆኑ አረጋግጦአል። … ይህም የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሮአዊ ሰውኛ/Humanistic/ ነው ወደሚል መደምደሚያ የሚወስድ ሲሆን፤ … ከዚህ አንጻር ሰዎች በጋራ ጉዳያቸው/አጀንዳዎቻቸው/ ላይ እየተደራደሩ ከመኖር ውጭ ምንም የተሻለ ምርጫ የላቸውም፤ … ስለዚህም ራሳቸው ያወጡትን “Divided we Fail United we Stand” መርህ በመጣስ በጸብ  መበታተናቸው እራስን በራስ መቃረን ብቻ ሳይሆን ፋይዳ ቢስና በጋራ ያለውን ጥቅም የሚያሳጣ/ጉዳት/ ነው።

ከአለም ህዝብ ብዛት 10% በታች የሚሆኑት ምእራባውያን በጋራ እየተደራደሩ ባለመግባባትም ቢሆን ተገባብተው/agree to disagree/ ሁለንተናዊ አቅማቸውን በማሳደግ በኢኮኖሚው በፖለቲካውና በወታደራዊ የበላይ ሆነው አለምን ይመራሉ/ይቆጣጠራሉ/ … አፍሪካውያን ግን ዛሬም ድረስ ካልተግባባን መጨራረስ ያለብን ይመስል እንደ አይጥና ድመት እየተጠባበቀን በጦርነት እየተገዳደልን እንደ ቅርጫ ስጋ እየተከፋፈልንና እየተበታተንን አቅም በማጣት እንዳክራለን፤ … በተራ አለመግባባት ምክንያት በከፋ መቃቃር፥ በጸብ በቂምና በጥላቻ በመለያየት፥ ብዙ የተወጠነበትንና የተደከመበትን ቤተሰባዊ፥ መንፈሳዊ፥ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ህብረት ሀገራዊ አንድነትን በቀላሉ በማፍረስ፥ አንዱን አንዱን አጥፍቶ በሰላም ለመኖር ይችል ይመስል፤ አንዳችን አንዳችንን አጥፍተን በ”ሰላም” ለመኖር እንጥራለን፥ … በተለይ ይህ ችግር በኢትዮጵያውያን ላይ እጅግ ከፍቶ ይታያል፤ …ኢትዮጵያውያን እየተደራደርን ተግባብተን መስራት በፍጹም የሚያቅተን /0% tolerance/ ባህርይ ከየት የመጣ ይሆን? … የአመለካከት ልዩነቶችን በአፍራሽነት በመመልከት፤ በጋራ አጀንዳ ላይ ለድርድር እንቢተኛ መሆን ጸረ-ስልጣኔ፤ ኢ-ዲሞክራሲያዊነትና እንዲሁም አምባገነንነት ነው። … በራእይ በአላማና እንዲሁም በግብ አንድ ሆነው ሳለ … በሃሳብ ልዩነቶቻቸው ላይ በጋራ መደራደር እያቃታቸው ጥበብንና ማስተዋልን እየጎደላቸው በግትርነትና በስሜታዊነት በሽታዎች በየግዜው በመሰነጣጠቅ ከሚፈርሱትና ከሚበታተኑት የኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ህብረቶች መካከል …የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችን፤ … የገዢው ፓርቲ ኢሊቶችን፤ … የዳያስፖራ ጊዜያዊ ፖለቲካ ማህበራትን፥ … የዳያስፖራ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲዎችን … የዳያስፖራ የኢትዮጵያ ስፖርት ማህበራትን፥ እንዲሁም ደግሞ የኢትዮጵያውያን የክርስቲያን መንፈሳዊ ህብረቶች ሳይቀር ለአብነት ያህል መጥቀስ ይቻላል።

ኢትዮጵያውያን በቤተሰብም ሆነ በት/ቤት ውስጥ እድገታችን እንዲሁም ደግሞ የመንግስታቶቻችን የአገዛዝ ባህርይ በውይይትና በድርድርና በመቻቻል ሳይሆን፥ በገዢና-በተገዥነት … በበላይና-በበታችነት … ትእዛዝ-በመስጠት እና መመሪያ-በመቀበል … በአለቃና-በምንዝር በጌታና-በሎሌ አይነት ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ፤ … ስሜታችን እየተጨፈለቀ /Emotional Suppression/ ስለምናድግ፤ … አዋቂ /adult/ ከሆንን በኋላ ባለን ህይወት ውይይት ክርክርና ድርድር በማድረግ መስራት የሞት ያህል ይከብደናል። … በዚህም በልዩነትም ቢሆን “ባለመግባባት ተግባብተን” ከመስራት ይልቅ፤ የጋራ ጥቅማችን ላይ ከማተኮር ይልቅ “እኔነት” ላይ በማተኮር፤ በቅሬታና በኩርፊያ አንድነትን ረግጠን መውጣት/መበተን/ ይቀለናል። … በድርጅት/በተቋም/በፓርቲ/በመንፈሳዊ ህብረቶች ወዘተ ውስጥ ከሆንም የድርጅቱ/የማህበሩ ህገ-ደንብ /መተዳደሪያ ደንብ/By-law/ በማይፈቅደውና ጠቅላላ አባላት /ጉባኤ/ ሳያውቀው ሳያፀድቀው /አንዳንድ ጊዜም በአብላጫ ድምጽ ቢጸድቅም/ የተቃወመን ሁሉ ጠላት ስለሚመስለን፤ በአመለካከት የማይመስሉንን ሰዎች በጠላትነት ፈርጀን ወዲያውኑ ወደ ተከላካይነት ከዚያም አጥቂነት እንቀየራለን። … የእኛን ሀሳብ የሚጋሩ ጥቂት ደካማ ደጋፊዎች /Cliques/ ካገኘንም በብልጣብልጥነት እየተጥመለመልን አንጃ ለመፍጠር እንጥራላን እንጂ፤ ሞት ቢመጣ በይቅርታ ታርቀንና ተራርመን “አንድነት ሀይል ነው” ብለን እንደገና ህብረታችንን እንቀጥል አንልም። … በመሆኑም ብዙ የታቀደለትንና ለመገንባትም ዘመናት የፈጀንበትን ህብረት/ተቋም በአንዲት ጀንበር አፍርሰን ቁጭ እንላለን። … በጋራ ውይይት/ድርድር ችግሩን ለመፍታትም አንጥርም፤ … መታረቅንም ከሰይጣን በላይ በመፍራት እንሸሻለን፤ … ማንም የፈለገውን ቢል ግድ አይሰጠንም… ምክንያቱም ከራሳችን በስተቀር ማንንም አናምንም፤ አንሰማምም። … ከዚህ ከተጠናወተን ክፉ “ራስን ብቻ የመስማት” የባህርይ በሽታ ለመፈወስ በእውቀት በመልካም ባህርይ በሚያመዛዝን በጎ ህሊና እና ንጹህ አእምሮ /Uncorrupted Mind/ የታነጸ ነጻ ትውልድ እስኪነሳ ድረስ ጊዜ የሚፈጅብን ይመስለኛል።

ጆርጅ ፓትሰን የተባለ ሰው “If everyone thinking alike, then somebody is not thinking” “ሰው ሁሉ ተመሳሳይ ሀሳብ ቢኖረው ኖሮ፥ ሌላው ሰው ማሰብ አያስፈልገውም ነበር፥” ይላል … የአንድ ሰው ሀሳብ ለሰዎች ሁሉ በቂ ስለሚሆን ሌሎች ሰዎች ማሰብ አያስፈልጋቸውም ነበር እንደማለት፤ … ሰዎች ከአስተዳደግ ተጽእኖ፥ … ከመንፈሳዊ እምነት ተጽእኖ፥ … ከህይወት ልምድ ተጽእኖ፥ … ከትምህርት ዝግጅት ተጽእኖ … በትውልዶች መሀከል ወይም የዘመን/እድሜ ልዩነት የተነሳ (Generation gap) ወዘተ ተመሳሳይ አመለካከት ሊኖራቸው በፍፁም ስለማይችል፤ አመጻን ካልፈለጉ በስተቀር፤ በአንድ ፕላኔት ላይ ስለሚኖሩ የጋራም ሀላፊነት ስላለባቸው ማስተዋል በሞላበት የድርድር ጥበብ በጋራ በመስራት የጋራ ውሳኔ ላይ ከመድረስ ውጭ ሌላ አማራጭ የላቸውም።

የዚህ ፅሁፍ ተልእኮ የዜግነት ግዴታን መወጣት ሲሆን … አላማው ደግሞ፤ 1ኛ/ በዋና ዋና ብሄራዊ/ሀገራዊ/ አጀንዳዎቻችን ላይ የአንድን ፓርቲ ወይም ቡድን ፍላጎት ብቻ በማወደስ የተለየ አመለካከት ያላቸውን ወገኖች ደግሞ ማብጠልጠልና መግፋት ለማንኛችንም የማይበጅ ዘላቂ ስምምነት ላይ የማያደርሰን፤ ዘላቂ ብልጽግናና ሰላም የማያመጣልን መሆኑን ማስገንዘብ ነው፤ … 2ኛ/ የፖለቲካ አይዲዮሎጂያችን እምነቶቻችን መርሆቻችን የአመለካከት ልዩነቶቻችን እንደተጠበቁ ሆነው በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግን ከግል ከቡድናዊ/ፓርቲ አመለካከት ነፃ በሆነ እይታ በጋራ የምንመራባቸው ሀገራዊ ፖሊሲዎች በጋራ መቅረፅ እንደሚያስፈልገን ማስገንዘብ ነው። … 3ኛ/ የጋራ ብሄራዊ/ሀገራዊ/ ፖሊሲዎችን በጋራ ለመቅረፅ አክራሪነት/ፅንፈኛነት/በሁለት ጫፍ ያሉት ፖለቲካዊ አመለካከቶች ወደ ማእከላዊ አመለካከት (Centrism: Centre Left and Centre Right) መምጣት እንደሚገባቸው ማስገንዘብ ነው። … 4ኛ/ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሁሉም የጋራ ውሳኔ የሚሰጥበት ብሄራዊ የጋራ አጀንዳ ቢኖረን … በትንሽ በትልቁ የፖለቲካ ንትርካችን ይቀንሳል … የፖለቲከኞቻችን ጭቅጭቅና የስራ ውጥረት ይቀንሳል … የብልፅግና ጉዞ ዘመንም ወዘተ እንደሚያጥር ማስገንዘብ ነው፤ … 5ኛ/ ከሁሉም በላይ የጋራ ብሄራዊ አጀንዳዎችን/ብሄራዊ ፖሊሲዎችን/ ለመቅረፅ የሚያስፈልገን ብሄራዊ መግባባት ብቻ እንደሆነ ማስገንዘብ ነው። … በተጨማሪም 6ኛ/ የጋራ ብሄራዊ አጀንዳ ለመቅረፅ በፖለቲካ አይዶሎጂ ከማንም ጋር ያልወገኑ /ገለልተኛ ሰዎች/ … በሙስና ውስጥ የሌሉ ሰዎች … በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሰዎች፤ … ለሀገር ትንሽም ብትሆን አስተዋፆ በማድረግ የሚታወቁ ሰዎች ተውጣጥተው ከገዢውና ከተቀዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በጋራ እንዲቀርጹት በህዝበ-ውሳኔ እንዲወሰንም ማስገንዘብ ብቻ ነው።

               “ኢትዮጵያውያን በጋራ መብላት እንጂ በጋራ መስራት “

የአመለካከት ልዩነታችን የተለያዩ ሀሳቦችን በማመንጨት በጋራ ሀገራዊ ግንባታ ላይ የሚጫወተው ሚና ቀላል አይደለም። … ይሁንና ኢትዮጵያውያን በትንሹም ይሁን በትልቁ በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳዮቻችን ላይ ዘወትር በከፋ የአለመግባባት ልዩነት /ቅራኔ/ ውስጥ ስለምንገባ፥ በህብረት /በአንድነት/ ለመስራት ፈፅሞ አለመቻላችን … ከመጥፎ ሰብእና/ባህርይ ችግር/ ወደ መጥፎ ፖለቲካ ባህልነት እየተቀየረ መጥቶአል። … የኢትዮጵያ ህዝብ ለሺ አመታት የዘለቁ ታላላቅ ቀደምት ሀይማኖቶች ተካታይ እንደመሆኑ፤ … ከእኛ በላይ በጥሩ ስነ ምግባር የታነጸና ደግሞም ባለታሪክ ህዝብ በአለም ላይ የሚገኝ አይመስለንም፤ … ነገርግን እንደታሪካችን ጥንታዊነትና የቆየ ሀይማኖተኛነታችን ሳይሆን፤ … ትላንትና ነጻነታቸውን ካገኙ ሀገሮች ጋር ስንወዳደር እንኳን ያለማደጋችን ምስጢር የእኛን የባህርይ ችግር የሚያጋልጥ ነው። … ነጻነታቸውን ካገኙ 50 ሀምሳ አመት ያልሞላቸው ሀገሮች ከሞላ ጎደል በአጭር ጊዜያት ውስጥ ሰርተው ለውጥ ሲያመጡ፥ … እኛ ሺ አመታት ቀደምት ብንሆንም ተስማምተን በጋራ ለመስራት ባለመቻላችን ብቻ፥ … ዛሬ በአለም ላይ ከአንዲት አፍሪካዊት ሀገር በስተቀር የምንቀድመው ሀገር የለም … እርግጥ የውጭ ወራሪ ሀይልን በመመከት ጦርነት ውጤታማነታችን በአለም የታወቅን ለመሆናችን ምንም ጥርጥር የለውም። … ነገር ግን ወደ ውስጥ ፖለቲካዊ አሰተዳደር ጉዳይ ስንመጣ ዘላቂ ፖለቲካዊ ሰላም ማስፈንና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን ከማስፋፋት አንጻር በማየት እንዲያውም እንደወደቀ ወይም ዋጋ ቢስ እርባና ቢስ መንግስት/Failed State/ የሚመለከቱን በርካታ የፖለቲካ ተንታኞችና አጥኚዎች ናቸው። … ዋና ሆኖ ሊጠቀስ የሚችለው “እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ” የባህርይ ችግር የግለኝነት ፖሊሲያችን ነው … ለዚህም መሪዎቻችን ለእግዚአብሄርም ለህዝብም ባስቸገረ ማንነት፥ ያለ ህዝብ ፍላጎት በሀይል ተጭነው በመግዛት፥ ሀገርን በፍትህ በመምራት ወደ ብልፅግና ለማምጣት ባለመቻል በስልጣን በመሻኮት እጅግ በከፋ የጥላቻና የቂም በቀል ኩሬ ውስጥ ተዘፍቀው እርስበርስ በመጠፋፋት ፖሊሲያቸው፥ አንደኛው በሌላኛው ላይ ስልጣኑን በሀይል ለመመስረት በሚያደርገው የጦርነት ትግል፥ ትውልዶች በጦርነት እሳት በከንቱ አለቁ፥ … የሀገሪትዋ ሀብትም ወደመ፥ … ከዚህ የተነሳ መልካም አስተዳድር በማጣት ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ሊኖር አልቻለም፤ ለዚህ ማስረጃ ሶስት ቀላል ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል።

                         1- ኢኮኖሚ

እስከዚህ ግሎባላይዜሽን ዘመን ድረስ በዶማና በጥንታዊው ማረሻ እያረስን/እየቆፈርን የሺ አመታት የጦርነት ታሪካችንን ለዘመናት ስንደልቅ … ነጻነታቸውን ካገኙ 50 (ሀምሳ) አመት ያልሞላቸው የአፍሪካ ሀገሮች ቢያንስ ከርሀብ ወጥተዋል። … እኛ ግን አሁንም ድረስ እንራባለን፤ … በFAO የ2013 መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ በየኣመቱ ባማካይ ከ16 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የምግብ እህል እርዳታ ጠባቂ ነው፤… ከህዝባችን 93% ያህል የሚሆነው ለመኖር የሚያስፈልጉትን ሶስት 3 መሰረታዊ ነገሮች፥ /በቂ ምግብ ልብስና መጠለያ-ቤት/ ሳይሟላለት በከፋ ድህነት ውስጥ የሚማቅቅ ለመሆኑ፤ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ባደረገው ጥልቅ ጥናት የኢትዮጵያን የድህነት ስፋት መጠን በየክልሉ በተለይም በገጠሩ እንደሚከተለው እንደሆነ ያስረዳል፤…”The Global Multidimensional Poverty Index (MPI), published by Oxford University, Ethiopia ranks the second poorest country in the world just ahead of Niger. The study is based on analysis of acute poverty in 108 developing countries around the world. Despite making progress at reducing the percentage of destitute people, Ethiopia is still home to more than 76 million poor people”.  “In rural Ethiopia 96.3% are poor. … Comparing the poverty rate by regions, Somali region has the highest poverty rate at 93% followed by Oromiya region 91.2% and Afar 90.9%. Amhara region has 90.1% poverty rate while Tigray has 85.4%”  … በ3ሺ አመታት ታሪክ ውስጥ በምግብ ራስን ያለመቻል ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የስልጣኔ መሰረት የሆነውን የቴክኖሎጂ ልማት ብንመለከት ደግሞ በአፍሪካ ሀገሮችና በኢትዮጵያ መካከል ለምሳሌ በኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት፥ … በኢንተርኔት አቅርቦት፥ … በስልክ አቅርቦት … በመኖርያ ቤት አቅርቦት እና … በንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ በርካታ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

                       2- ከፍተኛ ትምህርት

በርካታ መቶ አመታትን ያስቆጠሩት የቤተክህነት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለምሳሌ እንድ ዋሸራ ዩኒቨርሲቲ የመሳሰሉት እንዳሉ ሆኖ፤ … ኢትዮጵያ በዘመናዊ ት/ርት እጅግ ወደኋላ መቅረትዋን በተመለከተ ያጋጠመኝን አንድ እውነተኛ ታሪክ እዚህ ላይ ባካፍል የክርክሬን ጭብጥ ያጠናክራል፤ … አንድ የውጭ ሀገር ሰው “እ.ኤ. አ. 2000 አ.ም. ላይ ይመስለኛል “ዛሬ ዜና ሰማሁ … በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 50ኛ አመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በአል ተከበረ” … ይሄ ነገር/ዜና ስህተት ይመስለኛል ኢትዮጵያ የ3ሺ አመታት ታሪክ ያላት ሀገር እንዴት የዘመናዊ ት/ርት 50 አመት ብቻ…? …ምናልባት 500 (አምስት መቶ) ማለቱ ይሆን? … ዜና አንባቢው ተሳስቶ ይሆን?” የሚል ጥያቄ ይጥይቃል፤… ከመሀከላችን አንዱ ጓደኛችን ፈጠን ብሎ “ልክ ነው 50 አመት ብቻ ነው…እሱንም እድሜ ለንጉስ ሀይለስላሴ ቤተመንግስታቸው ‘ሲደብራቸው’ ከዛሬ ጀምሮ ዩኒቨርስቲ/ኮሌጅ አድርጉት ብለው ስለሰጡ ነው” ማለቱ ትዝ ይለኛል። … ይህ ቀልድ ባለመሆኑ ከዚህ እውነት ወዴት ልንደበቅ እንችላለን? … የኡጋንዳው ማካራሬ ዩኒቨርስቲ ከተመሰረተ 115 አመታት ያለፈው ሲሆን … የእኛው “አንጋፋ” አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ግን ገና 65 አመት አካባቢ ነው። … በዚህ መሰረት ትላንትና ነፃነቷን ካገኘችው ኡጋንዳ ጋር ስንወዳደር … ለ50 አመታት /3 ትውልድ ያህል/ ከከፍተኛ ት/ርት ወደሁዋላ እንድንቀር ተደርጓል … ከኡጋንዳ አንጻር እንኳን ስንወዳደር የመጀመሪያው ትውልድ ከ120 በፊት ኮሌጅ/ዩኒቨርስቲ መግባት የነበረበት ሲሆን … “አንጋፋው” አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በአሁኑ ሰአት 3ኛ ትውልድ ሳይሆን ቢያንስ 6ኛ ትውልድ በማስተማር ላይ መገኘት ነበረበት። ከ120… 150… አመታት በፊት ኮሌጅ/ዩኒቨርስቲ የገባ የመጀመሪያ ትውልድ ቢኖር ኖሮ የተሻለ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ይኖረን ነበር።

                          3- ፖለቲካ

የአጼዎቹ አገዛዝ/የፊውዶ ቡርዥዋ፤ የደርግ ወታደራዊ አገዛዝ/የኮሚኒስት ፖለቲካ ወዘተ እያልኩ በመዘብዘብ ጊዜ መፍጀቱን ትቼ፤ … እንደው ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህላችን ግሎባላይዜሽን ዘመን ላይ ደርሰን እንኳን “አባረህ በለው” የጦርነት ታሪክ ነው፤ … ይህም በፖለቲካዊ የስልጣን ሽኩቻ አዲስ ገቢው መንግስት በአሮጌው መንግስት መቃብር ላይ ቀድሞ የተሰራ መልካም ስራ ሳይቀር እያፈረሰ የራሱን አዲስ አገዛዝ ያለ ህዝብ ይሁንታ በሀይል የሚመሰርትበት … ዘላቂ ሰላም ብልፅግናና መልካም አስተዳደር/ዲሞክራሲ እንዲሰፍን በመከባበርና በመቻቻል ላይ የተመሰረተ የሰለጠነ ፖለቲካዊ ክርክር/ውድድር/ምርጫ ተድርጎ የፖለቲካ ስልጣን ርክክብ የማይደረግበት … ዛሬም እንደ ጥንቱ  “የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጅ የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጅ” የሚለውን የመጠፋፋት ዘፈን የምናቀነቅንበት ወዘተ በመሆኑ የፖለቲካ ባህላችን በሽተኛ ስለሆነ ፈውስ/መድሀኒት የሚያስፈልገው ነው። … ይህ ግን ህዝባችን በአለም የተደነቀበትን በአንድነት በሰላምና በፍቅር ተቻችሎ ተከባብሮ የሚኖርበትን የሀይማኖት ፅናት አይመለከትም።

                        ምኑን አወቅን?

ጥላቻ በሰላም በጋራ ሊያኖር የማያስችል መርዝ … ቂም ወደ ተለመደው እርስ በርስ ጦርነት የሚወስደን አቋራጭ መንገድ … በቀል የህይወት መጋዝ መሆኑን በግሎባላይዜሽን ዘመን ካልተረዳን መቼ ነው የምንረዳው? … መልካም መንፈስና አእምሮ ያለው ሰው ምንጊዜም ገለልተኛነትን በማራመድ ሰውን ሁሉ እኩል የሚያይ ነው። … ከወገናዊነት ነፃ በመሆን ሚዛናዊ አስተሳሰብን የምናራምደው የጋራ ችግራችንን በጋራ በሰላም የምንፈታበት ሁሉም እኩል የሚያሸንፈበት /Win-Win Resolution/ መንገድ ስለሆነ ብቻ ነው። … መቻቻልን ዛሬ ካልሰራን መቼ ነው የምንሰራው? የምንገኝበት ዘመንም ይህን ግድ እንደሚለን እንዴት አልተገነዘብንም? … ይህንን ለማወቅም ሆነ መቻቻልን እውን ለማድረግ የአስተሳሰብ ልቀት የሚያስፈልግ ሲሆን … በአስተሳስብ ለመላቅ ደግሞ ‘MA’ ‘PhD’ ዲግሪ መጫን አያስፈልግም። ጥላቻን ክፋትን ምቀኝነትን ስግብግብነትንና ምዝበራን ቂም-በቀልን ወዘተ በማስወገድ በምትካቸው ንፁህ አዕምሮና ንፁህ ልብን ለመፍጠር አመለካከትን/አስተሳሰብን ማስተካከል ብቻ ነው።

እንደ ጥቂቶች ሃሳብ ኦሮሚያንና ኦጋዴንን እንደ ኤርትራ የማስገንጠል ምኞት ሳይሆን ኤርትራም፤ ኢትዮጵያም/ኦሮሚያም ሱማሌም፤ ጅቡቲም፤ ሱዳንም፤ ደቡብ ሱዳንም፤ ኬንያም፤ ኡጋንዳም፤ ባጠቃላይ የምስራቅ አፍሪካ ህዝብ በሙሉ የጋራ ችግርን በጋራ ለመፍታት፤ … ከድርቅ ከርሀብና ከጦርነት ነፃ ለማውጣት…ጠንካራ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር በመመስረት ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር ለዘላቂ የጋራ ጥቅም ፖለቲካዊ ውህደት በማምጣት በሰላም እና በብልጽግና የምንኖርበት፤ ጠንካራ ኢኮኖሚና ዘላቂ ሰላም የሰፈነባትን የምስራቅ አፍሪካን ሀገራት ለመመስረት መስራት፤ ካላወቅን ምኑን አወቅን? … ዛሬም እንደትላንቱ ህዝቦችን የመከፋፍል ስራ ሁላችንንም ይዞ የሚጠፋ እብደት መሆኑን ካላወቅን ምኑን አወቅን? … ባጠቃላይ ከአስተሳሰብ ድህነት ነፃ ካልወጣን ከኢኮኖሚም ሆነ ከፖለቲካ ድህነት ነፃ ልንወጣ እንደማንችል ካላወቅን ምኑን አወቅን? … ለጋራ ጥቅምም አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የጋራ ትብብር ማድረግ ካላወቅን ምኑን አወቅን? … ስለሆነም አዲሱ ትውልድ ከመንግስቱ ሀይለማርያም፥ ከኢሳያስ አፈወርቂና ከመሳሰሉት “እኔ” ባይ /self centered/ ትውልዶች “ከራስ በላይ እግር” አስተሳሰብ ነፃ ካልወጣ ምኑን ነጻ ወጣ? … ዋናና ትልቁ ነፃ መውጣት ከጥላቻና “እኔ የምለው ብቻ ትክክል ነው” ጀብደኛ ግትርና ግለኛ አስተሳሰብ ነፃ መውጣት ነው።

የመንፈስና የአእምሮ ልእልናን ገና አልተቀዳጀንም፤ ሌሎች ወገኖች የሚሉትን ባለመቀበል እኛ የምንለው ብቻ እንዲሆን የስሜታችን/የፍላጎታችን/ ባሪያዎችነን፤ … ስለሆነም ሰዎችን ነፃ ልናወጣ ቀርቶ ራሳችንም ነፃ ሳንወጣ ዘመናችንን ጨርሰን ወደ መቃብር እንወርዳለን … የመሬት ሆድ ውስጥ ገብተን ለዘላለም ፀጥ ከማለታችን በፊት ‘ሰውን መውደድ’ ‘ሰላምን መውደድ’ እንደሆነ በቅድሚያ እንወቅ። … ፍቅርንና ሰላምን ካልሰበክን በስተቀር እንደለመድነው በማይጠቅም ደምሳሽ እርስበርስ ጦርነት መጠፋፋት ብቻ ነው ዛሬም ያለን አማራጭ። … የቱን እንምረጥ ሰላምን ፍቅርን ወይስ ጥላቻና ቂም-በቀል የሚወልደውን እርስበርስ መጠፋፋት? ምርጫው የእኛና የእኛ ብቻ ነው፤ … ህዝቦችን አንዱን ብሄር ካንዱ፥ ኦሮሞን ከኣማራ፥ ትግሬንም አማራንም ከኤርትራ፥ ወዘተ እርስ በርስ ማጣላት ከንቱነት ስለሆነ በቅን አስተሳሰብ፥ በሰላም ወዳድነት፥ በንጹህ ኣእምሮ /uncorrupted Mind/ እንጂ በጉልበት/በጦርነት ማሰባችን ያብቃ። … ብናስተውል መልካም ይሆናል ኣውቀንም ይሁን ሳናውቅ በሰራነው በደል ቀርቶ በተናገርንበት ነገር ሁሉ የምንጠየቅበት ዘመን ነው። … ሰው ከትግሬም፥ ከኤርትራም፥ ከአማራም፥ ከኦሮሞም ከየትም ይወለድ/ይምጣ በማንነቱ መከበር አለበት። … “ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራም ለመጪው ይታሰብበታል እንጂ” እንዲሉ መጭውን ዘመን እያሰብን እርስ በርስ መልካም እናድርግ … ሁሉም ህዝቦች በሰላምና በብልጽግና ይኖሩ ዘንድ በህብረት እንስራ … አንዱ አንዱን አጥፍቶ ብቻውን መልማት በግሎባላይዜሽን ዘመን አይቻለውምና።               

                      ግንዛቤ እጦትና ጭፍን ተቃውሞ

ባለመግባባት የተነሳ ያለን ግንዛቤ የተዛባ በመሆኑ በማንኛውም ጉዳይ የምንቃረን ሲሆን እንደ ምሳሌ አባይን መውሰድ ይቻላል … አባይ አለም አቀፍ ወንዝ በመሆኑ ከተፋሰሱ ሀገራት በተጨማሪ በመካከለኛው ምስራቅ አረብ-እስራኤል ላይም ጂኦ-ፖለቲካዊ ተፅእኖ ያለው መሆኑን እየተረዳን በአለመረዳት እንቃረናለን። … አባይ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ኩራት የሚሆነው ስንጠቀምበት እንጂ አሊያ ኩራትነቱ ለግብጽ መሆኑን እየተረዳን በአለመረዳት እንቃረናለን። … አባይ አንድነታችንን የሚያስጠብቀው በጋራ ለጋራ ልማት ሲውል እንጂ ፖለቲካዊ በዘፈን አለመሆኑን ዛሬም ድረስ እየተረዳን በአለመረዳት እንቃረናለን።  … በአለመግባባታችን ምክንያት ምናልባት አባይ ሊገነባ ባይችል ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ችግራችንን እየተባባሰ እንጂ እየተሻሻለ የሚመጣ አለመሆኑን በአለመረዳት እንቃረናለን … ከሰሀራ በታች የአባይ ተፋሰስ ሀገራት በአለም ላይ እጅግ ድሀ ሲሆኑ … የአባይ ግድብ መሰረታዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በማምጣት የጋራ ልማትን የሚያፋጥን መሆኑን በአለመረዳት እንቃወማለን፤ … በአለም ላይ በፖለቲካ አለመረጋጋቱ የሚታወቀውን የአፍሪካ ቀንድ የአባይ ግድብ ዘላቂ ልማትና የንግድ ትስስር እንዲኖር በማድረግ የፖለቲካ መረጋጋት ሊያመጣ የሚችል መሆኑን በአለመረዳታችን እንቃወማለን።

                            የኑሮ ልዩነትና ፍትሀዊ የሀብት ስርጭት ችግር

ዛሬ ዛሬ አብረን ለመቁረስ እንኳን እንዳንችል የሰማይና የምድር ያህል ያራራቀን የገቢ ልዩነታችን ያስፈራናል … እንደቀድሞው በጋራ የማንገባበዝበት ምክንያት የኑሮ ውድነት ችግር ብቻ ሳይሆን የጥቂቶቻችን የሀብት ምንጩ ስለ”ማይታወቅ” ስለምናፍርበት ይሆን?። … የደሀና የሀብታም የኑሮ ልዩነት እጅግ የመስፋት ችግር /Economic Inequality/ በተመለከተ በጥቂት ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ/በአሜሪካ ስታንዳርድ ደረጃ በላይ በሆነ ኑሮ ውስጥ እንዲኖሩ ሲደረግ ከ96% በላይ ህዝብ ደግሞ የእርዛት ኑሮ መኖር ሀገራዊ መሰረታዊ ችግራችን ነው። … በዚያች ደሀ ሀገር ውስጥ የገቢ ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል መራቅ ችግርና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ስርጭት ችግር መኖር “መንግስተ ሰማይም ሲኦልም እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው” የሚሉን ደግሞ የውጭ ታዛቢዎች/ነጮች ናቸው። … ከዚሁ ጋር ተያይዞም በዋናነት የምግብ ዋስትና ችግር … የመልካም አስተዳደር ችግር … የፍትህ መዛባት ችግር/ … የሙስና ችግር/ባቋራጭ ሀብታም የመሆን ችግር … የስራ አጥነት ችግር … የተነሳ ህዝቡ ኑሮና ብልሀቱ እየተጣረሰበት በሰላም ሊኖር አይቻለውም፤ ስለሆነም መንግስት የደሀና የሀብታም የኑሮ ልዩነት ችግር /Income gap/ እና ፍትሀዊ የሀብት ስርጭት ችግር መፍታት የህልውና ጉዳይ ስለሆነ Tax & Economic Policy የመሳሰሉትን ማሻሻያ ማድረግ እንዳለበት ማንም ሊመክረው አይገባም።                        

                    ድህነት አለመግባባትን ያባብሳል

አለመግባባታችንን ከሚያባብሱ ነገሮች ውስጥ ድህነት ዋነኛው ነው።  … ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የሚርመሰመስባት ሀገር ስትሆን … በአሁኑ ሰአት የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦትዋ ግን፤ ከ2ሺ ሜጋ ዋት የማይበልጥ በመሆኑ … በዚህና በሌሎች የድህነት መስፈርቶችም ጭምር የድህነታችን ልክ ሲለካ … በአለም ላይ ከመጨረሻ 2ኛው ደሃ ሀገር እንደሆንን በቅርቡ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በ2014/2015 ባደረገው ጥልቅና ሰፊ የጥናት መረጃ ጠቁሞኣል /Global Multidimensional Poverty Index (GMPI) http://www.ophi.org.uk/ … በጥናቱ መሰረት 93% የኢትዮጵያ ህዝብ (በገጠር 96%) በከፋ ድህነት/Chronic Poverty/ ውስጥ የሚኖር መሆኑ ተረጋግጧል። … ሀገሪቱ ግን በቂ የተፈጥሮ ሀብት እያላት ከርሀብ ያለመውጣትዋ ችግር አያዎ/paradox/ ነው። … አባይ አንዱ ምሳሌ ነው … የኤሌክትሪክ ሀይል ለአፍሪካና ለመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ኤክስፖርት በማድረግ በቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ የማግኘት ከፍተኛ አቅም አላት። … አባይ ቢገደብና 6ሺ ሜጋዋት በማመንጨት የኤሌክትሪክ ሀይል አቅማችንን ወደ 8ሺ ሜጋዋት ከፍ ቢል … 1ኛ/ የሀገር ውስጥ ሀይል ፍላጎትን በእጅጉ ይሻሻላል (ቢያንስ ቢያንስ መብራት ተቋረጠብን ማለት ይቀራል) … 2ኛ/ የውጭ ኢንቨትመንት እንዲስፋፋ የኤልክትሪክ ሀይል አቅርቦት በእጅጉ ወሳኝ በመሆኑ … የውጭ ኢንቨስተር ከፖለቲካ መረጋጋት ቀጥሎ የሚጠይቀው “ምን ያህል የኤሌክትሪክ ሀይል ኣቅርቦት አላችሁ በመሆኑ?” … 3ኛ/ የኤሌክትሪክ ሀይል ኤክስፖርት የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማግኘት ለተጨማሪ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት/ግንባታና ባፋጣኝ ከድህነት ለመውጣት አስተዋፆው እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ነው።

ሌላው የድህነታችን ትልቁ መግለጫ የገቢ ንግድ /Import/ እና የወጭ ንግዳችን /Export/ ነው። … የኢትዮጵያ መንግስት የብሄራዊ ባንክ በ2012 /2013 ባወጣው የሀገሪቱ የገቢና የውጪ ንግድ ስታትስቲክስ መሰረት፤ የሀገራችን የገቢና የወጭ ንግድ ሬሽዮ (ንጽጽር) በአለም ላይ ካሉት የመጨረሻ ደካማ ሀገሮች ተርታ ነው። … ይኸውም ወደ ውጪ የምንልካቸው ምርቶች ከውጭ ከምናስገባቸው እቃዎች ጋር በዋጋ ሲነፃፀር Export-Import ratio 1 እጅ ለ3 እጅ ነው። … በአሀዝ ሲታይ በ2012/2013 ሀገሪቱ ወደ ውጭ የላከችው ምርቶች ዋጋ በድምሩ ወደ 3.5 (ሶስት ተኩል) ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሲሆን፤ ከውጭ ያስመጣቻቸው እቃዎች ዋጋ ደግሞ በድምሩ ወደ 10 (አስር) ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል።… በዚህ ስሌት መሰረት ከውጭ የምናስመጣቸውን እቃዎች ያለ ንግድ ጉድለት /Trade Deficit/ ለማከናወን ወደ ውጭ የምንልካቸውን እቃዎች በመጠን በጥራትና በሽያጭ ዋጋ ከሶስት (3) እጥፍ በላይ ማደግ አለበት።

                  ዘር ወይስ ኢትዮጵያዊነት የቱ ይቀድማል?

አንዳንድ ሰዎች የሚያሳስባቸው ህወሀት/ኢህአዴግ እንዴት በሀይል ስልጣን ሊለቅ እንደሚችል ሲሆን፥ ኢህአዴግ በሀይል ስልጣን ቢለቅ ተያይዞ የሚመጣው ሀገራዊና አህጉራዊ (የአፍሪካ ቀንድ) ከፍተኛ ቀውስና መዘዞቹ ግን ይበልጥ ያሳስባል። … ይህም የተለመደው የኢትዮጵያ መንግስታት ስልጣን በሀይል የመገለባበጥ ባህል … አዲስ ገቢው መንግስት በአሮጌው መንግስት መቃብር ላይ የቀድሞውን እያፈረሰ የራሱን አገዛዝ በሀይል በሚመሰርትበት ወቅት… በህዝብ ላይ የሚደርሰው ጥፋት … አመፅ … ግድያ …ከስፍራ ከስራና ከንብረት መፈናቀል እጅግ የከፋ ነው፥ … ይበልጥ ደግሞ በዚህ ዘመን ኢህአዴግ በሀይል እንዲወድቅ ቢደረግ ከሀይለስላሴና ከደርግ መውደቅ የበለጠ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውሶችን የሚያመጣ፥ በቀላሉ ሊታረቁ በማይችሉ ብሄራዊና ፖለቲካዊ ቅራኔዎች የታጨቁበት፥ ማህበረሰባዊ ጉዳቱም የትየለሌ ነው… እንደ ምሳሌ ህወሀትንና (TPLF) ኦነግን (OLF) የብሄር ፖለቲካ ድርጅቶች ብንውስድ፥ ለ 40 አመት (ሁለት ትውልዶች) ያደረጉት ብሄር-ተኮር ፖለቲካዊ ትግል፥ የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ፌዴራላዊት ኢትዮጵያን ፈጥሮአል ብቻ ሳይሆን፥ TPLF/EPRDF መንግስት ሆኖ ሀገር ሲመራ ሩብ ምእተ አመት (ከአንድ ትውልድ በላይ) ሞላው፥ … ከዚህ የተነሳ በመላው ኢትዮጵያ ለማለት ይቻላል የብሄር ነፃ አውጭ ድርጅት የሌለበት ወይም ቢያንስ የብሄር ፖለቲካ ፓርቲ የሌለበት አካባቢ የለም። … የብሄር ፖለቲካ አደረጃጀት የህወሀት እና የኦህዴድ ኢሊቶች ፍላጎት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን … 1/ ገዢው ፓርቲ የ‘ብሄር ፖለቲካ አደረጃጀት’ን የትግል ውጤት እንደሆነ ማመኑ … 2/የብሄር ፖለቲካ አደረጃጀት ከአዲስ አበባና ከአማራ ህዝብ በስተቀር የአብዛኛው ህዝብ ፍላጎትም እየሆነ መምጣት ዋና ዋና ናቸው። … ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁልግዜ የሚነሳውና የሚያጨቃጭቀው ዘር/ብሄርና ኢትዮጵያዊነት እየተጣረሱ የመምጣታቸው ጉዳይ ነው፤… አክቲቪስት ታማኝ በየነ ኢህአዴግ አዲስ አበባ እንደገባ በአድዋ ድል ክብረ በአል ላይ በአብዮት አደባባይ እንደረደርው “ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው” አይነት ግጥምና … ወይም ደግሞ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያምና … በቅርቡም ደግሞ ዶ/ር ያእቆብ ሀ/ማርያም እንደተናገሩት “ለኢትዮጵያዊነት ሲባል ዘራችንን እንካድ” አይነት አባባል፥ … ከቀድሞዎቹ አምባ-ገነን መንግስታት አንድ ሀገር … አንድ ባህል … አንድ ቋንቋ በኢትዮጵያዊነት ስም የብሄረሰቦችን ማንነት የሚጨፈልቅ/የሚያስክድ ማእከላዊ መንግስት የፖለቲካ አደረጃጀት /Central Government/ ብረትን ከብረት ጋር በሙጫ ለማጣበቅ የመሞከር ያህል ጥረት ከመሆን የሚያልፍ አይመስልም። አንዱ ዋና ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ዘር ባለመሆኑ ነው።

ለመሆኑ ጥናት ቢደረግ ምን ያህል ፐርሰንቱ ዘሩን/ብሄሩን ወይስ ኢትዮጵያዊነትን ያስቀድማል? … ዘሬ ‘ኦሮሞ’ ‘ትግሬ’ ‘ሲዳማ’ ወዘተ ሳይሆን “ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው” የሚል ይመስላችሁዋል? … አሜሪካ ለሚኖሩ ለተለያዩ 9 የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች አባላት ላቀረብኩላቸው “ዘር/ብሄር ወይስ ኢትዮጵያዊነት?” የቱ ይቀድማል? ጥያቄ … አዲስ አበባ ተወልዶ ካደገው ከአንድ ሰው… ከአማራ ክልል ከመጣ ሌላ አንድ ሰውና …እንዲሁም ጥያቄውን ለመመለስ ካልፈለገው አንድ ሰው በስተቀር የተቀሩት 6ቱ ሰዎች ‘ኢትዮጵያዊነት’ን ከብሄር/ዘራቸውን በፊት ለማስቀድም እንደሚቸገሩ (እንደማይችሉ) አረጋግጠዋል።  ኢትዮጵያዊነታቸውን ከማንነታቸው መከበር ጋር ነው የሚቀበሉት ማለት ነው። በዚህች ቀላል ዳሰሳዊ ጠቋሚ ናሙና መሰረት 66% ያህሉ ‘ዘሩን የማያስቀድም ኢትዮጵያዊነትን’ እንደማይቀበል ከገለጸ፤ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ አደረጃጀት የማይሰራው ‘በአዲስ አበባና በአማራ’ ክልል ብቻ ይመስላል…/የአማራ ክልል የብሄር አደረጃጀትን እንደማይቀበል እንደአለ ሆኖ ኢህአዴግ ባደረገው ጥናት 97% የአዲስ አበባ ህዝብ በዘር/ብሄር ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አደረጃጀት እንደማይቀበል በቅርቡ ኢህአዴግን የከዳው ሚ/ር ደኤታ ኤርምያስ በመጽሀፉ ነግሮናል/ … የአማራና የአዲስ አበባ ህዝብ ደግሞ ከሀገሪትዋ ህዝብ 1/3ኛ ወይም ከ30% በላይ አይወክልም። … እይታዬን ለማጠናከር አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ በቅርቡ በሚድያ ላይ “Oromo First” ያለውንና (አቶ መለስ ዜናዊም “ሰው በመጀመሪያ ኦሮሞ፤ አማራ፤ ትግሬ፤… ነው፤” ሲሉ ተሰምተዋል)… ከአመታት በፊት ደግሞ አንድ የኦነግ ወይም የኦህዴድ የሆነ ካድሬ  “ኦሮሞነቴን የማታረጋግጥ ኢትዮጵያ ሺ ቦታ ትበጣጠስ ” በማለት በሀገር ውስጥ ጋዜጣ ላይ ያስነበበውንም ያስታውሱአል። … ስለሆነም በብሄሮች መብት መከበር/Group Right/ ስም የግለሰብ መብትም/Individual Right/ እንዳይጨፈለቅ፤  ‘ሁለቱም መብቶች መከበር አለባቸው’ ለሁሉም መልስ ይሆናል። … ባጠቃላይ እይታ 1ኛ/ የኢህአዴግ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ አደረጃጀት ስር የሰደደ ስለሆነ፥ 2ኛ/ ከኢትዮጵያ ህዝብ/ብሄሮች አብላጫው ብሄሩን ያስቀደመ ኢትዮጵያዊነትን የሚፈልግ ከሆነ፥ 3ኛ/ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ አደረጃጀት የኢትዮጵያን አንድነት የሚጠናክር እንጂ የማይናጋ እስከሆነ ድረስ፥ 4ኛ/ በምርጫ ሳይሆን በጠመንጃ አፍሙዝ በሀይል/በጉልበት እርስበርስ በመጨራረስ ሀገር በማውደም የሚደረገው የፖለቲካ ስልጣን የመገለባበጥ ከንቱና አውዳሚ የፖለቲካ ባህል ከዚህ በኋላ እንዳይኖር ከመፈለግ ከፍተኛ ጥረት አንጻር፤ 5ኛ/ ፈር ለመያዝ በመከራ ዳር ዳር የሚለውን ኢኮኖሚ ከ50% በላይ እና እንዲሁም ወታደራዊውን ክንፍ ሙሉ በሙሉ ኢህአዴግ መንግስትም የፖለቲካ ፓርቲም ሆኖ የሚቆጣጠረው ስለሆነ፥ ብሄራዊ መግባባትን በመፍጠር በጋራ መስራት እንጂ፥ ሀይል የስልጣን መያዣ አማራጭ ቢሆን ሀገራዊ ምስቅልቅሉ ከቀድሞዎቹ መንግስታት እጅግ የሚከፋ እንጂ የተሻለ ፖለቲካ በቀላሉ የሚመጣ ስለማይመስል፥ በእኔ የግል እይታ እንዲያውም “EPRDF is too big to Fail” ለማለት እደፍራለሁ። … ነገር ግን “ኢህአዴግ too big too fail” ስለተባለም እንዳይታበይ ያስፈልጋል፥…ምክንያቱም ዋሽቶ የማያውቀው ዘላለማዊና ህያው መፅሀፍ ቅዱስ “ትእቢት ውድቀትን ትቀድማለች” ይላልና፤ ይህም ትእቢት ለሰው ልጅ ጊዜያዊ “መፈሪያ/መከበሪያ” ብትመስልም መውደቂያ ያውም በውርደት እንደሆነች በመገንዘብ ከሁሉም ጋር ተከባብሮ እና ተባብሮ በግልጽነትና በተጠያቂነት በጋራ መስራት እውቀት ጥበብና ደግሞም ትልቅነት ነው።

                 “እንደ እባብ ብልህ እንደ እርግብ የዋህ”

10,200 ኪሎ ሜትር ያህል በመጓዝ በአለም ላይ በርዝመቱ 1ኛ የሆነውን ታላቁን የአባይን ወንዝ መሰረት አድርጎ የተገነባው የግብፅ ህይወት የአስዋን ግድብ ለግብጽ መጠነ ሰፊ ጥቅም መስጠት ከጀመረ ግማሽ ምእተ አመት /50 አመት/ ሲያልፈው … ኢትዮጵያ በተባለችው ምድር ላይ የሚኖረውና የአባይ ምንጭ 86% ያህል መነሻ የሆነው ምስኪን ህዝብ ግን የ2ሺ አመታት መሰረተ እምነቱ እንደሚናገረው “እንደ እባብ ብልህ እንደ እርግብ የዋህ ሁን” ሆኖ ያልተገኘ ምንዱባን ህዝብ ነው። … ርግብነቱ (?) አለን ብንል እንኳን ብልህነቱ የት አለ? … ፈጣሪ የሰጠውን የተፈጥሮ በረከቶች በመጠቀም ከርሃብና ከእርዛት ሳይወጣ ለብዙ ሺ አመታት በድህነትና በጦርነት አዙሪት ውስጥ ሲዋትት ይገኛልና። … ይበልጥ ደግሞ በግሎባላይዜሽን ዘመን ላይ በጋራ ለመስራት የጋራ ተነሳሽነት ችግር መታየቱ እጅግ አስገራሚ ነው። … በሺ ኣመታት ረጅም ታሪክዋ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው መሪዎች ህዝብ የስልጣናቸው ምንጭ ስላልሆነ ከራሳቸው አመለካከት በላይ ለሀገር አርቀው ማሰብ ያልቻሉ፤ … በስልጣን ሽኩቻ በመናቆር አንዱ በአንዱ መቃብር ላይ የራሱን መንግስት በሀይል የሚገነባበት፥ … የህዝብ አመራር ጥበብና ማስተዋል የሌላቸው ጀብደኞች፤ ግትሮች፤ ራስ ወዳድዎች፤ ባጠቃላይ አምባ-ገነንዎች በመሆናቸው የተነሳ በጦርነት የደቀቀች፤ ድንቁርና ርሀብና ድህነት የተንሰራፋባት፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ እርስበርሰ ስር የሰደደ ጥላቻ ክፋትና ቂም በቀል የተስፋፋባትን ሀገር እንጂ፤ ሌላ ምንም ውርስ አላስረከቡንም። … በመሆኑም በራሳችን ችግር ምክንያት፤ አባይንም ይሁን ሌሎች በረከቶቻችንን ለመጠቀም ባለመቻላችን፤ ለዘመናት በከንቱ በመባከን የተራቆተን ህዝብ ስለሆንን ሊታዘንልን እንኳን የማይገባን ነበር። … ሌላው አለም ስለ የሚበላ እህል ማሰብ ትቶ የላቀ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ግሎባላይዜሽን ዘመን ላይ እኛ በአለም ፊት የድርቅና የጦርነት ምሳሌ ርሀብተኛ/ተመፅዋች/ ስደተኞች ነን። … “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” እንዲሉ አባይንም ይሁን ሌሎች ተፈጥሮአዊ ሀብቶቻችንንና የሰው ሀይል ሀብታችንን ሳንጠቀምባቸው በድህነትና በጦርነት አዙሪት (Vicious Circle of Poverty & War) ለዘመናት ስንዳክር እዚህ ደርሰናል። … እህል ሆኖ ሊመግበን ባልቻለ ታሪክም በባዶ ሜዳ ላይ ስንፎክርና ስናቅራራ የበረከት ምንጮቻችን ለዘመናት በከንቱ ባከኑ፤ ወንዞቻችንም በከንቱ ወረዱ፤ ከዚህ አንፃር እርዛትን እንደ ብልፅግና፥ … ርሀብን እንደጥጋብ በመቁጠር፤ … ለዘመናት እያለቅን ከንቱነታችንን ለአለም ያረጋገጥን የመሆናችንን እንቆቅልሽ በእፍረትም፤ በድፍረትም በመናገር ለመፍታት መነሳታችን ዛሬ እንኳን ካልሆነ መቼ ሊሆን ነው?

            ኢህአዴግና ተቀዋሚ ፓርቲዎች        

1/ ተቀዋሚ ፓርቲዎች፦ ገዢውን ፓርቲ በዲሞክራሲ እጦት ምክንያት በመክሰስ አባይ እንዳይገደብ መከላከላችሁ ከባህርይ ይሁን ከፖለቲካ አመለካከት ችግር አልታወቀም፤ … ለመሆኑ ከዲሞክራሲ እጦት ችግር ተቃዋሚዎች ራሳችሁ ነፃ ናችሁን? … ከፖለቲካ ስልጣን በፊት አስቀድማችሁ ዲሞክራሲን በመሀከላችሁ ለማስፈን ችላችሁዋልን? … ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ስልጣን የሙጥኝ የሚልበት አንዱ ምክንያት፥ ስልጣን ቢለቅ የመኖር ዋስትና ከማጣት ስጋት ቢሆንስ? … የፖለቲካ ስልጣን ሳትይዙ መስማማትና ዲሞክራሲን በመሀከላችሁ ማስፈን ያልቻላችሁ፥ … ስልጣን ብትይዙ እንዴት ነው ተስማምታችሁ ሀገር በሰላም ለመምራት የምትችሉትና  ስልጣኑን በምርጫ ላስረከባችሁ ፓርቲ በሰላም የመኖርም ይሁን እንደገና የመወዳደር/የመመረጥ እድል የምትሰጡት? … አስተያየቴ ጥቅል ቢሆንም በተለይ በ1997 ምርጫ ጥቂት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች “በእኔነት”ግትርነትና እና አንዳንዶችም ለግል ጥቅም በማደር በራሳችሁ ላይ የፖለቲካ ሞት /political suicide/ ከማምጣት ባሻገር ፓርቲያችሁ እንዲበታተን ምክንያት ለመሆናችሁ የአደባባይ ምስጢር ነው፤ እንዲሁም የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስልጣን ለመረከብ “ ዝግጅት ህብረት አንድነት መግባባት የሌላችሁ … መከናወን ያልቻላችሁ ራስ ወዳዶች፤ ግትሮችና፤ ግለኞች … የግል ሰብእናን ማጉላት ከመውደድ የተነሳ እንደ ጣቃ በየጊዜው በመሰነጣጠቅ እንደልጆች “ጫወታ አለቀ ዳቦ ተቆረሰ”የምትበታተኑ … ‘ሰርቶ ማሳያ ‘ሳይሆን ‘አጥፍቶ ማሳያ’ መሆናችሁን አለምን የምታሽከረክረው ሁሉ በእጅዋ ሁሉ በደጅዋ አሜሪካ በአምባሳደርዋ Tibor Nagy በኩል ከተናገረችው የሚከተለውን ለታሪክ የሚጠቀስ ነው “… a serious opposition to exist, while the opposition will also have to be serious, instead of fractious, petty, selfish and generally irrelevant …”  … ለተቃዋሚዎች የሚቀርበው ሌላው ዋና መሰረታዊ ጥያቄ ደግሞ ኢህአዴግ እንደ ገዢ ፓርቲ ከሞላ ጎደል እየሰራ ያለውን ልማቶች የመቀበል ጥያቄ ነው፤ … ይህም ምንም እንኩዋን ኢህአዴግ የያንዳንዱን ሰው መሰረታዊ ህይወት (የኑሮ ደረጃ) የለወጠ (Qualitative Life Change ወይም በጥቅል አነጋገር Economic Development) ባያመጣም፤ … ለዘለቄታው ግን በያንዳንዱ ሰው ህይወት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንደ መንገድ፥ ት/ቤቶች፥ ባቡር ሀዲድ፥ የከተማ ልማትና/መኖሪያ ቤት፤ የአባይ ግድብ ግንባታ፤ ወዘተ ይህም Quantitative changes or Economic growth ሊባል የሚችል ስራዎችን እየሰራ መሆኑን መቀበል ብሄራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ ያስችላል ብላችሁ ስለምን አትቀበሉም? … ከጥላቻ ፖለቲካ ይልቅ ከነጥፋቱና ድካሙ ኢህአዴግን በይቅርታ በመቀበል በጋራ መስራት ካልቻላችሁ ሰላማዊ የፖለቲካ ስልጣንን ለመረከብ እንዴት ለማመቻቸት ትችላላችሁ? … ከሁሉ በላይ ደግሞ ተቃዋሚዎች አስቀድማችሁ እርስበርስ በመግባባት ዘላቂ ህብረትና አንድነት ለምን አትፈጥሩም? … የትም የማይደርሱ ከየሰፈር የማያልፉ የግል ስም የሚያስጠሩ 90 እና 100 የነበቀለ የነከበደ የነእከሌን ፓርቲን ከማቋቋም ይልቅ፤ ህዝባዊና ሀገራዊ ጠንካራ መሰረት ያላቸው ጥቂት ብሄራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በበህብረት መፍጠር ካልሰራችሁ በስተቀር፤ ለዝንተ አለም ኢህአዴግን ለመገዳደር ሳትችሉ ውጤት/ፍሬ ያለው ስራ ሳትሰሩ፤ ዘመናችሁን በጭቅጭቅ ጨርሳችሁ ጡረታ እንደምትወጡ ወይም ደግሞ ዘመን ደርሶም ይህችን አለም መሰናበትም መኖሩን እንዴት ትረሳላችሁ? … እውነት እውነት ለመናገር ካስፈለገ ይህ ነው የሚባል ፍሬ ያለው ፖለቲካዊ ስራ ሳይሰሩ ይህችን አለም የሚሰናበቱ ጉምቱና እድሜ-ጠገብ ፖለቲከኞቻችንን በሚቀጥለው 10 አመታት ውስጥ እንደምናጣ ስነግራችሁ በጥንቆላ ሳይሆን ዘመናችሁን በመቁጠር ብቻ ነው። … አሮጌዎቹን ፖለቲከኞቻችንን የሚተካው ትውልድ ግን ከነዚህ ግትርና ራስ ወዳድ “እኔ ያልኩት ብቻ ትክክል ነው” ባዮች ፖለቲከኞች ስህተቶች በመማር ለሰለጠነ የመቻቻል ፖለቲካዊ ድርድር /Compromising/ “እኛ ብቻ ትክክል ነን እነሱ ትክክል አይደሉም” ፖለቲካ ነጻ በመውጣት “ሁላችንም በጋራ የምንስማማበት ትክክል ነው” ወደሚል ፖለቲካዊ አሰራር በመምጣት መስራት አለበት።

2/ ገዢው ፓርቲ፦  ሩብ ምእተ አመት ያህል በስልጣን ላይ ቆይቶ ሳለ ዛሬም “ዲሞክራሲ የሚገነባው በሂደት ነው” ሲል ይህ አባባል ስልጣን ላይ የመቆየት ፍላጎትን እንጂ ለዲሞክራሲ ስረአት ግንባታ ቁርጠኛነትን እንዴት ያሳል ብሎ ያምናል?ተግባር ብዙ ይናገራልና … ኢህአዴግ “ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ያስፈልጋል” “የዲሞክራሲ ጥያቄ ከመብትም በላይ የህልውና ጥያቄ ነው” ብሎ ከመናገሩ አንጻርም ከ1997 ምርጫ በስተቀር’ለመድብለ ፓርቲ ስረአት ግንባታ /ዲሞክራሲ ግንባታ/ ቁርጠኛነት አሳይቶአልን? ከተቃዋሚዊች ጋር ለመደራደር ኢህአዴግ የምሁራን እጥረት አለብኝ ብሎ ይሰጋ ይሆን? በ1997 የምርጫ ፖለቲካዊ/ፖሊሲ/ ክርክርን እንዳየነው ከሆነ ‘አብዮታዊ ዲሞክራሲ’ የሚለውን ፅንሰ ሀሳብ ከጠ/ሚር መለስ ዜናዊ በስተቀር የትኛውም የመንግስት ባለስልጣን የገባው አይመሰልም፤ በፖለቲካ ክርክሩ ወቅት ከአንድ የኢህአዴግ ሰው በስተቀር የመንግስት ባለስልጣን በሙሉ ሲንተባተብ ነበር የታየው። ኢህአዴግ አሁን ያለበት ሁኔታ ምን ያህል ተስማምቶኛል ብሎ ያምናል? የኑሮ ውድነትና የተተኪው ትውልድ ስራ የማጣት ችግር ብቻ የህዝብ ብሶትን በማባባስ በሂደት መሰረት ያናጋል ብሎ አይሰጋም? … በአባይ ግንባታ የህዝብን ልብ ከማግኘት የሀይል አድቫንቴጅ ፈጽሞ የሚልቅ ዘላቂ ውጤት ያለው ብሄራዊ መግባባት በማድረግ የዲሞክራሲያ ግንባታ መስረት በመጣል በሙሉ ሀይል ሀገር መገንባት አይቻልም ብሎ ያምናል? አቶ በረከት ስምኦን በ’የሁለት ምርጫዎች ወግ’መፅሀፋቸው “የኢህአዴግ ጌታ ህዝብ ነው” ከማለታቸው አንፃር ኢህአዴግ የህዝብን ልጆች ከማሳደድ ፖለቲካ Exclusive Policy/politic ይልቅ በማሳተፍ Inclusive policy ለመስራት ጥረት ካላደረገ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምና ብልጥግና እንዴት ሊኖር ይችላል ብሎ ያምናል?… ስለሆነም ኢህአዴግ ለመቻቻልና ለመደራደር ፖለቲካ ልቡን አስፍቶ፤ ስልጣን በሀይል የመያዝ ታሪክ እንዲያበቃና ስልጣን ከድምጽ ኮሮጆ ይወጣ ዘንድ በጽናት ሰርቶ የዲሞክራሲን ስርአትን ማስፈን ካልቻለ በስተቀር፤ ካለፉት መንግስታት የሚሻልበትን ለማወቅ ያስቸግራል ብቻ ሳይሆን፤ ራሱ ኢህአዴግ “ዴሞክራሲ መብት ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው” በማለት ስለተናገረ ኢህአዴግ ለህልውናው መስጋት ያለበት መሆኑን ማንም ሊመክረው አይገባም።

ገዢው ፓርቲና ተቀዋሚ ፓርቲዎች … ከአባይ ግድብ ግንባታ በፊት “ዲሞክራሲ ይገንባ” “ከዲሞክራሲ በፊት ታላቁን ጠላት ድህነትን አስቀድመን እንዋጋ” … “ዲሞክራሲ እህል ከጠገብን በሁዋላ” መባባላቸው … በቡድናዊ ፓርቲ አጀንዳ በመወጠር … በእርስበርስ ጥላቻ ክፋትና ቂም በቀል በመገፋት … አንዱ ላንዱ እንቅፋት ከመሆን ይልቅ በታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ብሄራዊ መግባባት /National Consensus/ በመፍጠር በጋራ በመስራት ከፖለቲከኛነት ይበልጥ የህዝብ አጋርነታቸውን ማሳየት አለባቸው። yeihdieg… በቅርቡ ጠ/ሚር ሀ/ማርያም “ለጋራ ሀገራችን በጋራ እንወያይ የሚል ጥሪ ማድረግ እፈልጋለሁ” ላደረጉት ጥሪ ተቀዋሚ ፓርቲዎች በቂና መግባባት የሚያማጣ ምላሽ መስጠት አለባችው። … እጅግ አብዛኛው የኢህአዴግ አመራር የኢህአፓ ትውልድ) የፖለቲካ ዘመኑን ጨርሶ ጡረታ የሚወጣበት ጊዜ ላይ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ ባለው ዘመኑ የእድሜ ባለጸጋነትን ከታደለ ከአማካሪነት ያልዘለለ ስራ ነው የሚሰራው፤ በዚሁ መሰረት “እኔ የምለው ብቻ ትክክል ነው” ፖሊሲ ወይም ፖለቲካዊ አመለካከትን በመለወጥ መልካም መጻኢ እድል ፈጥሮ ማለፍ አለበት። … ባጠቃላይ ሀገሪትዋ ‘በEthnic based Federalism’ አደራጃጀትና ‘በCentral Government/non-federal-government ሁለት የፖለቲካ አመለካከት ተወጥራ መዝለቅ አያዋጣትምና መግባባት ላይ የሚያድረስ መፍትሄ ማበጀት ብልህነት ሲሆን ለዚህም ‘ብሄራዊ መግባባት’ ዋና ነው።

                    ዲሞክራሲ ወይስ ልማት የቱ ይቀድማል?

በቻይና አንድ አውራ ገዢ ፓርቲ ከግማሽ ምእተ አመት በላይ በመግዛት ላለፉት አስርት አመታት ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስመዝገብ ቢችልም … ‘ዲሞክራሲ ልማትን’ ‘ልማትም ዲሞክራሲ’ን ሳይቀድም እጅ ለእጅ ተያይዘው ሳይነጣጠሉ ሲጓዙ ውጤታማ ለመሆናቸው ማስረጃው በማንኛውም መስፈርት የቻይናንና-የአውሮፓን የሩሲያንና-የአሜሪካንን የእድገት ደረጃ በማወዳደር መልስ ማግኘት ይቻላል። … ኢህአዴግ በ‘አብዮታዊ ዲሞክራሲ ‘አይዲዮሎጂ የቻይናን የሚመስል’ ልማታዊ መንግስት’ ተከትሏል። … የMACRO ኢኮኖሚ ለውጥ /Quantitative changes or Economic growth/ በማምጣት ላይ ይገኛል … ነገር ግን መሰረታዊ የህዝብ ኑሮ እድገት/ለውጥ /Qualitative Life Change or Economic Development/ ባለመምጣቱ መንግስት በዚህ ረገድ ከፍተኛ ስጋት ሊገባውና የEconomic Policy ለውጥ በማድረግ መስራት አለበት። … በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በጠንካራ እጅ ሁሉንም ነገር እንደፈለገው የመቆጣጠር ጉዳይን በተመለከተ ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ የጋና ጉብኝታቸው ወቅት “Africa doesn’t need strong Man, but strong civic institutions” አፍሪካ “ጠንካራ መሪ” ሳይሆን ጠንካራ የህዝብ ተቋማት ነው የሚያስፈልጋት” ቢሉም … ጠ/ሚር ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በአሜሪካ ሀገር በCNBC ቴሌቪዝን ቻናል በሰጡት ኢንተርቪው ላይ “ኢትዮጵያ አሁንም ጠንካራ እጅ ያስፈልጋታል” /“Ethiopia still needs strong hand”/ ብለው መናገራቸው ኢህአዴግ ከፖለቲካውም ይሁን ከኢኮኖሚውም ውስጥ በቅርቡ እጁን የሚያወጣ አይመስልም … ነገርግን ኢህአዴግ “የዲሞክራሲ ጥያቄ ከመብትም በላይ የህልውና ጥያቄ ነው” በማለት መስጋቱ መልካም ቢሆንም ብሄራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ ተቀዋሚ ፓርቲዎችን  በተግባር በማሳተፍ  መስራት ካልቻለ አባባሉ ከአባባልነት አያልፍም ብቻ ሳይሆን ሄዶ ሄዶ ኢህአዴግን ዋጋ የሚያስከፍል ስለሆነ መታሰብ ያለበት አሁን ነው።   

                     ብሄራዊ መግባባት /National Consensus/                                  

በአለም ‘አንጋፋ የታሪክ ባለቤትነት’ ‘በሀይማኖት በስነ ምግባር በመልካም ሰብእና በመታነፅ’ ‘በሰው አክባሪነት’ ‘በእንግዳ ተቃባይነት’ ወዘተ ቅፅሎች ሁሉ እንዳሉ ናቸው ብንል … ይህ ማንነት ግን ተግባባተን በጋራ ለመስራት አላስቻለንም። … ባህርያችን በስራችን የሚገለጥ መሆኑን አላስተዋልንም … ባለመግባባት ችግር የተነሳ የአለመተማመን ክስረት ውስጥ የገባ እንደ እኛ አይነት ህዝብ በአለም ላይ ያለ አይመስልም … የምንከተለው ሀይማኖትም ፍቅር ቢሰብክም … ፍቅራችን ግን የግብዝነትና የለበጣ በመሆኑ፥ … በፍቅር መሸናነፍ ቀርቶ ተራ ሰውኛ መግባባት ላይ እንኳን ለመድረስ አልቻልንም … ባጠቃላይ የረዥም ዘመን ባለታሪክነት አብሮነትና ሀይማኖተኛነት በጋራ ጥቅማችን ላይ መስማማት የምንችልበትን አቅም ሊፈጥርልን አልቻለም … ስለሆነም “ኢትዮጵያውያን አብረው መብላት እንጂ አብረው መስራት አይችሉም” የሚሉት ስድባዊ አባባል እርግጥም እውነትነት አለው። … ነግ በእኔ ነውና የኢህአዴግ መንግስት በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ያለጠላትነት ስሜት ለደርግ ባለስልጣናት ምህረትና ይቅርታ ማድረጉ በእጅጉ የሚያስመሰግነው ስራ ነው። … በዚህ መልካም ጅምር በመበረታታት ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት 1ኛ/ ከ40 አመታት ወዲህ የሞት የአካልና የንብረት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ካሳ መክፈልና ይቅርታ መጠየቅ፡ … 2ኛ/ለፖለቲካ እስረኞች ምህረትና ይቅርታ ማድረግ፡ … 3ኛ/ገዢውና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአይዲዮሎጂ ቢለያዩም፥ ተመሳሳይ የሀገር እድገት አላማ ቢኖራቸውም… ነገርግን ብሄራዊ መግባባት ስለሌላቸው፥ ጦርነት ቀረሽ ፖለቲካዊ ጭቅጭቃቸው መረጋጋት እንዳይኖር ኢኮኖሚም በፍጥነት እንዳይስፋፋ ያደርጋል … ገዢውና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጋራ ብሄራዊ አጀንዳ ፖሊሲ ስለሌላቸው የማይፈታ በሚመስል ቅራኔ ውስጥ ለመግባታቸው ማረጋጋጫው ከሚሆኑት ውስጥ … ምሳሌ 1/ የባህር በር፥ … ጠ/ሚር መለስ “ወደብ ሸቀጥ ነው” በማለታቸው፥ ኢህአዴግ የባህር በር አጀንዳን የዘጋ ይመስላል፡፡ … ተቃዋሚዎች ደግሞ “ሀገሪትዋ የባህር በር የማግኘት ህጋዊ፥ ታሪካዊ፥ ፖለቲካዊና አለም አቀፋዊ መብት አላት” ይላሉ … ታዲያ ይሄን ተራራ የሚያህል የብሄራዊ ፖሊሲ ልዩነት ሳይፈታ /ብሄራዊ መግባባት ሳይኖር/ ኢህአዴግ እራሱን ለማጥፋት ነው በምርጫ መሸነፍም ቢሆን የፖለቲካ ስልጣንን ለተቃዋሚ ፓርቲ የሚያስረክበው? … ምሳሌ 2/ የመሬት ፖሊሲ፥ … “መሬት የግል ይሁን የመንግስት?” የሚለው ብሄራዊ ጥያቈ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በኢህአዴግ መካከል የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቅ ልዩነት ሳይፈታ ወይም ብሄራዊ መግባባት ሳይኖር ኢህአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፖለቲካዊ ድርድር እንዴት ሊያደርጉ ይችላሉ? … ስለሆነም ለነዚህና ለሌሎች ሀጋራዊ ጉዳዮች ሁሉም ፖለቲካዊ ፓርቲዎችና ህዝብም በሀገር ግንባታው ላይ በሙሉ ሀይል እንዲሳተፍ ለማድረግ … አስተማማኝ/ዘላቂ ሰላምለማምጣት ብሄራዊ መግባባት የግድ አስፈላጊ ነው።

                          አባይ ለብሄራዊ መግባቢያነት

የአባይ ግድብ ግንባታን መቃወም ግን ምን የአይነት የፖለቲካ ስልት ነው? … እንዲያውም የአባይ ግድብ ግንባታ የከረረውን የጥላቻ ፖለቲካችንን ውጥረትን ያረግባል። ስርነቀል የእድገት ለውጥ ለማምጣት የሀይል አቅርቦት በእጅጉ የሚያስፈልጋት ኢትዮጵያ በራሱ በመንግስት ስታትስቲክስ መሰረት አሁን ባለችበት የ2ሺ ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት፤ እንኳን የውጭ ኢንቨስተሮችን ለልማት ለመጋበዝ ቀርቶ … የሀገር ውስጥ ፍጆታን እንኳን ለሟሟላት ፈፅሞ አትችልም።  … ይህ በዚህ እንዳለ የአባይ ግድብ ግንባታ ለሀገሪትዋ ሁለገብ የልማት ስራዎች ዋና የሀይል ምንጭነት እጅግ መሰረታዊ ከመሆኑ በመለስ ለብሄራዊ ፖለቲካ መግባቢያነት ከሚረዱን ግብአቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን በቅንነት ያለመረዳት ችግር ያለ ይመስለኛል። … ምክንያቱም ይህንን የተረዳን ቢሆን ኖሮ ከቡድናዊ ፖለቲካዊ አመለካከታችን ውጭ በመሆን ግድቡን ማንም ይገንባው ባለን አቅም መረባረብ እንጂ ገዢውን ፓርቲን ከመጥላት ችግር ጋር ማያያዝ አልነበረብንም። … ስለሆነም አባይ ቢገደብ ለብሄራዊ መግባቢያነት በር ይከፍታል ብሎ ማሰብ ይበጃል። … በማስተዋልና በጥበብ መመላለስ ማለት አባይን ተቃዋሚ-ፓርቲ ገደበው ገዢው-ፓርቲ ገደበው የተሰራውን ስራ መቀበል /acknowledge/ በማድረግ በአባይ ግድብ ስራ መነሻነት በመከባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ፖለቲካዊ ባህል ሊጀመር ይችላል ብሎ ማሰብ ጤነማ ግንዛቤ ነው። … እውነትም አባይ ተገድቦ የኢትዮጵያ ህዝብም ተጠቅሞ፥ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ኢህአዴግም በፖለቲካዊ መቻቻል መልካም ግንኙነት ቢመሰርቱ  አባይ ለብሄራዊ መግባቢያነት ቢሆን ከትላቅ ድል በላይ ታላቅ ገድል ነው። … ስለሆነም አስተውለንና ተግባብተን በብሄራዊ ጉዳይ በጋራ ለመስራት ካልቻልን በስተቀር፥ አንድ የፖለቲካ ምሁር እንደጠቀሰው  (“If we are Political depressed, we will find it much harder to cope with political stalemates and our frustration lead us to wrong decision /action/” ) በፖለቲካዊ ድንዛዜ ውስጥ ገብተናል ማለት ነው፥ … ወይም ደግሞ ከጥንት የተጠናወተን የእርስበርስ ክፋት፥ ጥላቻና ቂም በቀል ዛሬም የግሎባላይዜሽን ዘመን ላይም ያልለቀቀን “እኔ የምለው ብቻ ትክክል ነው” /My way is the Highway/ በማለት ከህዝብ በላይ ራስወዳድና ግትሮችም ነን።

                      የኤምባሲዎቻችን ጉዳይ

አቶ መለስ ዜናዊ ከቀረጹት የውጭ ጉዳይ መርህ “ዘላቂ ጥቅም እንጂ ዘላቂ ወዳጅ የለም” በእኔ እምነት የተሻለ ፖሊሲ ይመስለኛል። … ነገርግን በውጭ ሀገራት ያሉትን የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ከህንጻዎቹ ማማር በስተቀር እጅግ ብዙዎቹ የኤምባሲው ሰራተኞች እንኳን በኢንተርናሽናል በቀበሌ ደረጃ መስራት የማይገባቸው ብቃት የሌላቸው ናቸው፤ … በተለይም ዶክመንት/ቪዛ በማስተናገድ ስራ ላይ ከተስተናጋጅ ጋር በየጊዜው በቀጠታ የሚገናኙት ፕሮቶኮል የማይጠብቁ፤ … ምንም አይነት ስልጠና ፈጽመው አይተው የሚያውቁ የማይመስሉ፤ … እንደ ዲፕሎማት ማየት፤ መናገርና መስራት የማይችሉ ሀይል/Energy/ ፍላጎት፤ ተነሳሽነት፤ ቅልጥፍና የሌላቸው የተዳከሙ፤ ባግባቡ በስነስርአት በትህትና ማስረዳት የማይችሉ፤ የመግባባት ክህሎት/communication skill/የሌላቸው፤ ወጭ ሀገር ሆነው በሀገር ቤት አስተሳሰብ /mentality/የሚኖሩ፤ ዲያስፖራውን ወደ ሀገር ቤት የሚስቡ ሳይሆን የሚያስበረግጉ፤ ወዳጅ ሳይሆን ጠላት እንዲሆን የሚያደርጉ፤ ደስታ የማይነብብባቸው ስራ ላይ ሆነው ፊታቸውን ኮሶ ያገሳት አሮጊት የሚያስምስሉ/የሚኮሳትሩ/ ወዘተ ናቸው፤ … ለጉዳይ ወደ ኤምባሲው ለሚመጣ ባለጉዳይ እንደ ዲፕሎማት “Good morning Sir/Madam, welcome to the Ethiopian Embassy, How can I help you today?” ባማርኛም ይሁን በእንግሊዘኛም በሚስብ ፈገግታ ለማለት የማይችሉ ዘጊዎች ናቸው፤… ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ቀርቶ ነጮችን በማግባባት ወደ ሀገር ቤት ሄደው በሀገር ቤት ገንዘብ እንዲያፈሱ ኢንቨስት እንዲያድርጉ ቀርቶ እንዲሸሽ የሚያደርግ አቀራረብ ያላቸው የደካሞች ስብስብ ነው… ይህ ብቻ አይደለም በአንድ ወቅት በማንነትዋ እላፊ የምትመካ አንዲት የኤምባሲው ሰራተኛና በአንድ ኢትዮጵያዊ ተስተናጋጅ መካከል የተነሳው ዱላ ቀረሽ ጭቅጭቅና ስድብ ኤምባሲ ሳይሆን ተራ መጠጥ ቤት ይመስል ስነበረ ብዙ ሰዎች ነጮች ሳይቀሩ ይህንን ውርደት ከማየት መቅረት ይሻላል እያሉ ሲመለሱ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ለመታዘብ ችሏል፤ … ስለዚህ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የብሄር ስብጥር ጠብቆ መመደብ እንዳለ ሆኖ 1/ ለዝቅተኛው የኤምባሲው የስራ መደብ ሳይቀር ቢያንስ የመጀመሪያው ዲግሪ ያለው/ያላት 2/ ሰዎችን ነጩንም ይሁን ዳያስፖራ/ኢትዮጵያዊውን ጎትተው ኢትዮጵያ ለማስገባት ጥረት የሚያደርጉ 3/ ትሁት፤ 4/ ቀልጣፋ፤ 5/ ደስተኛና የሚስብ ፈገግታ 6/ ፕሮፌሽናል አቀራረብ ጋር ያላቸውን ዜጎች በመመልመል በሚገባ በማሰልጠን በየኤምባሲዎቻችን ማሰማራት አለበት  ከዚያ በኋላ የሚመጣውን ለውጥ ለማየት ይቻላል። 

                    ጥላቻ-አልባ ገለልተኛ ሚድያ

ሚዲያ አለምን ከሚያሽከረክሩ ሃይላት 4ተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ትልቅ መሳሪያ ነው፤ በመሆኑም  ሚዲያ ለልማትም ሆነ ለጥፋት ለፍቅርም ሆነ ለጦርነት አስተዋጾው እጅግ ታላቅ ነው። … ተረታችንስ ሚዲያ ለጦርነት ያለውን አስተዋጻኦ “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” አይድል የሚለው፤ … እንደምናየው ከሆነ ለጊዢው ፓርቲ EBC /Ethiopian Broadcasting Corporation/ ለተቃዋሚዎች ደግሞ ESAT /Ethiopian Satellite TV/ እንዲሁም ሌሎች የግል ሚዲያዎች ያንድ ወገን አገልጋይ ስለሚመስሉ ሳይሆን እየሆኑ ፕሮፓጋንዳ በሚመስል ስራ ላይ ስለተጠመዱ አንዱ አንደኛውን ለማስወገድ እንጂ በተቃራኒዎች መካከል ስምምነትን ለማምጣት እየሰሩ አይደለም፤ ባጠቃላይ ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት እየሰሩ አይደለም። … በመሆኑም ለሁሉም ወገኖች በእኩልነት የሚያገለግል ‘ጥላቻ-አልባ ገለልተኛ’ አማራጭ ነጻ ሚዲያ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም። ይኽውም ገዢውን ፓርቲንም ሆነ ተቀዋሚ ፓርቲዎችንም እንዲሁም ገለልተኛ አመለካከት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በመቀበል የሚያጋለግል ገለልተኛ ሚድያ ለማቋቋም ራእይ ጥሪና አላማ ላላችሁ ሰዎች ጥሪ ማስተላላፍ ይገባል። … እንዲሁም የሶሻል ሚዲያው ያንድ ወገን ደጋፊ ሆኖ ጥላቻ ከማስፋፋት ይልቅ ሚዲያውን የማስታረቂያና የማግባቢያ መድረክ ለማድረግ መስራት አለበት … በተጨማሪም ሶሻል ሚዲያው በወገናዊነት ተከፋፍሎ ለሀገር የማይበጅ በተራ ቅስቀሳ ስድብና ነቀፌታ ማዶ ለማዶ በተቃዋሚና በደጋፊ ጠባብ ቡድን ውስጥ ተወስኖ የሚያጠፋፋ ፕሮፓጋንዳ በመባዝን ከሚሰራ ይልቅ ሁሉም ወገን ሊጠቀም በሚቻልበት ጥላቻ አልባ ስራ ቢሰራ በቀና አመለካከት ብሄራዊ መግባባትን ለማዳበር በእርግጠኛነት ያስችላል።

                 3ኛው አማራጭ ኣስተሳሰብ /Third Alternatives/

“እኛ የምንለው” … “እነሱ የሚሉት” ከሚባለው በግሎባላይዜሽን ዘመን ከማይሰራና አንደኛው ሌላውን ከሚያገልል ቡድናዊ ጠባብ ኣስተሳሰብ ነፃ ወጥተን “የጋራ ውሳኔያችን ትክክል ነው” በሚለው 3ኛው ኣስተሳሰብ /Third Alternatives/ መተካት አለበት … በአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ ዶ/ር መረራ ጉዲና “የአገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለውጭ ሃይል መጠቀሚያ ለመሆን ይዘጋጃሉ የሚል ግምት የለኝም” … “አባይን በሚመለከት ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ ያነሰ የአገር ስሜት አላቸው ብዬ አልገምትም” እንደ አሉት ሁሉም አባይን በጋራ ለመገንባት መነሳት ይገባዋል። … አባይን ለብሄራዊ መግባባት መሰረት ነውና። … አባይን ለጋራ አላማ በህብረት መስራት እንጂ … “ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ የተሻለ ብሄራዊ ስሜት አላቸው” … “ኢህአዴግም ከተቃዋሚዎች የተሻለ የብሄረሰቦች መብት ያስከብራል” ወዘተ የመሳሰሉት ተራ መነቃቀፎች ወደፊት ስለማንራመድ ወደ ኋላ መቅረት ላይ እንጂ የትም አያደርሱንምና ተጠንቅቀን ባንድነት መስራቱ ይበጀናል።

                      ለአባይ ግድብ የፋይናንስ ምንጮች

ለአባይ ግድብ ግንባታ ብድርም ይሁን እርዳታ በርግጠኛነት የሚገኝ ለመሆኑ ከግብጽ ዲፕሊማሲያዊ ጥረትና ውጤት አንጻር የተዘጋ ፋይል ይመስላል። … ሁሉም አማራጭ ከጠፋ በራሳችን አቅም እንሰራዋለን በማለት መንግስት ይውተረተራል። … እስካሁን ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ያህል (የግድቡን ወጭ 10%) ለመሰብሰብ እንደተቻለ ይፋ ሆኖአል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለይ በውጭ ሀገራት የሚኖሩቱ፥ … “ስልጣን ላይ ያለው መንግስት አሰብን ያለድርድር ስለሰጠ … አባይን ለመገደብ ሀገራዊ ሞራል ብቃትና ኢኮኖሚያዊ አቅም የለውም” … “አሁን ባለው ሁኔታ /trend)/ ህዝቡ ገንዘብ ዋጣቱን ያለማቋረጥ ቢቀጥል እንኳን 5 ቢሊዮን ዶላር ለግድቡ ስራ ለማጠራቀም ከአስር (10) አመታት በላይ ስለሚፈጅ ኢህአዴግና አባይ 0 ለ 0 ናቸው” ይላሉ። … በእኔ እምነት ግን ተቃዋሚው ወገን የአባይን ጉዳይ ለፖለቲካዊ ፍጆታ ለማዋል መሞከሩ አለማስተዋል ብቻ ሳይሆን ዝቅጠት ውስጥ መግባት ይመስለኛል። … የፋይናንስ አቅምን በተመለከተ ግን የራስን ቅሪት ባግባቡ በመጠቀም መፍትሄ ሊያመጡ የሚችሉ አምስት 5 ዋና ዋና የፋይናንስ ምንጭ አካላት ሊኖሩን ይችላሉ ብዬ በማመን የሚከተሉትን እጠቁማለሁ:-

                      ምንጭ -1- የሀገር ቤት ህዝብ

የሀገር ቤት ህዝብ እስካሁን ድርስ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ለማዋጣት ችሏል፥ … ከዚህ በተጨማሪ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ለማዋጣት ይችላል ብለን ብንገምት፥ … በድምሩ አንድ ቢሊዮን ዶላር በማዋጣት የግድቡን ወጭ 20% ድርሻ በመያዝ የአክሲዮን ባለቤት ይሆናል ምንም እንኳን ህዝቡ ገንዘብ ተርፎት ሳይሆን ከጉድለቱ ቢሰጥም፥ ለአባይ ታላቅ ሀገራዊ ልማት በህብረት መረባረቡ ሁለት ጎን ጥቅም አለው፥ … አንደኛው አባይ መልሶ የሚከፍል መሆኑ ሲሆን፥ … ሁለተኛው ደግሞ አባይ ሀገራዊ አንድነትንም በእጅጉ ማጠናከሩ ነው … ስለዚህ የሀገር ቤቱ ህዝብ ቀበቶንም መቀነትም ጠበቅ ማድረግ ያስፈልገዋል።

                    ምንጭ -2- ዳያስፖራ

ፖለቲካዊ የአመለካከት ችግር ባይኖር ኖሮ ኣንድ ሚሊዮን የሚጠጋው በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ /ዳያስፖራ/ ባማካይ በትንሹ 5 ሺ ዶላር በማዋጣት በ5 ቢሊዮን ዶላር አባይን ብቻውን ለመገደብ የሚያስችል አቅም አለው። … ነገርግን “ጽድቁ ቀርቶ…” እንደሚባለው ሌላው ቢቀር በትንሹ ባማካይ 1 ሺ ዶላር ቢያዋጣ በድምሩ 1 ቢሊዮን ዶላር (የግድቡን 20% ወጭ) በማውጣት በሀገር ግንባታና በኢንቨስትመንት አጋርነት ባለአክሲዮን ከመሆን በላይ ለሰላማዊ የመቻቻል ፖለቲካ በር ይከፍትም ያስከፍትም ነበር።

                   ምንጭ -3- ኢንዳውመንት ፈንድ /EFFORT/

የትግራይ ኢንዳውመንት ፈንድ ጠንካራ መሆኑን በሚሰራቸው ታላላቅ ልማቶች በርግጥ እያሳየ ነው። … አባይ ግድብ ዘላቂና አስተማማኝ ብቻ ሳይሆን የወጣበትን ውጭ ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመመለስ አቅም ያለው በመሆኑ ኢፈርት ለአባይ ግድብ ግንባታ አንድ ቢሊዮን ዶላር (የግድቡን 20% ወጭ )በማዋጣት ትልቁ ኢትዮጵያዊ የኢንዳውመንት ፈንድ ሆኖ ብሄራዊ ድርሻ ሊይዝ ይገባዋል።

                   ምንጭ -4- ሼክ መሀመድ ኣላሙዲ

አላሙዲ በአለም ቱጃሮች 75ኛ ተርታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን … በዘመናቸው አንድ ትልቅ ልማታዊ ስራ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰርተው ለማየት የማይጓጓ ሰው የሌለ አይመስለኝም። … በርግጥ ታዋቂ ሰዎችንና ዘፋኞችን ስለሚያሳክሙና ስለሚረዱ ለዚያም ምስጋና አለን። … ሀገራዊ ልማታዊ ስራን በተመለከተ ግን አላሙዲ እንደ ኣንድ ተራ ኢንቨስተር በሻኪሶ ብቸኛ የወርቅ ማእድን ማውጣትና ኤክስፖርት በማድረግ … በሊሙ በቴፒና በበቃ ሰፋፊ ዘመናዊ እርሻዎች ላይ የቡና ምርት መሰብሰብና ኤክስፖርት በማድረግ … በሸራተን የሆቴል ንግድ ከመስራት በስተቀር የህዝብን አንጀት የሚያርስ እርሳቸውንም እጀ-ሰባራ የማያደርግ መሬት ጠብ የሚል ስራ እየሰሩ እንደሆነ መረጃ የለኝም … ቢኖር ኖሮ አይደበቅም ይታይ ነብር። … በመሆኑም በእኔ እምነት አላሙዲ የህዝብ ልብ ውስጥ የሚገቡበት ዋና ስራ የአባይ ግንባታ አንዱ በመሆኑ በግንባታ ወጭው በሚገባ መሳተፍ አለባቸው። … ስለዚህም ሼክ መሀመድ ሳይበዛ በትንሹ ኣንድ ቢሊዮን ዶላር/የግድቡን ወጭ 20%/ በማዋጣት እጣ ቢገዙ ህዝቡ ‘እውነትም እኝህ ሰው’ የሚል ይመስለኛል። … ከዚህ በተጨማሪም በግብርናው ዘርፍም በምግብ ራስን በመቻል ፕሮግራም ቢሳተፉ አላሙዲ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ወዳጅ በመሆን ስማቸውን በመልካም ስራ ለዝንተ አለም ተጠራ ማለት ይሄኔ ነው። … /አላሙዲ “መፃፍ እንጂ ቁጥር አታውቅም ለካ!” እንዳይሉኝማ አቅም አስልቼ ነው የፃፍኩት/

                    ምንጭ -5- ፍላጎትና አቅም ያላቸው ኢትዮጵያውያን

ቀሪውን ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የግድቡን ወጭ /20% ያህል/ በውጭና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ፍላጎትና አቅም ያላቸው ኢትዮጵያውያን አክሲዮን ለመግዛት ቢችሉ ባጠቃላይ የተፈለገው 5 /አምስት ቢሊዮን ዶላር(ከነመጠባበቂያው)ግድቡን ያስጨርሳል ማለት ነው፤ ኢትዮጵያም የኤሌክትሪክ ሀይል አቅምዋን በኣራት እጥፍ በማሳድግ ጠንካራ የልማት መሰረትዋን ጣለች ለማለት ያስችላል።

                     ማጠቃለያ/   “ፍቅር የህግ ፍጻሜ ነው”

አገራችን ያለችበትን የፖለቲካ ትኩሳት በመረዳት … ካለፉት የጠላትነት ስሜት የጎደፈ ፖለቲካ ታሪካችን በመማር … የአለም አቀፍ ተጨባጭ ሁኔታ ግሎባላይዜሽንን በማገናዘብ፥ …በተለይም ልዩ መታወቂያችን የሆነውን ‘እርስበርስ የመጠፋፋት ፖሊሲያችን’ን በማስወገድ ብሄራዊ መግባባት ላይ በመድረስ ሀገራዊ እድገትን በጋራ የሚያራምድ የጋራ ብሄራዊ አጀንዳ ለመቅረፅ እራሳችንን እንታደግ “ይህ የሚቻል አይደለም” ለምትሉ፥ … ‘በፍቅር ከሆነ ሁሉም ይቻላል’ … “ሁሉም ነገር በፍቅር በጦርነትና ትክክል ነው” የተባለው እኮ፥ የሰው ልጅ የጠብመንጃ አፈሙዝ ከተደቀነበት፥ ወይም ደግሞ በተቃራኒው በፍቅር ከመጡበት ምንግዜም ቢሆን ተሸናፊ ስለሆነ ነው። … ፍቅሩ ቀርቶ ቢያንስ ጥላቻና ቂም በቀልን ወደኋላ ትተን … እርስ በራሳችን ምህረትንና ይቅርታን በማድረግ ዘላቂ የጋራ ሰላምና ልማት ለማምጣት አሁኑኑ እንነሳ … ፈቃጅም ወሳኝም እኛው ስለሆንን፤ ይህንን እውን ለማድረግ ከልብ እልኸኛነት በስተቀር የሚያቅተን የለም … መፅሀፍ ቅዱስ “እምነት፥ ተስፋ፥ ፍቅር ሶስቱ ጸንተው ይኖራሉ፥ ከሁሉም ፍቅር ይበልጣል” (1ኛ ቆሮንቶስ 13፤ 13) እንደሚል ‘በከፋው ፖለቲካችን ላይ ቤንዚን ሳይሆን ፍቅርን በመጨመር፥ ከህገ-እግዚአብሄርም ከህገ-ተፈጥሮም ሳንወጣ፥ … እራሳችንን እንታደግ።

ፍቅር ዝም ብሎ ከሜዳ ኣይመጣም፤ ፍቅርን ማምጣት ከባድም ቀላልም ነው። … ፍቅር የሚከብደው እልኸኛነትና ትእቢት ሲሞላብን ነው … ፍቅር የሚቀለው ደግሞ ከምህረትና ከይቅርታ ሲጀመር ነው … ‘እልኸኛነትንና ትእቢትን’ ከመረጥን መዘዙ ከባድ ነው፥ … መጽሀፍ “ትእቢት ውድቀትን ትቀድማለች” እንደሚል ከትእቢታችን ቀጥሎ ያለጥርጥር ውድቀታችን ያውም በውርደት ይመጣል። … ነገርግን ‘ይቅርታና ምህረትን’ ከመረጥን እዳው ገብስ ነው። … የፖለቲካ ባላንጣን እንድ ጠላት ላለማየት ‘መመነን’ ወይም ‘መመንኮስ’ አያስፈልግም። … ሰዎችን ለመውደድ ቢያስቸግር ቢያንስ ባለመጥላት የራስንም የባላንጣንም ደስታና ሰላም በመጠበቅ ለመጓዝ ግን ይቻላል። … መጽሀፍ “እርስበርሱ የሚቃረን መንግስት(ሀገር)አይጸናም” እንደሚል፥ መቃረናችን ባግባቡ ያለጥላቻና ቂም በቀል፥ ያለ እርስበርስ መጠፋፋትም፥ በመቻቻልና በመደራደር ብቻ ይሆን ዘንድ ግድ ነው።

በአለም ላይ ለጠላቶቻቸው ምህረትና ይቅርታ በማድረግ ያለጠላትነት በሰላም በጋራ የመኖር ጥበብ ሞዴሎች ከሆኑት የሀገር መሪዎች ውስጥ ኒልሰን ማንዴላና ማህተመ ጋንዲ ምንግዜም ተጠቃሽ ናቸው። ማንዴላ “ጠላትህን ውደድ” “ወንድምህ ቢበድልህ ሰባት ግዜ ሰባ ይቅር በለው” በሚሉት የመጽሀፍ ቅዱሰ መመሪያዎች መሰረት … በቄስ ዴዝሞንድ ቱቱ ምክር በመታገዝ ለግፈኞቹ ህዳጣን ነጮች ገዢዎች ታላቅ ምህረትና ይቅርታ አድርገው ደቡብ አፍሪካን የሁሉም እኩል መኖሪያ /የኢኮኖሚ እኩልነትን Economic Equality ሳይጨምር/ በማድረግ ዲሞክራሲና ሰላምን አስፍነዋል። … ኒልሰን ማንዴላና ማህተመ ጋንዲ በሀገራቸው አስተማማኝ ሰላምና እድገት ለማምጣት የመረጡት ይቅርታና ምህረት ያለበትን የፍቅር ጎዳና ሲሆን፤ እንዳዋጣቸው የምናውቀው ዘላቂ ሰላምና ዲሞክራሲ በማስፈን በብልጽግና ጎዳና ላይ መሆናቸው ነው። … ጋንዲን ካነሳን አይቀር አርአያነታቸው ብቻ ሳይሆን ከመልካም ተሞክሮአቸው ከተገኘው ምክራቸው ለእኛ የባህርይ ለውጥ /መግባባት/ ለማምጣት ምንግዜም ቢሆን ቀና አስተሳሰብ ያስፈልጋልና ‘ታናሽ የምትመስል’ ‘ታላቅ ምክራቸውን’ እንጠቀምባት … ”Keep your THOUGHTs Positive because your Thoughts become your WORDs … Keep your words Positive because your Words become your BEHAVIOR … Keep your Behavior Positive because your Behavior becomes your HABITS … Keep your Habits Positive because your Habits become your VALUEs … Keep your Values Positive because your Values become your DESTINY.”

በአንድ ወቅት አንድ የእንግሊዝ ቄስ ለማህተመ ጋንዲ መፅሀፍ ቅዱስ ሲሰጣቸው … ጋንዲ የመለሱት መልስ አስገራሚ ነበር፤ “እናንተን /እንግሊዞችን/ አልወዳችሁም ኢየሱሳችሁን ግን እወደዋለሁ” በማለት፥ … እንግሊዞች መፅሀፍ ቅዱስን መሸከም እንጂ የሰላም ትእዛዛቱን፤ የፍቅር መንገዱን ሲዘነጉት፥ … ጋንዲ ግን የፍቅርና የሰላም መንገድን አሸናፊነት ተረድናውት ነበርና ነው። … ጋንዲም ይሁኑ ኒልሰን ማንዴላ የበርካታ ብሄረሰቦችና ሀይማኖቶች ሀገሮቻቸውን ከጥላቻና ከቂም በቀል ፖለቲካ ያፀዱት በሁለት ነገሮች ብቻ ነው … 1/ በምህረትና ይቅርታ /Forgiveness/ 2/ ገደብ በሌለበት ፍቅር ናቸው፥ … እኛስ? አሸባሪ … ዘረኛ … ጠባብ … ትምክህተኛ … ነፍጠኛ … ተለጣፊ … ባንዳ … ጎበና ወዘተ በመባባል አንዳችን አንዳችንን ለማጥፋት ስለት ከመሳል፤ ጦር ከመስበቅ ይልቅ፤ … በመተሳሰብና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ጥላቻ-አልባ የፖለቲካ ህይወት ወሳኝ በመሆኑ … በምህረትና በይቅርታ ታድሰን፥ በመቻቻል ተደራድረን፥ ፍትህና ነጻነት፥ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማምጣት ግድ አይለንም? … ዘላቂና እውነተኛ ሰላም፥ ልማት ነፃነትና እኩልነት የሚኖሩት ፍቅር ሁሉን ሲያሸንፍ ብቻ ነው … ምክንያቱም ፍቅር የሕግ ፍፃሜ ነውና /ሮሜ ምእ. 13-10/ … “ቤት በጥበብ ይሰራል፥ በማስተዋልም ይጸናል፥” የሚለውም ያኔ ተግባራዊ ይሆናል።

            ፈጣሪ ማስተዋሉን ያድለን                  

           danruth2000@gmail.com

የመንፈሳዊ አመራር ያለህ !!!

የመንፈሳዊ አመራር ያለህ !!!

 (በዮሴፍ ወርቁ ደግፌ)

በአሜሪካ የፔንሴልቬኒያ ክፍለ ግዛት በላንካስተር አነስተኛ ከተማ ውስጥ በመንፈሳዊ አመራር ጉድለት የተነሳ ተበታትነው በሚገኙት የወንጌላዊት ቤተክርስቲያናት ላይ ያጠነጠነ ዳሰሳዊ ጥናት (Assessment)

ምእራፍ -1- መግቢያ 

1.1     ሶስት አይነት ሰዎች

1. ፍጥረታውያን ሰዎች

መፅሀፍ ቅዱስ ሰዎችን በአጠቃላይ በሶስት ይከፍላቸዋል። እነዚህም ፍጥረታውያን ስጋውያንና መንፈሳውያን ሰዎች ናቸው። ፍጥረታውያን ሰዎች በእግዚአብሄር ማመን ሞኝነት ስመሰላቸው፤ ከእግዚአብሄር በተቃራኒው በራሳቸው መንገድ በደመነፍስ-ስሜታቸው እንደመራቸው የሚዋትቱ ናቸው። እነኚህ ሰዎች በቃኝና እረፍት የሌለበትን ምድራዊ ምኞቶቻቸውን ብቻ በማሳደድ ሌት ተቀን የሚባትሉ ሰዎች ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስም እንደዚህ አይነት ሰዎችን “ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም በማለት በ1ኛ ቆሮንቶስ 2፤14 ይመሰክርባቸዋል።ፍጥረታውያን ሰዎች ዕድል ፈንታቸው በህይወታቸውና (በእጃቸው) ወይም ከዚህ አለም ብቻ ስለሚመስላቸው፤ ወደዘላለም ሞት የሚጓዙ መሆናቸውን እንኳን ላያውቁትም ስለሚችሉ፤ የቤተክርስቲያን ስብከት ብቻ ሳይሆን የክርስቲያኖች የህይወት ምስክርነትም ይበልጥ የሚያስፈልጋቸው ብርቱ የሚመስሉ ነፍሳቸው ግን እጅግ የጎሰቆለችና የከሳች ሰዎች ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስ “እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች…” (መዝሙር፤ 17፡14) የሚላቸው እንደነዚህ አይነት ሰዎችን ነው። ከዚህ የተነሳም የአለም መድሀኒት የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀሉ ሀይል እና በትንሳኤው ጉልበት ለፈፀመው የዘለላም ህይወት (የደህንነት ጥሪ) ልባቸውን በማደንደን፤ ነገርግን የአለምን ከንቱ ነገር በመከተል ልባቸው እንደፈለገው የሚነዳቸው ናቸው።

ፍጥረታውያን ሰዎች በሃጢያት ብዛት አለምን በማተራመስና በማጎሳቆል የሙስና ህይወት (corrupted life) የሚኖሩ፤ ከምድራዊ ኑሮ-ከራሳቸው ሕይወት ውጭ የሚመኩበት ምንም ነገር ስለሌላችው ራሳቸውን እስከማምለክ የሚደርሱ ሰዎች መሆናቸውን በገሀዱ አለም የምናየው ነው። እግዚአብሄርን መምረጥ ወይም አለመምረጥ ጉዳይ የምርጫ ጉዳይ ስለሆነ፤ ፍጥረታውያን ሰዎች እግዚአብሄርን ለመምረጥ ያልፈለጉና ህሊናቸውን ያሳወሩ ሰዎች ናቸው። ፍጥረታውያን ሰዎች በምድርም ላይ የህይወት ዘመናቸው ስጋዊ ፍሬዎችን ስለሚያፈሩ የእግዚአብሄርን መንግስት እንደማይወርሱም መዕሀፍ ቅዱስ ይናገራል። የስጋ ፍሬዎችም (“ዝሙት፤ ርኵሰት፤ መዳራት፤ ጣዖትን ማምለክ፤ ምዋርት፤ ጥል፤ ክርክር፤ ቅንዓት፤ ቁጣ፤ አድመኛነት፤ መለያየት፤ መናፍቅነት፤ ምቀኝነት፤ መግደል፤ ስካር ዘፋኝነት፤ ይህንም የሚመስል ነው፤ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤” (ገላትያ 5፤19-21) ናቸው። ስለሆነም ፍጥረታውያን ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን አርነታቸውን ሰላላወጁና በእግዚአብሄር መንፈስም ስለማይመሩ፤ ዘወትር ከአለም ከስጋና ከሰይጣን ቀንበር በታች የሚኖሩ ሰዎች ሲሆኑ፤ ነገርግን በስጋ ሞት ከማለፋቸው በፊት ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው ለመምረጥ እድል ምንግዜም ቢሆን ያላቸው ሰዎች ናቸው።

2.  ስጋውያን ሰዎች

መፅሀፍ ቅዱስ ሁለተኛዎቹን ሰዎች ደግሞ ስጋውያን ሰዎች ይላቸዋል። እነዚህም በቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ አብላጫውን ቁጥርም የሚይዙ ሰዎች ሲሆኑ፤ ፈቃዳቸውንም ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሄር ያላስገዙ በመሆናቸው መንፈሳዊ ፍሬዎችን ለማፍራት ያልቻሉ ፍሬ አልባ ክርስቲያኖች እንደሆኑ መፅሃፍ ቅዱስ ይናገራል። በተጨማሪም ስጋውያን ክርስቲያኖች ከተግባራቸው የተነሳ መዳናቸውን አረጋግጠው ለመኖር ስላልቻሉ መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ይገልፃቸዋል። “እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው። ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።” (ዮሃንስ 15፤ 1-2 ) ደግሞም “ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል። በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።” (ዮሀ. 15፥ 4-6)። ይህ የህይወት ቃል የተፃፈው ለአለማውያን ሳይሆን በርግጥ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚኖሩ ወይም የሚመላለሱ ለስጋውያን ክርስቲያኖች መሆኑ አያጠራጥርም።

ስጋውያን ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ ስም የሚመላለሱ፤ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ሳይሆን፤ የራሳቸውንና የእግዚአብሄርን ፈቃድ በመቀላቀል የሚከተሉ ሰዎች ሲሆኑ፤ መንፈሳዊ አምልኮ መልክ ያላቸው፤ ነገርግን ስጋዊነት በእኔነት ላይ አድርቶ (ተመስርቶ) የሚገዛቸው፤ መንፈሳዊ ፍሬ የማይታይባቸው፤ በከንቱ የሚደክሙ ሰዎች ናቸው። ይኸውም የእግዚአብሄር መንፈስ እንዳይሰራ ማድረጋቸውን እንኳን ሳያስተውሉ የሚኖሩ በመሆናቸው ከሁሉ ይበልጥ ጎጂነት አለው። ለዚህም ነው ስጋውያን ክርስቲያኖች ለቤተክርስቲያን መሰነጣጠቅና (መከፋፈል) ደግሞም ለእግዚአብሄር ህዝብ መበታተን ዋነኛ ተዋናዮች የሚሆኑትና መንፈሳዊ ፍሬ አልባ ጉዞ የሚጓዙት። ስጋውያን ክርስቲያኖች የቤተክርስቲያን ምእመናን ብቻ ሳይሆኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሊሆኑም ይችላሉ። ምክንያቱም መንፈሳዊ ፍሬዎችን የማታፈራ ቤተክርስቲያን በስጋውያን መሪዎች መመራትዋ የማይቀር ስለሆነ ነው። በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት የኤስ. አይ. ኤም. ስነ-ፅሁፍ ክፍል እ.ኤ.አ. 2005 ዓ.ም. ባሳተመው መፅሀፍ በቤበተክርስቲያን ውስጥ የብዙ ችግሮች ምንጮች መንፈሳዊ ያልሆኑ መሪዎች እንደሆኑ ይናገራል። ከዚህ የተነሳ ስጋውያን የቤተክርስቲያን አመራሮች በአሰራራቸው እግዚአብሄርን ለማስደሰት ስለማይችሉ፤ የእግዚአብሄር ወገን እንዳልሆኑና መንፈሳዊ ፍሬዎችንም ለማፍራት እንደማይችሉ መፅሀፍ ቅዱስ ይናገራል። “በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም። እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም፤” (ሮሜ 8፤8-9) ደግሞም የዚህ አለም ባለጠግነት ከንቱ ሃሳብም፤ ምኞትም አእምሮአቸውን፤ ስጋቸውን፤ ስሜታቸውንና መንፈሳቸውን ጨምድዶ ስለያዘው የእግዚአብሄርን ቃል ያንቃሉ። ፍሬም አያፈሩም። ”የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል።…” (ማርቆስ፤ 4፥19)

በመሆኑም ስጋውያን ሰዎች እንደ አለማውያን ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ “…ጥል፤ ክርክር፤ ቅንአት፤ ቁጣ፤ አድመኝነትና መለያየትን…” (ገላትያ 5፤19፤21) ከስጋዊ አሰራራቸው የተነሳ ስለሚያመጡ ለነፍሳት (አዲስ ሰዎች) የደህንነት ማሰናከያ ይሆናሉ። በዚህም የወንጌልን ስራ ባለማስተዋል ያደናቅፋሉ። በተጨማሪም ስጋዊነት በአማኞች መካከልም መንፈሳዊ ህብረትና አንድነትን ለማምጣት ስለማያስችል፤ ቤተክርስቲያን በየጊዜው እየተሰነጣጠቀች የመገኘትዋ ምስጢር ሌላ ሳይሆን፤ ይኸው የስጋዊነት ችግር መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም። የስጋዊነት ወይም የእኔነት ችግር በክርስቶስ ኢየሱስ ትምህርት ላይ በእውነት እና በማስተዋል በመንፈስ ለመቆም ያለመቻል፤ ወይም በወይኑ ግንድ በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ በመጣበቅ መንፈሳዊ ፍሬዎችን ለማፍራት ያለመቻል ችግር ሲሆን፤ ይህም ችግር በምዕመናን፤ በአገልጋዮች፤ በወንጌላውያን፤ በፓስተሮች፤ በዘማሪዎች፤ እና በሽማግሌዎችም ላይ እየታየ የሚገኝ፤ የመንፈሳዊ ህብረትና አንድነት ደግሞም በረከት ዋነኛ ጠላት ነው። “ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው…በዚያ እግዚአብሄር በረከቱን፤ ህይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና” (መዝሙር፤33፤1) እንደሚለው ህያው ቃል በመኖር በረከትን ለማግኘት አለመቻል የስጋዊነት ውጤት ነው። ስለዚህ ክርስቲያን ሁሉ በእግዚአብሄር መንፈስ እየተመራን መንፈሳዊ ሰው መሆን ካልቻለና፤ ክርስቲያን ነኝ በማለታችን ብቻ መንፈሳዊ ሰው ለመሆንና ደህንነታችንነም ለማረጋገጥ ስለማንችል (ፍሬዎቻችንን እያየን) ራሳችንን በመፈተሽ ልንመለስ ይገባል።

3.  መንፈሳውያን ሰዎች

ሶስተኛዎቹ ደግሞ መንፈሳውያን ሰዎች ሲሆኑ፤ በመንፈሳዊ ህብረት (ቤተክርስቲያን) ውስጥ እጅግ በጣም ጥቂት ቁጥር ያላቸው እና በእግዚአብሄር መንፈስ ብቻ በመመራት የሚኖሩ ናቸው። መንፈሳውያን ሰዎች “ፍቅር፤ ደስታ፤ ሰላም፤ ትዕግሥት፤ ቸርነት፤ በጎነት፤ እምነት፤ የውሃት፤ ራስን መግዛት…።” (ገላትያ 5፡ 22-23) የመሳሰሉትን መንፈሳዊ ፍሬዎችን በማፍራት ስለሚመላለሱ የእግዚአብሄር ሰዎች መሆናቸው ይታወቃል። መንፈሳውያን ሰዎች በአማኞች ህብረት (ቤተክርስቲያን) ውስጥ የልብንና የመንፈስን አንድነት እንዲኖር የሚተጉ፤ በወንጌል ስም የግል አላማና ጥቅም የሌላቸው፤ እግዚአብሄርን በመፍራት የሚሰሩ፤ የእግዚአብሄርን ህዝብ የሚያከብሩና የሚያፈቅሩ ሰዎች ናቸው። የመንፈሳውያን ሰዎች ዋነኛ መገለጫቸው ወይም መለያቸው መንፈሳዊ ፍሬዎችን ለማፍራት መቻላቸው ነው። በመሆኑም መንፈሳውያን ሰዎች በስጋዊ ክርስቲያኖች መካከል ተውጠው ያለ መንፈሳዊ ፍሬዎች የሚቀሩ ሰዎች እንዳልሆኑም በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱልን መንፈሳዊ አባቶችና እናቶች ልንማር እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪም መንፈሳውያን ሰዎች ለሌሎች ወገኖች መንፈሳዊ እድገት የሚተጉ፤ ላልዳኑት ሰዎች የደህንነትን መንገድ የሚያሳዩ፤ የሚፀልዩ፤ የሚያስተምሩ፤ የሚመክሩ፤ የሚያስታርቁ፤ ይቅር የሚሉ፤ የሚምሩ፤ ትሁታን እንጂ ከራስ በላይ… ራስ ወዳዶች… ራሳቸውን ያልካዱ ሰዎችም በፍፁም አይደሉም። ከዚህ በተጨማሪም መንፈሳውያን ሰዎች ሁሉን በመንፈስ በመመርመር የሚራመዱ ናቸው። “….መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል…” (1ኛ ቆሮንቶስ 2፤ 17) መንፈሳውያን እያንዳንዱ ጉዞአቸውንም በመንፈሳዊ ፍሬዎች የሚመዝኑ እንጂ፤ ዘመናቸው በከንቱ ያለ መንፈሳዊ ፍሬዎች የሚነጉድባቸው (የሚቃጠልባቸው) ፍሬ-አልባ ክርስቲያን አይደሉም። የመንፈሳውያን ሰዎች በዚህ ምድር የመኖር ዋነኛ አላማ ለእግዚአብሄር ክብር መኖርና፤ ለሰዎችም ደህንነትና መንፈሳዊ በረከት መሆን ብቻ ነው። ይሁንና ዋነኛው ጥያቄ መንፈሳውያን ሰዎች በአንድ ህብረት (አነስተኛም ብትሆን) ውስጥ አሉ ካልን፤ ፍሬዎቻቸው ወዴት አለ? በማለት መጠየቅ ይጠበቅብናል፤ ምክንያቱም ክርስትና “ሾላ በድፍኑ”…“ውስጡን ለቄስ” እያልን የምንኖርበት ተራ ህይወት አይደለምና ነው።

1.2 የጥናቱዳራ

1.2.1 የላንካስተር ቤተክርስቲያን

ቤተክርስቲያን ሰማያዊ (መንፈሳዊ) ደግሞም ምድራዊ ተቋም መሆንዋን በቅድሚያ ማወቅ አመራርዋን እና አሰራርዋን ፍሬያማ ለማድረግ ይጠቅማል። ይኸውም የቤተክርስቲያን ተቋምነት የሚለካው በአካል ብልቶች አንድነት ምሳሌ እንደተጠቀሰው፤ የዳኑ ሰዎች-በክርስቶስ ኢየሱስ መንፈስ በአንድ ልብ ሆነው የሚኖሩባትና መንፈሳዊ ፍሬዎች የሚፈራበት ነው። “በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።” (ሮሜ 12፡ 4-5) ተብሎ እንደተፃፈልን ማለት ነው። እንደዚሁም ደግሞ ሐዋርያው ጰውሎስ በእርሱና በመንፈሳዊ ልጁ በቲቶ እንዲሁም በሌሎች አማኞች መካከል ስለሚኖረው ህብረትና አንድነት ወይም ስለ ቤተክርስቲያን ህብረትና አንድነት እንደሚከተለው ብሎ መፃፉ በምድር ላይ ስላለው አንድነትና ህብረት ነው። “በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤” (ቲቶ 1፡4) በስጋ ከመውለድ የበለጠውን መንፈሳዊ ልጅነትን ወይም አንድነት ነው ቅዱስ ጳውሎስ እዚህ ላይ የገለጠውና ለትምህርታችን እንዲሆን የፈለገው እንጂ፤ በአለምም ቢሆን ውጤታማ ህብረቶችና አንድነቶች ሞልተዋል።

ቤተክርስቲያን ምድራዊ ተቋምም መሆንዋ የሚገለጠው ደግሞ ሰማያዊውን ተልዕኮዋን ለመወጣት በምድር ላይ በሰዎች አማካይነት የምትሰራ እንደመሆኑ መጠን ድርጅታዊ መዋቅር (Organizational structure) እና ከሁሉ በላይ ደግሞ ጥሪና ራእይ ባለው ተልእኮዋን ለማስፈፀም በተጠራ አመራርና አስተዳደር (Christian Leadership and Church Administration) የምትመራ ተቋም (Institute) በመሆን ነው። ቤ/ክርስቲያን ሰማያዊ ተልእኰዋን በሚገባ ለመወጣት ምድራዊ ተቋምዋ ጠንካራ መሆን ያለባትም ለዚህ ነው። ይኸውም ሁሉንም ዝርዝር ጉዳዮችዋን በፍቅር፤ በግልፅነትና በነፃነት ለመስራት የምትችልበት የመተዳደሪያ ደንብ እና የፋይናንስ ደንብና የመሳሰሉት የውስጥ መመሪያዎች ሲኖራትና ሲሰራባቸው ጠንካራ ምድራዊ ተቋም በመሆን ሰማያዊ ተልእኮዋን ለመወጣት ያስችላታል ነው።

የቤተክርስቲያን ሰማያዊና ምድራዊ ተቋምነት አሰራሮች የሚጣረሱትና ቤተክርስቲያን በስጋ ስራዎች የመከፋፈል አደጋ የምትበታተነው አመራርዋ ጥሪና ራእይ ሳይኖረው ሲቀርና፤ ከመንፈሳዊነት ይልቅ ስጋዊነት ወይም ንቅዘት (corruption) ውስጥ ሲገባ ብቻ ነው። በመሆኑም ስጋዊነት (እኔነት) በመንፈሳዊነት ላይ ሲያይል የቤተክርስቲያን መሰነጣጠቅና የምእመናን መበታተን ችግር በቀላሉና በተደጋጋሚ ይከሰታል።

1.2.2 የላንካስተር ቤተክርስቲያን ዳራ

በአሜሪካ የፔንሴልቬኒያ ክፍለግዛት በላንካሰተር የገጠር ከተማ ውስጥ የወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ህብረት በአንድነት የሚገለገሉባት አንዲት ቤተክርስቲያን ብቻ የነበረች ሲሆን፤ ከወንጌል ተልዕኮ እና አላማ ውጭ በተደጋጋሚ ጊዜያት ቢያንስ ለስድሰተኛ ጊዜ ስድስት ቦታዎች በመሰንጠቅዋ (በመከፈልዋ) ምክንያት የእግዚአብሄር ህዝብ ተበታትኖና ፍሬ አልባ ሆኖ ይገኛል። ለማስረጃ ያህልም እኔ ወደ ላንካስተር ከመጣሁኝ 5 አመታት የተቆጠሩ ሲሆን፤ በወቅቱ ተከፋፍለው ነው ተብለው ያገኘሁዋቸው 3 (ሶስት) ቤተክርስቶያናት ብቻ ነበሩ፤ ከ5 (አምስት) አመታት በሁዋላ መከፋፈሉ ቀጥሎ ዛሬ 6 (ስድስት) ጥቃቅንና ደካማ “ቤተክርስቲያናት” ደርዘን እንኳን የማይሞሉ፤እያንዳንዳቸው ስድስትና ሰባት ሰዎችን ይዘው እርስበርሳቸው ያለፍቅር በመኖር እየተገፋፉና እተከፋፉ መንፈሳዊ ፍሬ አልባ ጉዞአቸውን ተያይዘውታል።

በመሆኑም ይህ ዳሰሳዊ ጥናት የተበታተኑት መሪዎች እግዚአብሄርን በመፍራት ምዕመኑንም በማፈቀር የአንድነትና የህብረት ጥማቱንም በማየት፤ ቤተክርስቲያንዋ ተመልሳ አንድ የምትሆንበትን መንፈሳዊ መንገድ ሊያመጡ ይችላሉ፤ በሚል ዕምነት የተበታተነችውን ቤተክርስቲያን በአንድ ላይ በማጠቃለል ዳሰሳውንም ሆነ አስተያቱን ያጠናክራል። ቤተክርስቲያኒቱ ከሁለት አስርት አመታት በላይ እድሜ እንዳላት ነባሮች ይናገራሉ። እንደዛሬው በርከት ያሉ የምድረ አበሻ ስደተኞች ከመሰባሰባቸው በፊት፤ በወቅቱ ለፀሎትም፤ ይሁን ለመፅሀፍ ቅዱስ ጥናት፤ በክርስቶስ ስም ታናሽዋን ህብረት ለጠነሰሱትና የጀመሩት ወገኖች ታላቅ መሰረት ጥለው ነበር። እንደዚሁም ቤተክርስቲያንዋ የመሰነጣጠቅ አባዜ ከመጀመርዋ በፊት፤ በአንድ ልብና በአንድ መንፈስ፤ በወንድማማች ህብረትና ፍቅር በመሰባሰብ ተባብረውም ይሰሩ የነበረ ስለሆነ ቤተክርስቲያኒትዋ አሁን በሰው ሰራሽ (ስጋዊ ስራዎች) የመበታተን ችግር ውስጥ ብትሆንም በዚያን ወቅት መልካም ጅማሬ በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል።

የቤተክርስያንዋ መስራቾች ሊወቀሱበት የሚገባ ነገር ቢኖር፤ የአማኞች ህብረት መሰብሰቢያ የሆነችው ቤተክርስቲያን እንደ መንፈሳዊ ተቋምነት መሰረትዋና ማእከልዋ ማድረግ ያለባት ኢየሱስ ክርስቶስን እና መፅሐፍ ቅዱስን  መሆኑን የሚያጠያይቅ አይደልም። ከዚያ በመለስ ግን፤ ታናሽዋ ህብረት (መንፈሳዊ ማህበር) እንደ ምድራዊ ተቋምነትዋ፤ እግዚአብሄር ርስቴ ላለው ህዝቡ (አባላት-ምዕመን) ተጠሪና የበላይ የሆነበት ድርጅታዊ መዋቅር አስተዳደርና አሰራር አለመቀየሳቸው ዋነኛ መሰረታዊ ችግር ሆኖ ይታያል። ከዚህ በተጨማሪም ደግሞ የቤተክርስቲያን የመተዳደሪያ ደንብ፤ ራዕይና ተልእኮ መግለጫዎች፤ የቤተክርስቲያን የፋይናንስ አሰተዳደር መመሪያ፤ የቤተክርስቲያን የውስጥ አሰተዳደር ደንብ፤ ወዘተ በወቅቱ በአለመቀረፃቸው፤ የተነሳ የግለሰቦች የበላይነትና “እኔ እሻል” (እኔ እበልጥ) ፎክክር መኖር የዛሬው መበታተን ዋነኛ ምክንያት ሆኖአል። ከዚህ ሁሉ በፊትና በላይ ደግሞ ለመሪነትና ጥሪውና ስጦታ ደግሞ ራእይ ያላቸውን ሰዎች በመንፈሳዊ አመራርና ቦታዎች ላይ በማስቀመጥ አለመጀመራቸው የመጀመሪያው ትልቅ ስህተት ሆኖ ተገኝቶአል። ባጠቃላይ የቤተክርስቲያን መሪዎች ተጠሪነት ለጠቅላላ ጉባኤው ወይም ምዕመናን በማድረግ ተጠያቂነትን ከአንድ ግለሰብ ይልቅ ወደ እግዚአብሄር ህዝብ (የምእመን ጠቅላላ ጉባኤ) በማዛወር የቤተክርስቲያን ባለቤትነትን ከክርስቶስ በታች ለጠቅላላ ጉባኤው ስልጣንና ወሳኝነት ባለመሰጠቱ የተነሳ የፈለጉትን ነገር እንደፈለጉት ማድረግ ለቻሉት ጥቂት ግለሰቦች እጅ ቤተክርስቲያን በመውደቅዋ፤ ቤተክርስቲያን ዛሬ እደረሰችበት ደረጃ ላይ በቀላሉ በመድረስ ልትወድቅ ችላለች።

በላንካስተር እና አካባቢዋ ህፃናትን ጨምሮ ከስድስት (600) የማይበልጡ ትውልደ ኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች እንደሚኖሩ መረጃዎች ሲጠቁሙ፤ ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህል የሚጠጋው የወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መሰረተ እምነት ተከታዮች (አማኞች) እንደሚሆን ይገመታል። ከዚህ አንፃር በእግዚአብሄር መንፈስ ብቻ የሚሆነው መንፈሳዊ አመራር እና የውስጥ አስተዳደር፤ የልብ እና የመንፈስ አንድነት፤ ከዚሁም ጋር ሁሉን የሚጠቀልለውና ከሁሉ የሚበልጠው የመንፈስ ፍቅር ቢኖር ኖሮ ግን፤ ባካባቢው የሚኖረው ምዕመናን ቁጥር አንድ አነስተኛ ቤተክርስቲያን እንኳን የማይሞላ ነበር። አሁንም ነው። በዚህ ጥናት መሰረት ቤተክርስቲያንዋ ህብረት ከጀመረችበት ከጥቂት አመታት በሁዋላ እና በተለይም ደግሞ በአሁን ወቅት ያለችበት ሁኔታ ሲታይ ከመንፈሳዊ ደረጃ በመውረድ፤ ስጋዊነት እና እኔነት የነገሰባት፤ ተልዕኮዋንና  አላማዋን ለመወጣት ያልቻለች፤ ራእይ የሌላት፤ በሰውኛ ጎዳና ስለምትጓዝ ጥል፤ ክርክር፤ ቅንአት፤ ቁጣ፤ አድመኝነትና መለያየትን (ገላትያ 5፤19-21) የነገሰባት፤ ላልዳኑት ሰዎች ማሰናከያ እና መዘባበቻ የሆነች፤ ለዳኑት ደግሞ ያለመንፈሳዊ  ፍሬ እድገትና የህይወት ለውጥ በከንቱ መመላለሻ የሆነች፤ ተተኪ ትውልድ የሌላት (የማታፈራ) “አመራሩ” በግልፅነትና በተጠያቂነት (Accountability and Transparency) የማይሰራባት፤ ምእመናኑን አንድነትና ህብረት ያጣባት፤ ባጠቃላይ እየሄደች የማትሄድ፤ ማደግዋን (መብዛትዋን) በመከፋፈል የምትለካ፤ ስድስት ትናንሽ በድካም ብዛት የጠወለጉ የደረቀች ቤተክርስቲያናት ሆና ትገኛለች።

1.3   የዳሰሳዊ ጥናቱ መንስኤ

 1.  ተበታትነው የሚገኙት የቤተክርስቲያኒትዋ አመራሮች በመንፈስ ጀምረው በስጋ በመጨረሳቸው ምክንያት የዚህ ዳሰሳዊ ጥናት ዋነኛ መንስኤ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም…
 2.   አካሄዳችንም መንፈሳዊ ባለመሆኑ፤ ይኸውም በአንድ ልብና በአንድ መንፈስ ደግሞም በፍቅርም ባለመመላለሳችን፤ መንፈሳዊ ፍሬዎችን ሳይሆን ስጋዊ ፍሬዎችን…“የሥጋ ሥራም        የተገለጠ ነው  እርሱም ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥…” (ገላትያ 19-21) እያፈራን በአለማስተዋልና ከዚያም በላይ በግብዝነት እየተመላለስን በመገኘታችን ምክንያት የጥናት ዋነኛ መንስኤ ሆነ።
 3. ለመንፈሳዊ ህብረት ዋነኛ እንቅፋት ከሚሆኑት የቤተክርስቲያን ችግሮች አንደኛው የመንፈሳዊ አመራር ችግር መሆኑን አለማስተዋል በራሱ ችግር ሲሆን እያወቅንም ከሆነ ግብዝነት ስለሆነ የዚህ ዳሰሳዊ   ጥናት መንስኤ ሆነ።
 4. ከሁሉም በላይ ደግሞ በእኛ ክርስቲያን ተብለን በምንጠራው ሰዎች ስራ ምክንያት በጌታ ስም የምትጠራው ቤተክርስቲያን የደህንነት ቤት፤ የፈውስ ቤት፤ የሰላም ቤት፤ የፍቅር ቤት፤ የመንፈሳዊ እድገት ቤት መሆን ሳትችል ሲቀርና ከሁሉም በላይ ደግሞ ላልዳኑት ወገኖቻችን ማሰናከያ ስለሆንን የዚህ ዳሰሳ ጥናት መንስኤ ሆነ።

ከዚህም በመነሳት ይህች አነስተኛ ጥናታዊ ፅሁፍ የቤተክርስቲያን መሰነጣጠቅና የእግዚአብሄር ህዝብ መበታተን ችግር ብዙ ጊዜ እንደምናሳብበውና እንደምንለው ሰይጣን የፈጠረው ችግር ሳይሆን፤ ምንጩን ስጋዊነት እና እኔነት ላይ የተከለ የሰዎች አመራር ችግር ነው በማለት የምትሞግተው። እንደዚሁም ደግሞ ምዕመኑ በመንፈሳዊ ህይወቱ ባለመጎልበቱ በመንፈሳዊ ህይወቱ ድርቀትና ውድቀት ከሚያመጡት ምክንያቶች አንዱ የመንፈሳዊ አመራር ችግር ነው። በሌላ በኩል የሚታየው የመንፈሳዊ አመራር ችግር ደግሞ…

 1. ቤተክርስቲያን የውስጥ አስተዳደር ችግርዋን ለመፍታት ስላቃታት በተገላቢጦሽ ከአለም ዳኝነትና ፍትህ ጠያቂ የመሆንዋ ምክንያት የመንፈሳዊ አመራር እጦት መሆኑ፤
 2. ቤተክርስቲያን ለአለም የሰርቶ ማሳያ ስፍራ መሆን ሲገባት የአጥፍቶ ማሳያ ስፍራ የመሆንዋ ምክንያት፤ የመንፈሳዊ አመራር ችግር መሆኑ፤
 3. መንፈሳዊ አመራሩ ያለግልዕነትና (Transparency) ያለተጠያቂነት (Accountability) መስራቱና እኔነት መግነኑ የመንፈሳዊ አመራር ችግር መሆኑ፤
 4. የቤተክርስቲያን የውስጥ አስተዳደርና አሰራርዋ በየጊዜው እየተበላሸ ስለሄደ ምእመናን በአመራሩ ላይ አመኔታ ማጣታቸው የመንፈሳዊ አመራር ችግር በመሆኑ፤ ይኸውም በመንፈሳዊ አመራር ምትክ የስጋዊ  አመራር እየተስፋፋ የምእመኑ የልብና የመንፈስ አንድነት እየተሸረሸረ መተማመን መጥፋትና መበታተን የአመራር ችግር መሆኑ፤
 5. በክርስቶስ ስም የተቋቋመች መንፈሳዊ ህብረት፤ የመንፈስ ሳይሆን የስጋ ፍሬዎችን የማፍራትዋ ምክንያት መንፈሳዊ አመራር ከማጣት የተነሳ በመሆኑ፤ ከዳሰሳዊ ጥናቱ መንስኤዎች መካከል ዋነኞቹ ሆነዋል

1.4 የዳሰሳዊ ጥናቱ አላማ

 1. የዚህ ዳሰሳዊ ጥናት ዋና አላማ በቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋዮች ላይ በመፍረድ ለማሳጣት የታሰበ ሳይሆን፤ እንዲያውም አገልጋዮችን ለመርዳትና ለማቅናት ነው። የእግዚአብሄር ቃል “የተገለጠ ዘለፋ ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል” (ምሳሌ 27፥5) እንደሚል፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚታዩትን መንፈሳዊ ያልሆኑ አሰራሮችና ልምምዶች፤ በግልፅነትና በተጠያቂነት በመዳሰስ ጠቃሚ አስተያየቶችን በመስጠት ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል በማመን መጠቆም የጥናቱ አላማ ሆነ።
 2. በክርስቶስ ኢየሱስ ባለኝ አርነት መሰረት፤ በመንፈሳዊ ህብረቶችና የቤተክርስቲያን የውስጥ አሰራር ችግሮች ላይ ያለኝን መንፈሳዊ መረዳትና አመለካከት እንደ አባልነቴ ሳይሆን እንደ አካልነቴ በማቅረብ ቤተክርስቲያንን መርዳት አላማዬ ብቻ ሳይሆን ግዴታዬም ስለሆነ ይህንን መወጣት የጥናቱ አላማ ሆነ፤
 3. ክርስቲያናዊ ተግባርና ሃላፊነቶች ውስጥ አንዱ የጠፋው እንዲመለስ፤ የተሰበረው እንዲጠገን ፤ የተበታተነው እንዲሰባሰብ ፤ ህብረት አንድነትና ፍቅር እንዲመጣ መርዳት ይህንን ግዴታዬንም መወጣት የጥናቱ አላማ ሆነ፤
 4. በህብረት ውስጥ መንፈሳዊ ፍሬዎች በማፍራት ላልዳኑት ወገኖች የደህንነትን መንገድ እንድናሳይ፤ ለእግዚአብሄር ክብር እንድንኖር፤ ተባርከንም ለበረከት እንድንሆን የተጠራን ሆኖ ሳለ ከዚህ በተቃራኒው እየኖር መገኘታችንን ማሳሰብ የጥናቱ ዋና አላማ ሆነ፤
 5. ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ተልዕኮዋን እንድትወጣ (ማቴ 28፤19-20) መንፈሳዊ መሪዎችን በሚያስፈልገው (በጎደለው) መርዳት/መጠቆም የጥናቱ አላማ ሆነ፤
 6. ቤተክርስቲያን በሃላፊነት (Responsibility) በተጠያቂነት (Accountability) እና በግልፅነት (Transparency) የሚመሩዋት መንፈሳዊ መሪዎች እንዲኖርዋት መፈለግ የጥናቱ አላማ ሆነ፤
 7. ቤተክርስቲያን አለማዋን ያወቀች፤ ተልእኮዋን ያልጣለች፤ እና ባለ ራእይ መንፈሳዊ ተቋም ሆና እንድትሰራ ከመፈለግ የዘለለ ምንም አይነት ሰውኛ አላማ የሌለኝ መሆኑን እገልፃለሁ።

ምዕራፍ-2- መንፈሳዊ ህብረት

2.1 ስጋዊነትና መንፈሳዊ ህብረት

ስጋዊነትና መንፈሳዊነት የሚጣረሱ ናቸው። ማለትም ስጋም በመንፈስ ላይ፤ መንፈስም በስጋ ላይ የሚነሳ በመሆኑ አብረው ሊሄዱ አይችሉም። ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥..እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።”(1ኛ ቆሮ 3፡1) በማለት የተናገረውም ስጋዊነትና መንፈሳዊነት ስለሚጣረሱ ነው። ስጋዊነት በቤተክርስቲያን ውስጥ በብዛት እንደሚገኝ የእግዚአብሄር ቃል የሚናገር ከሆነና፤ ክርስቲያን ነኝ የምንል በሙሉ መንፈሳውያን ሆነን ካልተገኘን፤ ክርስቲያን ነኝ ማለታችን ብቻ በቂና የደህንነታችን ማረጋገጫ ዋስትና፤ ወይም ማስረጃችን ሊሆነን አይችልም። ስለሆነም ክርስቲያን ነኝ፤ አገልጋይ ነኝ፤ መሪ ነኝ፤ ፓስተር ነኝ፤ ወንጌላዊ ነኝ፤ ዘማሪ ነኝ፤ ወዘተ ማለታችን፤ ራሳችንን በመካድ በእውነት መንፈሳዊ ሆነን ካልተገኘን በስተቀር፤ ማገልገላችንና ቤተክርስቲያን መመላለሳችን በራሱ መንፈሳዊ ሰዎች ስለማያደርገን፤ መንፈሳዊ ሰው ለመሆን፤ እንደ ቃሉ መኖር አለብን። ምክንያቱም ክርስትና ባለማወቅና ባለማስተዋል የምንመላለስበት የግብዝነት ህይወት አይደለምና። በመሆኑም ጊዜአችንንም መዋጀት ሲገባን፤ ጊዜው በተቃራኒው እየዋጀን፤ በከንቱ በመመላለስ የተወሰነልን ምድራዊ ዘመናችን ያለ ፍሬ በከንቱ እያረጀ ወደ መቃብር ከመውረዳችን በፊት ዛሬውኑ መንፈሳዊ ሰው ልንሆን ለመሆን ልንሰራና መዳናችንንም ልናረጋግጥ ይገባናል።

ክርስቲያን ከሆንን ላይቀር መንፈሳውያን ሰዎች ካልሆንን በስተቀር፤ በቤተክርስቲያን ብንመላለስም እንኳን ስጋውያን ሰዎች መሆናችን የማይቀር ነው። ምክንያቱም መንፈሳዊ ክርስቲያን ካልሆንን፤ ስጋዊ ክርስቲያን መሆናችን ወዲያው ነው። ሁለቱንም ካልሆን ደግሞ አለማውያን መሆናችን የግድ ነው። ከሶስቱ ውጭ ሌላ አይነት ሰው ወይም ባንድ ጊዜ ስጋዊም መንፈሳዊም ሰው ለመሆን ፈፅሞ አንችልም። ክርስቲያን ነኝ እያልን፤ በመንፈሳዊ ህብረታችን ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሄር መንፈስ ካልነገሰ፤ ወይም ደግሞ በመንፈሳዊ አሰራር እና በአመራር ካልተመራን በስተቀር፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስጋዊነትና ስጋዊ አመራር መንገሱ የግድ ነው። የለም እኛ መንፈሳውያን ሰዎች ነን የምንል ከሆነም፤ የመንፈሳዊነት ሰውነትና የመንፈሳዊ አመራር መገለጫዎቹ ሊታዩብን ወይም ሊገለጡብን ይገባል። እነዚህም መንፈሳዊ ፍሬዎች ናቸው። ለመንፈሳዊነት ውጤቱ መንፈሳዊ ፍሬዎች እንደሆነ ሁሉ፤ ለስጋዊነትም ውጤቶቹ የስጋ ፍሬዎች ናቸውና።

በአማኞች ህብረት፤ (በቤተክርስቲያን ውስጥ) መንፈሳዊ እድገት ቢኖር መንፈሳዊ አመራር ለመኖሩ ማስረጃ እንደሚሆን ሁሉ፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመንፈሳዊ ድርቀትና ውድቀትም ወይም ደግሞ ስጋዊነት፤ መገለጫው ስጋዊ ህይወትና ስጋዊ አመራር ነው። በዚህም ምክንያት ለሚመጣው የቤተክርስቲያን መሰነጣጠቅና የእግዚአብሄር ህዝብ መበታተን፤ ምዕመኑም የራሱ ድርሻ ቢኖረውም፤ በቅድሚያ ተጠያቂው ግን መንፈሳዊ አመራሩ ነው። አመራሩ እና አሰራሩ መንፈሳዊ ቢሆን ፍሬዎቹም የመንፈስ ፍሬዎች ይሆኑ ነበርና። አመራሩ ስጋዊ ከሆነ ደግሞ ፍሬዎቹም የስጋ ፍሬዎች  እነዚህም ጥል፤ ክርክር፤ ቅንአት፤ ቁጣ፤ አድመኝነትና በመጨረሻም ታላቁ የስጋ ስራ መለያየት (ገላትያ 5፤ 19-21) መሆናቸውን የሚናገሩት ሰዎች ወይም ከሳሻችን ሰይጣን ሳይሆን ራሱ ህያው ቃሉ ነው። ከዚህ አንፃር የእኛ መንፈሳዊ ህብረት በየትኛው አመራር ውስጥ ነው ያለው? በመንፈሳዊ? ወይስ በስጋዊ? ቢያንስ በዚህ ጥናት መሰረት የምንመላለስበት አመራር መንፈሳዊ ያለመሆኑን ያለንበት ሁኔታ ራሱ ገላጭ በመሆኑ፤ ሌላ ማስረጃ ወይም ጥናትም ላያስፈልገው ያችላል። ይኸውም በስጋዊ ስራዎቻችን ፍሬዎች ተውጠን በይሉኝታ፤ በግብዝነትና፤ ባለማስተዋል እየተማላለስን ለመሆኑን ማስረጃ የማያስፈልገው በግልፅ የሚታይ ነው። ውጤቱም ደግሞ እርስበርስ የተቃረንን፤ ስለምንገፋፋ የተራራቅንና፤ ፍቅር የሌለን ብቻ ሳይሆን የማንዋደድና እስከምንጠፋፋ ድረስ የምንከፋፋ መሆናችን ነው።

በመሆኑም ያካባቢያችንን ቤተክርስቲያን ምን አይነት አመራር እየመራት ነው ተብሎ ቢጠየቅ፤  “መንፈሳዊ አመራር”፤ አሊያም ደግሞ “ስጋዊ አመራር” ነው ማለት እንጂ፤ ሁለቱንም ባንድነት ነው ብንል፤ “…ብርሀን ከጨለማ ምንም ህብረት የለውም…” የሚለው ቃሉ ውሸተኛ ያደርገናል። ከሁለት ባንዱ (በስጋዊ ወይም በመንፈሳዊ) አመራር ካልተመራን ደግሞ በስውር በረቂቅ በአጋንንታዊ አሰራር እየተመራን ነው ወደሚባለው ጫፍ ሊወስደን እንደሚችል ማወቅ አለብን። በመሆኑም አመራሩ መንፈሳዊ ነውን? ወይስ ስጋዊ ነው? በማለት ከፍሬአችን ብቻ በመነሳት፤ ከግብዝነት ወጥተን፤ ራሳችንን በህያው ቃሉ በመመርመር፤ ስጋውያን ሆነን ከተገኘን በንስሃ በመመለስ እንደ ቃሉ መኖር የሚገባን ጊዜው አሁን ብቻ ነው። ይህንን ካደረግን መልካም ይሆንልናል፤ ቃሉ “በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።” (ገላትያ 5፡25) ይላልና። ከዚህ በመነሳት ባካባቢያችን ቤተክርስቲያን ተብለው በየቡድኑ የተሰየሙት ደርዘን የማይሞሉ ትንንሽ ደቃቃ ህብረቶች ሁሉ አስቀድሞ አመሰራረታቸው በራእይ በጥሪና በቤተክርስቲያን ተልእኮ መሰረት በመንፈሳዊ መንገድና አሰራር ነውን? ከሆነስ ስጋዊ ፍሬዎችን በገፍ ማፍራታቸው ከወዴት የመጣ ነው? ለዚህስ ተጠያቂው ማነው?  አመራሩ? ምእመኑ? ወይስ ሰይጣን? ወይስ ሌላ አለ?

2.2   ስራ የሌለው እምነት ቢኖረው

ቤት ማንን ይመስላል ቢባል ባለቤቱን እንደሚባለው ሁሉ፤ ቤተክርስቲያን የአማኞች ህብረት ማንን ትመስላለች ሲባልም ምዕመን ክርስቲያኑንና አመራሩን እንጂ ሌላ ማንንም ሊሆን አይችልም። ከዚህ አንፃር አማኞች በግልም ይሁን በህብረታችን ወይም በህይወታችን ከሚገለጠው የመንፈስ ወይም የስጋ ስራዎችና ፍሬዎች በመነሳት፤ የመንፈሳዊነት ወይም የስጋዊነት መገለጫ/መታወቂያ ወይም ቅፅል ስም እንበለው፤ አለን። ከዚህ ውጭ መንፈሳዊነት ወይም ስጋዊነት እንደዚሁ በማንም ላይ የሚለጠፍልን ስም አይደለም። ምክንያቱም ተግባራችን ወይም ምግባራችን ማንነታችንን ስለሚናገር (ስለሚገልፅ) የሆነውን የሚገለፅበት ስም ነው እንጂ እከሌ መንፈሳዊ ነው፤ እከሌ ደግሞ ስጋዊ ነው፤ ነች፤ በማለት ማንም ሊደልለንም ሆነ ይኽንን ይህንን ስም ሊያድለን የሚቻለው ነገር አይደለም።

በያዕቆብ መልእክት ላይ (“ወንድሞቼ ሆይ እምነት አለኝ የሚል ስራ ግን የሌለው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?”) (ያእቆብ፤ 1፤ 14) (“ስራ የሌለው እምነት ቢኖረው በራሱ የሞተ ነው።”) (ያእቆብ፤2፤16) የሚለው ቃል ከእምነታችን የተለየ ተግባር ቢኖረን የማይጠቅመንና የሞተ እንደሆነ በሚገባ ያስረዳናል። ከተግባራችን በላይ ሊገልፀን የሚችል በተግባር የሚታይ እምነት የሌለን መሆኑን ማወቅ አንድ መረዳት ሲሆን፤ በተጨማሪም ከእምነታችን የተለየ ተግባር የምንኖር ከሆነም፤ ራሳችንን በመመርመር እና በማስተዋል ለህይወት ለውጥ መነሳት መቻል ያስፈልገናል። ስጋውያንም፤ ሆኑ መንፈሳውያንም ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚገኙ መፅሀፍ ቅዱስ የሚናገር መሆኑን ካወቅንና ስጋውያን ሰዎች በቤተክርስቲያን ላይ ሊያመጡ የሚችሉትን የስጋ ስራዎችና ፍሬዎች ተፅዕኖ ከተገነዘብን፤ እንደ እግዚአብሄር ሰዎች በአማኞች ህብረታችን ውስጥ ከስጋ እስራት ነፃ በመውጣት በመንፈሳዊ ተሀድሶ በመታደስ፤ እርቅና ሰላምና ህብረት በማድረግ ለመኖር፤ የሚያቅተን ለምንድነው?

ምእመን እንሁን መጋቢ፤ ሽማግሌ፤ እንሁን አገልጋይ፤ የተበታተን እንሁን በየግሩፖች ውስጥ ያለን ሁላችን በክርስቶስ እውነተኛው ማንነታችን ቢፈተሽ፤ መሆን የምንችለው ወይ መንፈሳውያን ሰዎች ነው፤ አሊያም ደግሞ ስጋውያን ሰዎች ከመሆን ውጭ አናልፍም። ነገር ግን ስጋዊ ሰዎች አይደለንም፤ መንፈሳዊ ሰዎች ነን የምንል ከሆነም፤ መከራከር ሳያስፈልገን፤ በቤተክርስቲያን (በጥቃቅን ህብረቶች) ውስጥ እንደ ተራራ ተቆልለው፤ እስከመሰነጣጠቅና መበታተን ያደረሱንን የስጋ ስራዎቻችንና የስጋ ፍሬዎቻችንን ምን ልናደርጋቸው ነው? አጋላጮቻችን ሰዎች ወይም ከሳሹ ሰይጣን ሳይሆን በግልፅና በስውር የምንሰራው ስራዎቻችን ናቸውና። ሰው ስራውን ይመስላል ማለትም እንዲህ ነው። በእግዚአብሄር ታምነን ነገርግን መንፈሳዊ ፍሬዎችን ማፍራት ካልቻልን፤ እግዚአብሄርን እናውቃለን፤ እናምናለንም ማለታችን የማንኖርበት ወይም የማይታይ ከሆነ ጥቅሙ ምንድነው?። እግዚአብሄርን መፍራትና መኖሩን ማወቅንማ ሰይጣንም በደንብ ያውቀዋል፤ (“…እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል…።”) (ያዕቆብ 2፤19) እንደሚል በቃሉ የእኛ የስራ ድርሻ እግዚአብሄርን ማመንና ከእምነታችን የተነሳም መልካምንም ነገር ማድረግ ነው።

2.3 የአለም ብርሀን ናችሁ

ክርስቲያኖች መንፈሳዊም ሰው መሆን ካልቻልን የምንሆነው ስጋዊ ሰው ሲሆን፤ መንፈሳዊ  ወይም ስጋዊም ሰው መሆን ካልቻልን ደግሞ መሆን የምንችለው ፍጥረታዊ ሰው ወይም አለማዊ ሰው ብቻ መሆኑን ተደጋግሞ ተገልጦአል። በግል መንፈሳዊነት ቢሰማን እንኳን በእኛነታችንና (በግል ህይወት ዙሪያ) አልፎም በህብረታችን ውስጥ የሚገለጥ እንጂ ሊደበቅ የሚችል አይደለም። በመሆኑም መንፈሳዊነትን በግላችንም ይሁን በህብረታችን ውስጥ መገለጥ ካልቻለ መቼ ነው ኢየሱስ ክርስቶስን በመከተላችን ከጭለማ ወጥተን ለአለም ብርህን በመሆን እንደቃሉ የምንታየውና የእርሱም ተከታዮች መሆናችን የሚታወቀው? (“ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”) (ዮሃንስ 8፤12)

እንደዚሁም በተራራ ላይ እንዳለች ከተማስ ለሁሉም በግልፅ እየታየን መንፈሳዊ ፍሬዎችንም እያፈራን የምንገኘው በምድር ላይ መሆኑ ቀርቶ በሰማይ ላይ ይሆን እንዴ?? (“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።”) (ማቴዎስ 5፥14)  ደግሞም እንደቃሉ በርግጥ እኛ ለህይወት የሚሆን የህይወት ሽታ ነን ብለን በእውነት በራሳችንን እንተማመናለን? (“ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን።”)(2ኛ ቆሮንቶስ 2፥16) እንደ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነታችን እነዚህ ትእዛዛት በህይወታችን በግልም በህብረታችንም እየተገለፁ መንፈሳዊ ፍሬዎች አፍርተናልን ብለን እናምናለን?። በላንካስተር አካባቢ ከለፉት አምስት ጀምሮ የዚህ ተቃራኒው ሲደረግ ነው እኔ ያየሁት። የምመሰክረውም ያየሁትን ብቻ ነው፤ ይኸውም በጭለማ እየተመላለስን መሆኑን ነው። ለዚህም ከተግባራችን በላይ የሚመሰክርብን የለም፤ ይህም ስራችንም ነው።

2.4 ፍቅርቢኖራችሁ

ፍቅር ራስን በመካድ ብቻ የሚገኝ የምርጫ ጉዳይ ነው። ክርስትና ሀይማኖት ሳይሆን ህይወት ስለሆነ እርስ በራሳችን ቀርቶ ጠላታችንን እንድንወድ ታዘናል። የክርስትና ታላቁ ትእዛዝም ፍቅር ነው። ፍቅር ቢኖራችሁ በሚለው ብዙ ብዙ ተሰብኮበታል፤ ትምህርትም ተሰጥቶበታል። ነገርግን እንኳን ምዕመኑ አገልጋዩም፤ ፓስተሩም ራሱን በመካድ ፍቅር ሊወርሰውና ሊለወጥ ስላልቻለ፤ የዘመናችን ቤ/ክርስቲያን ያለፍቅር በከንቱ እየደከመች እተሰነጣጠቀች፤ እየተበታተነች፤ እንደ ኪዮስክ ሱቅ እዚህም እዚያም በየስርቻው ያለራእይና ያለጥሪ እየተከፈተች ፍሬ አልባ ጉዞዋን ከሰፈር እድር ባልተሻለ አደረጃጀትና አመራር እሄደች የማትሄድ ጉድ ሆናለች። ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱስ ስለፍቅር የሚያስተምረው ምንድን ነው?

 1. ፍቅርን ቢኖረን እውነኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት መሆናችንን (“እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”) (ዮሐ 13፤ 35)
 2. ሁሉም ነገር ቢኖረን ፍቅር ከሌለን ግን ከንቱ መሆናችንን፤ (“በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።”)
 3. እምነት ቢኖረን ፍቅር ከሌለን ዋጋቢስ መሆናችንን፤ (“ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።”)
 4. ፍቅር ድሆችን ከመመገብና ከመመፅወት በላይ መሆኑ (“ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።”
 5. ፍቅር ካለን ሁሉን የምንታገስ መሆኑን “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም አይታበይም፤”
 6. ፍቅርን የሚጥለው ሃይል የሌለ መሆኑን፤ (“ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።”
 7. ፍቅር ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑን (“እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።”
 8.  ትእዛት ሁሉ በፍቅር መጠቃለላቸውን (“እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።”) (2ኛ ዮሐንስ 1፥6)
 1. ይቀጥላል…….

የኢትዮጵያው የአባይ ግድብ እና የግብፅ የአስዋን ግድብ…

የኢትዮጵያው የአባይ ግድብ እና የግብፅ የአስዋን ግድብ…

(በዮሴፍ ወርቁ ደግፌ)

ታዋቂው ኢትዮጵያዊው ባለቅኔ የአለም ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን “…አባይ አባይ…የሀገር አድባር…የውጭ ሲሳይ…” እያለ ባለቅኔው ግዕዙን ወንዝ-አባይን ለሀገሩ ባዳ-ጠላት ለውጭ-ሲሳይ በረከ እንደሆነ ሲወቅሰው፤ የእኛንም “ስንፍና” በውስጠ ቅኔው ሸንቆጥ በማድረግ አልፎአል። ምክንያት? አባይን ለአገር ባዳ ለውጭ ሲሳይ ያደረገው አባይ ራሱ ሳይሆን እኛው በመሆናችን። በአለም ላይ በርዝመቱ አንደኛ የሆነውን ታላቁን የአባይን ወንዝ ብቸኛ ምንጭ አድርጎ የተገነባው የግብፅ ዋነኛ የኢኮኖሚ ዋልታና ምሰሶ የሆነውን የአስዋን ግድብ በተመለከተ፤ ግብፆች የከተቡትን አጭር የእንግሊዘኛ ፅሁፍ ከመረጃ መረባቸው ላይ ያገኘሁትን፤ ለግንዛቤ ያህልና እኛም ከምንሰራው ስራ አኳያ ለመገምገም እንዲረዳ ከዚህ ፅሁፍ ጋር አያይዤ አቅርቤዋለሁ። የአስዋን ግድብ ከተገደበና ለግብፅ መጠነ ሰፊ ጥቅም መስጠት ከጀመረ ከ45 አመታት በላይ እንደሞላው ታውቁ ነበርን? አዎን የግብፁ አባይ (የአስዋን ግድብ) ለግማሽ ምዕተ አመት ያህል ከፍተኛ ጥቅሞችን ለግብፅ ሲያበረክት፤ ኢትዮጵያ በተባለችው ምድር ላይ የሚኖረውና የአባይ ምንጭ የሆነው ጎስቋላና “ምስኪን” ህዝብ ግን መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚገልፀውና አብዛኛውም ህዝብም ለሁለት ሺ አመታትም በክርስትና እምነት እንደመቆየቱ መጠን እንደ እባብ ብልህ እንደ እርግብም የዋህ ሁን  በሚለው መጽሀፍ ቅዱሳዊ መርህ መሰረት እየኖረ ያልተገኘ ህዝብ ነው ። ርግብነቱ(?) አለን ብንል እንኳን፤ ብልህነታችን የታል? ፈጣሪ የሰጠንን ታላቅ የውሀ በረከት ስንጠቀምበትና ከርሃብ ስንወጣ ሳይሆን በርሀብ ምክንያት ፈጣሪን በማማረር  እየኖረን አለንና።

የሀገሪትዋ ረጅም ታሪክ በሙሉ የእርስ በርስ ጦርነት ታሪክ በመሆኑ ያፈራናቸው ጦረኛ መሪዎችንና በኢኮኖሚ የደቀቀ ህዝብን እንጂ ሀገር የሚያለማ ፈፅሞ አልነበረም። ስለሆነም በግብፅ ወይም በሌላው አለም ህዝብ ሳይሆን በራሳችን ችግር ምክንያት፤ አባይንም ይሁን ሌሎች በረከቶቻችንን ለመጠቀም ባለመቻላችን፤ ለዘመናት በመባከን ምክንያት የተራቆትን “ምስኪን” ህዝቦች ነን። በመሆኑም እስከዛሬም ድረስ በአለም ፊት ችጋራምና ተመፅዋች፤ መከረኛና ስደተኛ፤  ደግሞም የርሀብና የድርቅ ጥሩ ማስረጃዎች ሆነን እንገኛለን። በዘመናት የአዙሪት ጦርነት እኛ ስንተላለቅ፤ ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል እንዲሉ አባይንም ይሁን ሌሎች ወንዞቻችንን፤ የተፈጥሮ ድንግል መሬታችንን፤ የሰው ሀይል ሀብታችንን፤ ምንም ሳንጠቀምባቸው የግሎባላይዜሽን ዘመን ላይ ደርሰናል። አባይንም ቢሆን በደፈናው አባይ! አባይ! እያልን ወንዙን በዘፈን ስናሞካክሽ፤ እህል ሊሆን ባልቻለና ጥቅም ባልሰጠ ባዶ ታሪክ በሜዳ ላይ ለዘመናት ስንፎክርና ስናቅራራ፤  የበረከት ምንጮቻችን በከንቱ ባከኑ።  ከዚህ አንፃር ኢኮኖሚያዊ መመዘኛውን እንኳን ትተን በአስዋን ግድብ መመዘኛ ብቻ ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ብትወዳደር ቢያንስ 50 (ሀምሳ) አመታት ያህል በልማት ወደሁዋላ ቀርታለች።

የግብፅ ሲሳይ የሆነው “የአባይ ግድብ”፤ የአስዋን ግድብ ይዞታ ባጭሩ ስንመለከት፤ የአስዋን ግድብ አስር ቢሊዮን ኪሎዋት/ሰዓት በአመት የሚያመነጭ አቅም ያለው ሲሆን፤ ከ45 አመታት በፊት ግንባታው አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደ ፈጀ ተጠቅሶአል። የአስዋን ግድብ አንድ መቶ አስራ አንድ ሜትር ጥልቀት፤ አራት ኪሎ ሜትር የወርድ ስፋትና፤ ሃያ ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ርዝመት ያለው ሰው ሰራሽ ታላቅ ሀይቅና የውሀ ሀብት ክምችት የፈጠረላቸውም መሆኑን ግብፆች በኩራት ይገልፃሉ። በቀድሞው የግብፅ ፕሬዜዳንት ጋማል አብዱል ናስር ስም የተሰየመው የ“ናስር” ሰው ሰራሽ ሀይቅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጥቅሞች እየሰጠ እንደሚገኝና የአባይ ወንዝ ለግብፅ ብቻ እንደተፈጠረ፤ በዚህም ደግሞ እንደሚቀጥል የግብፆች ሀሳብ የትየለሌ ነው። ኢትዮጵያዊው አባይ ለግብፅ ከሚሰጣቸው ዋና ዋና ጥቅሞች ውስጥ አንዱ፤ በየአመቱ አርባ ሚሊዮን ቶን ደለል ለም አፈር ከኢትዮጵያ ምድር አግበስብሶ ለግብፅ ተፈጥሮአዊና ዘመናዊ የግብርና ልማት ከፍተኛ በረከት መስጠቱ ነው። በዚህም የሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችንን ክፍል የለም አፈር ደሀ አድርጎታል። ከዚህም የተነሳ ነው ግኡዝ የሆነው ወንዝ እንደ ባእድ ጠላት ተቆጥሮ፤ “አባይ ለሀገሩ ባእድ ጠላት ለውጭ ሲሳይ በረከት” የተባለውም። አባይ ለግብፅ ቢያንስ በሚከተሉት ስምንት የኢኮኖሚ መሰረቶች ማገልገሉን መረዳታችን ሳይሆን የሚጠቅመን፤ እኛስ? የሚል ተገቢ እልህና ቁጭት ሲያድርብንና ለመስራትም መነሳት ስንችል ብቻ ነው። አባይ ከብዙ በጥቂቱ ለግብፅ የሚከተሉትን ጥቅም እየሰጠ ነው። እኛስ?

 1. በሀይድሮ (የውሀ ሃይል) ኤሌክትሪክ ምንጭነት፤
 2.  የአሳ ሀብት ማስገሪያ (አሳ ማርቢያና መሰብሰቢያ) ሀይቅነት፤
 3. በውሀ ትራንስፖርትነትና የመዝናኛ አገልግሎት ሰጭነት፤
 4.  በዘመናዊ መስኖ ግብርና ልማት አገልግሎት፤
 5. በድንግል እና ለም አፈር ግብርና በረከት፤ (Organic and fertile Soil)
 6.  በምግብና በመጠጥ ውሀ አገልግሎት፤
 7. በግንባታና የተለያዩ ስራዎች አገልግሎት፤
 8.  በረሀማነትን የመቀነስ አገልግሎት ዋነኞቹ ናቸው።

መልካም ነው፤ እንኳንም አባይ ግብፅን ጠቀመ፤ አበለጠገም። ኢትዮጵያም በግብፅ ልማትና ብልጥግና አግባብ ያልሆነ ቅናት ቀንታ፤ ግብፅን በጦርነት ወርራ ልማትዋን ላውድም፤ አባይንም ለብቻዬ ልጠቀም አላለችም። ኢትዮጵያ ያለችው ነገር ቢኖር፤ ባጭር አገላለፅ የሚከተለውን ይመስለኛል። አንድ ቤተሰብ በቤቱ ውስጥ ምግብ አዘጋጅቶ ለመብላት፤ ጎረቤቱን ሄዶ ማስፈቀድ አያስፈልገውም ነው። ኢትዮጵያ አባይን በመገደብ የዘመናት ድሀ ህዝብዋን ለመጥቀም፤ የቅርብም ይሁን የሩቅ ጎረቤትዎችዋን ማስፈቀድ ፈፅሞ አይገባትም። ምናልባት ምግቡን አብረን እንብላ ብላ መጋበዝ ባህላችንም ነው። ይህንንም ደግሞ አድርጋለች። ለአባይ ምንጭ/መነሻ ያልሆነችው ግብፅ ይህን ያህል በአባይ የውሀ ሀብት የመጠቀም መብት ካገኘች፤ የአባይ ዋነኛ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ እጅግ ዘግይታም ቢሆን፤ የውሀ ሀብትዋን ዛሬ ልትጠቀምበት ስትሞክር፤ ግብፅ “እንዴት ተደርጎ?” በማለት መፎከርዋ ጎረቤት ጎረቤቱን ያንተን ቤት የማስተዳድረው እኔ ስለሆንኩ በቤትህ ውስጥ አዘጋጅተህ ለምትበላው ምግብ እኔን አስፈቅደኝ፤ አለዚያ ወዮልህ!ይመስላል የግብፅ አቀራረብ። እኔን የሚገርመኝና የሚያሳዝነኝ የግብፅ ማንኛውም አይነት ፉከራ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ የውሀ ሀብትዋን ለመጠቀም ከግብፅ አንፃር እንኳን ሲታይ አምሳ አመታትን ሙሉ ወደ ሁዋላ የመቅረትዋ ጉዳይ ብቻ ነው። ከዚህ አንጣር ኢትዮጵያ፤ ርሀብን እንደ ብልፅግና ቆጥራ፤ ዜጎችዋን በመከራና በእርዛት ለዘመናት በመፍጀት ከንቱነትዋን ያረጋገጠች አገር ስትሆን፤ ለውጭው አለም ግን ምቹና ታላቅ ሲሳይና በረከት የመሆንዋን እንቆቅልሽ በእፍረትም፤ በድፍረትም መናገር ያስፈልጋል። ምናልባት ትንሽ ወኔ ቢቀሰቅስብን።

ያለፈው አለፈ። ዛሬ ድንገት በመባነን ኢትዮጵያ አባይን ብትገነባና እንደተባለውም 6000 ያህል (ስድስት ሺ) ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ብታመነጭ ግብፅ ትጎዳ ይሆን? የማይመስል ነገር ለ….አትንገር፤ የሚባለው ተረት ግብፅ ውስጥ ላለመኖሩ አንጠይቅም። አካሄድዋ ያስታውቃልና። ምክንያቱም ግብፅ የውሃ እጥረት እንደማያጋጥማት የታወቀና በቅርቡም የአለም አቀፍ የኤክፐርቶችም ቡድንም ያረጋገጠው ጉዳይ ሆኖ ሳለ፤ የግብፅ ጫጫታ ከየት የመጣ ነው? ግብፅን ይህን ያህል ያሰጋት ከቶ ምንድን ይሆን? በዚህ ፅሁፍ አቅራቢ እምነት ግብፅ ላይ ሊፈጠርባት የማይችለው ምንም አይነት ችግር አይደለም ግብፅን ያሰጋት። ይልቁንም፤ ኢትዮጵያ ከአባይ ግንባታ በሁዋላ ሊኖራት የሚችለውን ኢኮኖሚዊ ጉልበት፤ በአፍሪካም ይሁን በአለም አቀፍ ደረጃ፤ ሊኖራት በሚችለው ፖለቲካዊና ማህበራዊ እንዲሁም ዲፖሎማሲያዊ ተሰሚነቶችና ጫናዎች የተነሳ ግብፅ አስቀድማ ስጋት ገብቶአት እንደሆነ ነው’ንጂ ሌላ በቂ ምክንያት የላትም። እንዲያውም ግብፅንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ ኢትዮጵያ እንምትሰራ ነው የሚታመነው፤  ይኸውም ቢያንስ 1ኛ/ ሐይድሮ ኤለክትሪክ በማቅረብ/በመሸጥ 2ኛ/ በአፈር ደለል እየተሞላ የሚያስቸግራትን የአስዋን ግድብዋን ንጡህ ውሀ በመላክ ናቸው። ዝርዝሩን ለውሀው ባለሙያዎቹ እተወዋለሁ።

ወደእኛ ጉዳይ ስመጣ ግን፤ ኢትዮጵያ ሀገሬ! ህዝባችን! ኢትዮጵያ! ወዘተ እያልን የምንቆጭ ሁሉ፤ የአባይ ጉዳይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ጂኦ-ፖለቲካዊ እንደሆነና ከእኛ አልፎ የሰሜንና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትንና እንዲሁም በሌሎች ሩቅ ሀገራት ላይም ትልቅ ተፅእኖ እንዳለው ማስተዋል የመጀመሪያው ታላቅ መረዳት ነው። በዚህም የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚያጎላ ብቻ ሳይሆን ትልቅ ሁለገብ ጠቀሜታ የሚያመጣላትም መሆኑን መረዳት ሁለተኛው ታላቅ ግንዛቤ ይሆናል። ደግሞም አባይን እንዲህ  አድረገን እንጠቀምበት ብሎ ለመስራት መነሳት ሶስተኛውና ከሁሉ የሚልቀው ግንዛቤ እና ስራ ነው። በመሆኑም የውስጥና የጋራ ችግራችንን  ወይም አለመግባባታችንን በጋራ በመፍታት ለአባይ ጉዳይ በህብረት ካልተነሳን በስተቀር፤ በግሎባላይዜሽን ዘመን ላይም ደርሰን እያለ፤ እንደሌላው ህዝብ እያሰብን የምንኖር ሰዎች ለመሆናችን ጥርጣሬ ብቻ ሳይሆን፤ በርግጥ የሰብእና ጉድለት የሌለብን ህዝቦች ለመሆናችን በሚገባ መፈተሽ ያለበን ይመስለኛል።ይኸውም ህዝባችንን ከሺ አመታት ድንቁርናና ርሀብ ከማውጣት ይልቅ ምናልባት የግል ስምና የፖለቲካ ዝና ወይም የግል ጥቅም በልጦብን፤ በታሪካችን እንደተለመደው እርስ በርስ መቆራቆዝ አሁንም ቢቀጥል፤ ሌላው በእኛ ለመጠቀምና የእኛን ሀብት እየበላ ለመኖር የሚፈልግ ሁሉ የምንጨራረስበትን መሳሪያ ያቀብለናል። በቅድሚያ እዚህ ላይ አንባቢ መረዳት ያለባችሁ ነገር ቢኖር፤ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የውጭ እርዳታ ለአባይ ግድብ ስራ እንዳታገኝ ግብፅ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ድል ማግኘትዋን ልብ በሉ። ከዚህ የተነሳ ኢትዮጵያ በራሴ ወጭ ግድቡን እሰራለሁ ለማለት ተገድዳ እየተንቀሳቀሰች ነው።  የሰሞኑን የግብፅ ፕሬዜዳንት የካቢኔ አበላትና የፖለቲካ መሪዎች ያደረጉትን ስብሰባ በተለያዩ ቻናሎች ላይ ተመልክተን ከሆነ የሚያስገርምና የማስፈራራት ውይይት ማድረጋቸው፤ ከላይ ያለውን ሀሳቤን  የሚያጠናክር ነው። ከውይታቸው ውስጥ የሚከተለው ባጭሩ ይገኝበታል። “የአዲስ አበባውን  ኤምባሲያችንን ዘግተን በስለላ ስራ በመሰማራት የውስጥ ጉዳያቸው ያልተረጋጋ ስለሆነ ጣልቃ እየገባን ኢትዮጵያን ማተራመስ አለብን”፤ “ከኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ከ35% በላይ የሆነውን ህዝብ የሚወከለው ተቃዋሚ ሀይል የሆነውን ኦነግ በመጠቀም ግድቡ እንዳይሰራ በሀይል ማደናቀፍ አለብን”፤ “ኤርትራን ጅቡቲንና ሶማሊያን የሚያካትት ትሪያንግል አክሲስ ሰርተን ኢትዮጵያን ማጥቃትና ማዳከም አለብን”፤ “ሁሉንም አማራጮች አድርገን ካቃተን ደግሞ ሀይል በመጠቀም ግድቡን ማውደም አለብን” ወዘተ የመሳሰሉትን ጠንካራና ነገርግን ያልተጠበቁ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ብስለት የሌላቸው ግልብ ሀሳቦችን ሲወያዩ  ነበር የተስተዋሉት። (“ኢትዮጵያ ማለት የግብፅ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን እንኳን ዘወትር የሚያሸንፋት ሀገር ነች” ወዘተ በማለት ተዛማችነት የሌለው ሀሳብ ሁሉ በማድረግ ሲወያዩ ነበር) እንዲያውም  ፕሬዜዳንት ሙርሲ ስለምትሰጡት ሀሳብ ጥንቃቄ አድርጉ፤ ውይይታችን በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ነውና፤ በማለት ባያቋርጡአቸው ኖሮ፤ የግብፅ ባለስልጣናትን የከፋና ጥበብ የጎደለው ውይይት በተጨማሪ በተመለከትን ነበር።

በሌላ በኩል ወደ ስምምነት ከሚያመጡን ወቅታዊ ታላላቅ አባባሎች ውስጥ አንዱ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሆኑት በዶ/ር መረራ ጉዲና የተጠቀሰው ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፤”የአገራችን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለውጭ ሃይል መጠቀሚያ ለመሆን ይዘጋጃሉ የሚል ግምት የለኝም…አባይን በሚመለከት ከኢህአዴግ ያነሰ የአገር ስሜት አላቸው ብዬ አልገምትም” አባባላቸው ከፖለቲካ ልዩነት በፊት የሀገር ልማት ይቅደም የሚልና፤  ለሀገሪትዋም የሚበጅ የአመለካከት ታላቅ ለውጥ የተደረገበት ፖሊሲ ነው። ከሌሎችም ይህ ይጠበቃል። ስለሆነም ከእኔ በላይ አዋቂና ለሀገር አሳቢ ለአሳር ነው ወይም ከእኛ ወዲያ ፉጨት አፍ ለማሞጥሞጥ ነው ከሚባለው ሀገርኛ ጎጂ አባባል ነፃ በመውጣት የመቻቻልና የመደራደር ተስማምቶም ለመስራት የእውቀትን ክህሎት ብቻ ሳይሆን፤ በተግባር እንነሳና አባይን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም በርካታ የልማት ስራዎችን እንስራ። “የእኔ መንገድ ብቻ ትክክል ነው” (my way is the high way) የሚለው ያረጀና ያፈጀ በግሎባላይዜሽን ዘመን የማይሰራ የግልና የቡድን አስተሳሰብ “ የጋራ ውሳኔያችን ትክክል ነው” በሚለው መተካት ያለበት አሁኑኑ ነው። ስለሆነም ከአባይ ግድብ ግንባታ በፊት ሰብአዊ መብት ይከበር! ዲሞክራሲና ፍትህ ይገንባ !!! ” የምንልም ሰዎችም እንሁን፤ ወይሞ ደግሞ ታላቁን ጠላት ድህነትን አስቀድመን እንዋጋ !!! ዲሞክራሲ እህል ከጠገብን በሁዋላ !!! ” የምንል ሁላችን፤ የአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ያንድ ወገን (ግሩፕ) ወይም ፓርቲ ጉዳይ ሳይሆን፤ የሁላችንም የጋራ ጉዳይ ነውና፤ በአባይ ጉዳይ ማንም ማንንም እንዳያገልል ሁላችንም እንጠንቀቅ አጥርተንም እንመልከት አርቀንም ለትውልድ እናስብ ዘንድ ይገባል። ስለሆነም ፖለቲከኛ ነኝ የምንል ሁሉ የግል አጀንዳንና በተለይም እርስ በርስ ጥላቻንና ክፋትን በማስወገድ ለሀገር ልማትና ለህዝብ አንድነት ሲባል በአባይ ግንባታ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ብሄራዊ መግባባትን በመፍጠር  በልዩነትም ቢሆን ባብላጫ ድምፅ ተስማምተን የሚገባውን አስቀድመን እንድናደርግ። የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቱ ከዚያ በሁዋላ ይምጣ። ከፖለቲካ የበላይነት የሀገር ልማትና የህዝብ አንድነት ይቅደም። የልብ አይኖቻችንን እግዚአብሄር ያብራልን የሚል ፀሎት ብቻውን የእኛ ፈቃደኝነት ከሌለበት ከምኞታችን ያለፈ ዋጋ የሌለው መሆኑን እንወቅ። ያለ ሰው ፈቃድና መታዘዝ እግዚአብሄር ሊረዳ አይችልምና። ህብረትና አንድነት፤ ሰላምና ልማት፤ ለምድራችን የሚመጣው በእኛ ፍላጎት፤ ፈቃድና መታዘዝ ብቻ ነውና። አሜን ይሁንልን !!! ስለአስዋን ግድባቸው ግብፆች በእንግሊዝኛ የከተቡት የሚከተለው ነው።

Aswan High Dam, Araic Al-Sadd al-ʿĀlī, rockfill dam across the Nile River, at Aswan, Egypt, completed in 1970 (and formally inaugurated in January 1971) at a cost of about $1 billion. The dam, 364 feet (111 meters) high, with a crest length of 12,562 feet (3,830 meters) and a volume of 57,940,000 cubic yards (44,300,000 cubic meters), impounds a reservoir, Lake Nasser, that has a gross capacity of 5.97 trillion cubic feet (169 billion cubic meters). Of the Nile’s total annual discharge, some 2.6 trillion cubic feet (74 billion cubic meters) of water have been allocated by treaty between Egypt and Sudan, with about 1.96 trillion cubic feet (55.5 billion cubic meters) apportioned to Egypt and the remainder to Sudan. Lake Nasser backs up the Nile about 200 miles (320 km) in Egypt and almost 100 miles (160 km) farther upstream (south) in Sudan; creation of the reservoir necessitated the costly relocation of the ancient Egyptian temple complex of Abu Simbel, which would otherwise have been submerged. Ninety thousand Egyptian fellahin (peasants) and Sudanese Nubian nomads had to be relocated. Fifty thousand Egyptians were transported to the Kawm Umbū valley, 30 miles (50 km) north of Aswan, to form a new agricultural zone called Nubaria, and most of the Sudanese were resettled around Khashm al-Qirbah, Sudan. The Aswan High Dam yields enormous benefits to the economy of Egypt.

For the first time in history, the annual Nile flood can be controlled by man. The dam impounds the flood waters, releasing them when needed to maximize their utility on irrigated land, to water hundreds of thousands of new acres, to improve navigation both above and below Aswān, and to generate enormous amounts of electric power (the dam’s 12 turbines can generate 10 billion kilowatt-hours annually). The reservoir, which has a depth of 300 feet (90 meters) and averages 14 miles (22 km) in width, supports a fishing industry. The Aswan High Dam has produced several negative side effects, however, chief of which is a gradual decrease in the fertility and hence the productivity of Egypt’s riverside agricultural lands. This is because of the dam’s complete control of the Nile’s annual flooding. Much of the flood and its load of rich fertilizing silt is now impounded in reservoirs and canals; the silt is thus no longer deposited by the Nile’s rising waters on farmlands. Egypt’s annual application of about 1 million tons of artificial fertilizers is an inadequate substitute for the 40 million tons of silt formerly deposited annually by the Nile flood. Completed in 1902, with its crest raised in 1912 and 1933, an earlier dam 4 miles (6 km) downstream from the Aswan High Dam holds back about 174.2 billion cubic feet (4.9 billion cubic meters) of water from the tail of the Nile flood in the late autumn. Once one of the largest dams in the world, it is 7,027 feet (2,142 meters) long and is pierced by 180 sluices that formerly passed the whole Nile flood, with its heavy load of silt.

የኢህአፓ ትውልድ ሌጋሲ እና መጭው ዘመን

ይህ ዳሰሳዊ ፅሁፍ ሶስት የኢትዮጵያ ትውልዶች ለ50 አመታት (ግማሽ ምእተ አመት) ያህል ያደረጉትን ፖለቲካዊ ትግልና ጭንገፋ፤ ውድቀት፥ ድንዛዜና ተስፋ መቁረጥ፥ ደግሞም ማንሰራራትና ተስፋ መለምለም (ትንሳኤ) ዙሪያ እያጠነጠነ፤ በዚያች ምድር የፖለቲካ ሀሁ- መደራደር-መቻቻልና-በልዩነትም አብሮ መስራት (ዲሞክራሲ) እስከተቻለ ድረስ፤ በመጭው የቅርብ ዘመናት በተለይም ሶስተኛው ትውልድ ብዬ በምጠራው አማካይነት ህዝቡ በጣም ርቆ በተሰቀለ የተስፋ-ዳቦ ከመኖር ወጥቶ ትንሳኤ በእጁና በደጁ እንደሆነ ይሞግታል።

የመጀመሪያው ትውልድ የምለው በንጉስ ሀይለስላሴ አገዛዝ የመውደቂያ ዘመን ላይ በወጣትነት የእድሜ ክልል ውስጥ የነበረውን ሲሆን፤ ትውልዱ በፖለቲካው-በኢኮኖሚው-በማህበራዊውና በሃይማኖቱም ሳይቀር ሀገሪቱን በ”መምራት” ታላቅ ሚና የነበረው እነ አቶ መለስ ዜናዊ የሚጠቃለሉበት የኢህአፓ ትውልድ ነው። ይህ ትውልድ በእውቀት ክህሎቱ የማይታማ ጠንካራ ትውልድ የነበረ ቢሆንም፤ የግራ-ዘመም ፖለቲካ (Communist Ideology) በእጅጉ ስለተጠናወተው የፖለቲካ ስልጣን ከአመጽ ትግል በስተቀር በዲሞክራሲ መንገድ ይገኛል ብሎ የማያምን ትውልድ ነበር። በመሆኑም የዲሞክራሲ እምብርት የሆነውን ፖለቲካዊ መደራደር-መቻቻልና-አብሮ መስራት ፈጽሞ ስላልሆነለት በጥይት የተጨራረሰ ሲሆን ከዚያ የተረፈው ጥቂት አባላቱም ህወሀት-ኢህአዴግን ጨምሮ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን እዚህም-እዚያም ቢመሰርትም “ያደቆነ-ሰይጣን ሳያቀስስ አይለቅም” እንዲሉ በግሎባላይዜሽን ዘመንም ላይ የዲሞክራሲ ሀሁ ጠፍቶት መደራደር-መቻቻልና-በልዩነትም አብሮ መስራት አቅቶት፥ እርስበርሱ እየተጣላ-እየተሰነጣጠቀ-እየተፈረካከሰ ወርቃማ ፖለቲካዊ ዘመኑን በከንቱ እየጨረሰ ይገኛል። ስለሆነም ይህ ትውልድ ሀገሪትዋን በመምራት ሳይሆን በመንዳት የሚታወቅ ትውልድ ለመሆኑ ማስረጃው ይህ ዛሬ የሚታየው ፍሬው ነው። ስር የሰደደው እርስ በርስ መናቆርና-ጥላቻ-ክፋትና-ቂምበቀል-በግፍና በጭካኔ መጠፋፋት የሆነው የዚህ ትውልድ ፖለቲካዊ ፖሊሲ በማንኛውም መንገድ ፍሬ አልባ አድርጎናል። በመሆኑም ዛሬ ከሚታየው ፖለቲካዊ ፍሬዎች ተነስተን የትውልዱን መገለጫዎች እንዘርዝር ብንል፤ ከላይ ከተጠቀሰው ፍሬ አልባነት በስተቀር ሌላ መልካም ነገር መኖሩን የምታሳዩን ወገኖች ካላችሁ አሳዩን። በመሆኑም በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እምነት ትውልዱም-ሀገሪትዋ ሳያልፍላቸው፤ ለትውልዱ የተወሰነለት ዘመን በማለቁ ትውልዱ የመጨረሻ ፖለቲካው ሞት ፍፃሜው ላይ መድረሱን ማረጋገጫው የአቶ መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት ሳይሆን ውጤት (ፍሬው) ነው።

ሁለተኛው ትውልድ ህወሃት-ኢህአዴግ ስልጣን በያዘበት ዘመን በወጣትነት የእድሜ ክልል ውስጥ የነበረውን የሚመለከት ሲሆን፤ ይህ ትውልድ ከእርሱ በፊት በነበረው የኢህአፓ ትውልድና ከእርሱ በሁዋላ በመጣው አዲስ ትውልድ (3ኛ ትውልድ) መሀከል እንደ ሳንዲዊች ተጨፍልቆ፤ ፖለቲካዊ ድንዛዜና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በመግባቱ በሀገሪቱ ፋይዳ ያለው ፖለቲካዊ ተጽእኖ ለማምጣት የሚፍጨረጨር ትውልድ ነው። በርካታ ሰዎች እንደሚያምኑትም የዚህ ትውልድ ድንዛዜ ዋናው ምክንያት የኢህአፓ ትውልድ ላይ ወታደራዊው አገዛዝ ያደረሰው ግፍ ሰቆቃና ግድያ የተነሳ ሁለተኛው ትውልድ “ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቁ ” እንዲል አድርጎት ነው’ንጂ … የሚሉ ሰዎች አሉ። እንደዚሁም ታዋቂው ኢትዮጵያዊ የአለም ሎሬት ባለቅኔ ጸጋዬ ገብረመድህን ባንድ ወቅት ይህንን ትውልድ “ጫታም ትውልድ” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን ጥቂት ሰዎችም የባለቅኔው ጸጋዬን አስተያየት ተጋርተዋል። አንድን ትውልድ ጠቅልሎ “ጫታም ትውልድ” በማለት መሰየም አግባብ ስላልሆነ ቅሬታ ከተሰማቸው ውስጥ አንዱ ነኝ። ምናልባት ታላቁ ሰው አቶ ጸጋዬ ስለሆኑ ነው እንጂ፤ አንድ ፖለቲከኛ ቢናገረው ኖሮ እንደ ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ወዲያውኑ ፖለቲካዊ ሞት ይሞት ነበር። በአጠቃላይ የዚህን ትውልድ ሞራልና ወኔ የሰለበው፤ ከእርሱ የቀደመው ትውልድ ፖለቲካዊ ፍሬ-አልባነት ብቻ ሳይሆን ትውልዱ በዋናነት በሁለት ትውልዶች መሀከል በአደገኛ ሁኔታ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ በመጨፍለቁ፤ ፖለቲካዊ አቅምም ሆነ ልምድ በማጣቱ፤ ተሳስሮና ተሸብቦ እየኖረ መሆኑን ለመናገር ማስረጃ መቁጠር አያሻም። ይሁንና ይህንን ትውልድ ወደ ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ ፖለቲካዊ ትግል ለማምጣት ቀላል ባይሆንም፥ ተስፋ የሚያስቆርጥ ግን አይደለም።

ሶስተኛው ትውልድ በህወሀት-ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመን ወቅት የተወለደውን ትውልድ የሚያጠቃልል ነው። ይህ ትውልድ አያቶቹና አባቶቹ ሊሆኑ ከሚችሉት ከቀደሙት ከሁለቱ ትውልዶች እጅግ በተሻለ ሁኔታ ውስጥ ለመኖር ጊዜ የታደገው ትውልድ ነው። ይኸውም የቴክኖሎጂ በፈጣን ሁኔታ መምጠቅ፤ የኢንፎርሜሽን (መረጃ) እና እውቀት በቀላሉ መሰራጨት፤ አለም በሁሉም አቅጣጫ በግሎባላይዜሽን አንዲት መንደር መሆንዋ ወዘተ የተነሳ፤ ትውልዱ ከጠባብ አስተሳሰብ የተላቀቀ፤ ከሰፈሩ ወጥቶ አለም አቀፋዊ አስተሳሰብን ያዳበረ፤ “ሰጥቶ በመቀበል”-“አድርግልኝ ላድርግልህ”-“Tit-for-Tat” እንደሚሉት መርህ አይነት የሚኖር፤ “ጀብደኛነት” – “ግትርነት” – “ትእቢት” – “ጠባብነትና ትምክህተኛነት” የለሌለበት፤ ጉልበቱን ሳይሆን አእምሮውን የሚጠቀም ብልህና ብሩህ ትውልድ ነው። ባጠቃላይ ይህ ትውልድ መደራደርንና መቻቻልን፤ መግባባትን ለጋራ ጥቅም አብሮ መስራት፤ የሊብራል ዲሞክራሲ መርሆች ትልቅ እሴቱ በማደርግ የሚሰራ ትውልድ ነው። ከዚህ በመነሳት ዳሰሳዊ ፅሁፉ አጠቃላይ መሰረታዊ አላማዎች ሶስት ናቸው። እነዚህም፤-

ከንጉስ ሃይለስላሴ የጭቆና አገዛዝና ከኮረኔል መንግስቱ ሀይለማርያም አንባገነናዊ አገዛዝ ከመነጨው ጥይት እና እስራት ያመለጠው የኢህአፓና የመለስ ትውልድ፤ በምድር ላይ የተወሰነለት የህይወት ዘመን በመገባደዱ ምክንያት፤ የትውልዱ ቁጥር እየመነመነ ለመገኘቱ፤ ማስረጃው፤ የአቶ መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት ሳይሆን፤ እንደዋዛ የተቃጠሉት እጅግ ውድና ወርቃማ ዘመናት ናቸው። በ1960ዎቹ ውስጥ እድሜው በትንሹ 18 አመት የሞላው የዚያ ዘመን አፍላ ወጣት፤ ከበርካታ ፍሬ አልባ ትግል በሁዋላ፤ በአሁኑ ወቅት በህይወት የሚኖር ጥሩ ጡረተኛ በመሆን ብቻ ነው። ምናልባትም መልካም ሰው ከሆነ ከአማካሪነት ያላለፈ ፖሊቲካዊ ጫና በማድረግ ከዚህ በሁዋላ ሀገር የመምራት አቅም የለውም። ስለዚህም የዚያ “ሀያል ትውልድ” አባል የሆነና ባሁኑ ሰአት በህይወት ያለ ሰው ማድረግ ያለባት አንድ ብቸኛና ዋና ነገር ቢኖር፤ የመጨረሻ እድል በመጠቀም ያለፉትን ፖለቲካዊ ስህተቶቹንና ድክመቶቹን፤ ከጥንካሬው ጋር እያዋዛ በመገምገም፤ ለቀጣዩ ትውልድ በግልፅ በማስተማር፤ የትውልድ ርክክብ ሃላፊነቱንና ግዴታውን መወጣት ብቻ ነው። ይህ እንዴት ሊሆን ይቻላል? የትውልዱ አባላት በያሉበት ስፍራ ህዝብን ለዚህ አላማ አጠቃላይ ስብሰባ መጥራትና ማወያየት፤ በሴል አሰራር እና የመረጃ መረብ በመጠቀም በሁሉ ስፍራ ርክክቦሹን ማሰራጨት፤ ከተቻለም መፅሀፍ በመፃፍ በማስተላለፍ ናቸው። በመሆኑም ይህ ትውልድ ርክክብ እንዲያደርግ ማሳሰብ የመጀመሪያው የዚህ ፅሁፍ አንደኛው አላማ ነው።

ሁለተኛው ትውልድ ነጮቹ የሳንዲዊች ትውልድ እንሚሉት አይነት ከየትኛውም ያገራችን ትውልድ በበለጠ፤ በወላጆቹና በልጆቹ መሃከል በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንደ ኑግ ተወቅጦ ያደገና በመጨፍለቁ ብዛት ፖለቲካዊ ድንዛዜ ውስጥ የገባ ትውልድ ነው። በተለይ በዚህ ትውልድ ላይ የደረሰበት የህይወት ኑሮ ክብደት ጫና፤ ምንም እንኳን በሞትና በህይወት መሀከል የመኖር ያህል ቢሰማውም፤ ጥቂት የመስራት ዘመናትና አቅምም ስላለው፤ ማድረግ ያለበት ትላላቅ ቁምነገሮች የሚከተሉት መሆናቸውን ማሳሰብ የዚህ ፅሁፍ ሁለተኛው አላማ ነው። እነዚህም፦

1ኛ/ ሁለተኛው የኢህአፓ ትውልድ ላይ የነበረው የግራ ዘመም የፖለቲካ አስተሳሰብ ሀገሪትዋን ያልጠቀማት መሆኑን በመረዳት፤ ሰላምን በመፍጠር በጋራ የመኖርና የመስራት ጥበብን ዋነኛ እሴቶች በማድረግ በሊብራል ዴሞክራሲ የፖለቲካ አይዲዮሎጂ መርህ መስራት ይኖርበታል ።

2ኛ/ካለፈው ትውልድ እርስበርስ መናቆርና መጣላት ብሎም እርሰበርስ መጠፋፋት ፖሊሲዎች በመማር፤ ለአዲሱ ትውልድ አዲስ የመደራደርና የመቻቻል ፖለቲካ ማስረጽ ያለበትም ይህ ትውልድ መሆኑን በመወቅ መስራት መጀምር ያለበት ኣሁኑኑ መሆኑን ማሳሰብ ሌላው ነው።

ሶስተኛው ትውልድ ከሁለቱም ትውልዶች በተሻለና በላቀ ደረጃ ቀልጣፋ የሆኑ በርካታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ ትውልድ ሲሆን፤ ከዚህ አንፃር ከቀደሙት ሁለት ትውልዶች እጅግ በበለጠ ሁኔታ፤ የኑሮ ድካምና ጥረት የቀነሰለት፤ ጉልበትና ጥይት ከመጠቀም ይልቅ፤ አእምሮውንና አንደበቱን የሚጠቀም፤ በድርድር፤ በመቻቻልና አብሮ በመስራት የሚያምን፤ ገርና ለስላሳ ነገርግን ፈጣንና ጠንቃቃ ትውልድ ነው። ትውልዱ ይልቁንም በአለምአቀፋዊ (Globalization) ተፅእኖ ውስጥ የሚኖር እንደመሆኑ፤ ከጠባብነት፤ ከእኔነትና ከግትርነት ከሚመነጩና የኢትዮጵያዊ ብቻ ከሚመስሉ የሰብእና በሽታዎች (personality disorders) የነፃ ይሆናል። እንደዚሁም ከሰፈሩ የወጣ አለማቀፋዊ አስተሳሰብ ያዳበረ ትውልድ ነው። ይሁንና ይህ ትውልድ የተሟላና የጠራ እይታ እንዲኖረው በማስፈለጉ፤ ያለፉት ትውልዶች ከሰሩት ታላላቅ ፖለቲካዊና ሀገራዊ ስህተቶችም ይሁን፤ መልካም ስራዎች ጭምር ልምድ በመውሰድ የሚመራባቸውን ራዕይ፤ መርሆች፤ ፖሊሲዎች፤ አላማዎችና ግቦች መንደፍ ያለበት ጊዜው አሁን ስለሆነ፤ የዚህ ፅሁፍ ሶስተኛው አላማ፤ ይህ ትውልድ ለዚህ እንዲዘጋጅ ማሳሰብና መርዳት ናቸው።

እንደ መነሻ
እጅግ በጣም የቆዩትን የነገስታትና የሰፈር ገዚዎች አገዛዝ ታሪክ ትተን ከሀምሳ አመታት ወዲህ ያሉትን የገዚዎቻችንን ታሪክ ብቻ ብንመልከት ብዙ ህፀፅዎችን ማውጣት እንችላለን። ታሪካቸው በጥቂት አስርት አመታት ብቻ የሚቆጠር በርካታ ሃገራት፤ ህዝባቸውን ከርሃብና ከድንቁርናና ከእርዛት ባጭር ጊዜ ውስጥ ነፃ ማውጣት ብቻ ሳይሆን፤ በስልጣኔ በመዝመም ላይ ናቸው። በሺ አመታት የሚቆጠር የታሪክ ባለቤትነት ከሚጠቀስላችውና፤ ቀደምት የስልጣኔ አሻራ እምብርት ከሆኑት ጥቂት የአለም ሃገራት መካከል፤ አንደኛዋና ዋነኛዋ የሆነችው ታላቋ ኢትዮጵያ ሀገራችን ግን “ፅድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ” እንዲሉ፤ በስልጣኔ መምጠቅ ቀርቶ፤ ህዝብዋ ዛሬም ድረስ ራሱን ለመመገብ እንኳን ያልቻለ፤ በአለም ፊት እጅግ ጎስቋላ፤ ረሀብተኛ፤ የታረዘ፤ ተመፅዋችና፤ ስደተኛ ህዝብ ነው። ስለዚህም የሀገራችን ሕዝብ በርሀብ፤ በእርዛት፤ በልመና፤ በድንቁርና፤ በእርስበርስ ጦርነት እንዲሁም በከፋ ስደተኛነት፤ በሞትና በህይወት መካከል መኖሩ በአለም ህዝብ ፊት በስፋት ይታወቃል። ራቅ ያሉትን ንጉሳዊ የግፍ አገዛዝ ዘመናት ታሪክ እንኳን ትተን፤ የቅርቦቹን የአገዛዝ ዘመኖችን በጥቂቱ ብንፈትሽ፤ ጭቆናና ርሀብ፤ ጦርነትና ስደት፤ መከራና ሞት ብቻ የነገሰባችው ግማሽ ምእተ አመት እንደዋዛ ማለፉቸውን አስተውለን ይሆን? ህዝባችን እንደ ገና ዳቦ ከላይም ከታችም የጉስቁልና እሳት እየነደደበት፤ ሳይኖር-የኖረ፤ ሳይበላ-የበላ እየመሰለ፤ በቁሙ-እየሞተ፤ ያለፈበቸው፤ እንደነዚህ ያሉ ዘመናት፤ በታሪካችን ውስጥ  የሚገኝ አይመስለኝም።

ከአርባ አመታት ወዲህ ነፃነታቸውን ያገኙት የአፍሪካ ሀገሮች እንኳን ቢያንስ በምግብ እህል ራሳቸውን ችለው ሲያድሩ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን፤ ዛሬም ድረስ ዳቦ ወይም እህል ሆኖ ከረሀብ ሊያወጣው ባልቻለ የሺ አመታት ታሪክ ውስጥ ተደብቆ፤ በከንቱም እየማሰነ፤ ከውጭ በቅኝ ሊገዙት የመጡ ባእዳን በሌሉበት፤ ነፃ ምድሩ ላይ እየኖረ፤ ከንቱና ፍሬ አልባ ዘመናት ሲቆጥር፤ እነሆ ግማሽ ምዕተ አመት አለፈው። ሶስተኛውን ሚሊኒየምን ለመረከብ በታሪክ አጋጣሚ “እድለኛ” ሆነው የታደሙት ሟቹ ጠ/ሚር አቶ መለስ ዜናዊ ሚሊኒየሙን ከተቀበሉበት ታሪካዊ አጋጣሚዎች አንዱ መካከል፤ የልመና እርዳታ እህል ለማግኘት ስምምነት በመፈራረም በመሆኑ፤ ሶስት ሺ አመታት ካለፈው ታሪካችንም በሁዋላ፤ ዛሬም የልመና የእርዳታ እህል ከመቀበላችን በላይ፤ ምን አይነት አያዎ (paradox) ህይወት ይኖረን ይሆን? በአለም ላይ እጅግ አሳፋሪው ከሆነው ስራ፤ ይህም እህል ተመፅዋች ከመሆን በላይ ይገኝ ይሆን? ነው ወይስ እህል ለምኖ ከመብላት የሚበልጥ ሌላ ተዋራጅነት ኑሮ ይኖር ይሆን? ይህ በሀገር ስም እየለመኑ የመብላት ታሪክ፤ ለሁሉም ትውልዶች፤ እጅግ በጣም ሊሰማቸው የሚገባና፤ የከፋ የህዝባችን መዋረድ መገለጫ ነው። ምክንያቱም በ21ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ እህል ለምኖ ከመብላት ፈፅሞ በህይወት አለመኖሩ ይሻላልና ነው።

በመሆኑም መጭው ትውልድ ይህን የእርዛትና የልመና ህይወት ታሪክ ለመጣል፤ ለመፍትሄ መነሳት ያለበት አሁን ብቻ ነው። ከዚህ በመነሳት ነው እንግዲህ፤ በነዚህ አምሳ አመታት ውስጥ ከሞላ ጎደል በአንባገነን አገዛዛቸው ከሚታወቁት መሪዎቻችን አንዱ የሆኑትንና በቅርቡ በማይቀረው ሞት እንደ ቀላል ሰው ከክርስቶስ የፍርድ ቀን በፊት ላይነሱ በሞት አለም ውስጥ የተጠቀለሉትን የጠ/ሚር መለስ ዜናዊ እና የኢህአፓ ትውልድ ሌጋሲና ከዚህስ በሁዋላ ምን መድረግ አለበት? በማለት ይህንን ዳሰሳዊ ፅሁፍ ለማዘጋጀት የቻልኩት። ከአስራ ሰባቱ አመታት የጦር ሜዳ ትግል በሁዋላ፤ አቶ መለስ ዜናዊ በሃያ አንድ አመታት የሀገር አገዛዝ ዘመናቸው፤ ጥቂት የሚባሉ መሰረታዊ የልማታዊ ስራዎችን (በተለይ ፓርቲያቸው ኢህአዴግ በቅንጅት ለአንድነት ፓርቲ በግንቦት 7 ምርጫ በድንገት ሳይታሰብ ከተሸንፈባቸው በሁዋላ ባደረጉት፤ የ’ደንበር ገተር’ ሩጫ፤ ጥቂት ለመስራት መውገርገራቸውን ለመዋሸት ግን ፈፅሞ አልችልም። አቶ መለስ ዜናዊ በጉዞአቸው በርካታ በጎ ያልሆኑ ስራዎችን ወይም ተፅእኖዎችን አድርሰዋል።  እነዚህን መጥፎም ይሁኑ ጥሩ ተፅእኖዎችን በእውነት ላይ በመመርኮዝ፤ በመረጃ በማቅረብ፤ ከወገንተኛነት በመራቅ፤ ከአድልኦና ከጭፍን ጥላቻ በፀዳ አመለካከት ላይ በመመርኮዝ፤ ከዚህም በሁዋላ ያገራችን ህዝብ ታላቅ ብሄራዊ መግባባት ላይ በመድረስ በህብረት እና በአንድነት ለመስራት መነሳት እንዲችል ከመጣር አኳያ መገምገም የቅን  አሳቢ ሰው ሁሉ ግዴታ ነው። በአቶ መለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመን የተሰራ “መልካም ስራ የሚባል የለም”፤ በማለት የምትሞግቱም ወገኖች እንዳላችሁም በማወቅ፤ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመካድ የማልችልበትን፤ አራት ዋና ዋና ምክንያቶች፤ በቅድሚያ ልጥቀስ።

                                    1/ ነባራዊው እውነት 

የተለያየ የሃይማኖት፤ የቋንቋና የፖለቲካ ወዘተ አመለካት ቢኖረንም፤ እንደዚሁም በተለያ የግልና የቡድን ባህርያት እና አመለካከታችን ውስጥ የምንኖር ብንሆንም፤ ተከባብረን በአንድነት ለመኖርና ለመስራት እንዳንችል የሚከለክለንን ጥሰን ለመውጣት እንችላለን፤ በማለት ማመኔ አንዱ ዋነኛ ምክንያት ነው። ይህንን ለማድረግ ለመቻላችን፤ አንድ እውነተኛ ሞዴል አቅርብልን ብባል፤ የማቀርበው፤ ታላቁን ጥቁር ሰው፤ የአፍሪካ መኩሪያ የሆነውን ኒለሰን ማንዴላ ነው። ማንዴላ ከአፍሪካ “መሪዎች” ልዩ የሚያደርገው፤ በቅድሚያ ከማንኛውም አይነት የፖለቲካ፤ የስልጣን እና የኢኮኖሚ ሙስናዎች (corruptions) ፍፁም ነፃ መሆኑ ዋነኛ ነው። ሁለተኛ የስልጣን ጥማት ስሌለበት፤ በአፍሪካ መሪዎች ታሪክ ውስጥ ከጁሊየስ ኔሬሬ ቀጥሎ ስልጣኑን በፈቃዱ ለተተኪው ያስረከበ መሆኑ ነው። ሶስተኛው ማንዴላን ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ሀገሩን በባርነት ከገዛው ከነጭ ህዳጣን ህዝብ ጋር እንኳን ሳይቀር ብሄራዊ እርቅ በማድረግ፤ “ይህ ሀገር ከዛሬ ጀምሮ የጥቁሩም የነጩም ህዝብ እኩል መኖሪያ ስለሆነ ሁላችንም ይቅር በመባባል በህብረት በመስራት እንኑር” በማለት ወደ ሰላምና ልማት ህዝቡን ለመመለስ መቻሉ ነው።አራተኛ ሀገሩን ፍትህና ዲሞክራሲያ፤ ነፃነትና አንፃራዊ እኩልነት (የኢኮኖሚ እኩልነት ለብዙሀን ጥቁር ህዝብ ገና አልሰፈነምና) ያለባት ሀገር ማድረጉ ናቸው። የእኛስ ሀገር ከዚህ አንፃር የት ነች? የትየለሌ ናት! ገና ገና ረጅም ርቀት መጓዝ ይጠይቀናል። በአብሮነታችን፤ አንዳችን ላንዳችን መልካም አእምሮና ንፁህ ልብ እንዲኖረን በማድረግ፤ ከራሳችን ጎጂና ጠባብ አስተሳሰብ፤ ሌላውን ወገናችንን በከንቱ መጥላትና ባህላችን ካደረግነው ክፉ አመለካከታችን ነፃ በመውጣት፤ ይቅር በመባባል አብረን ለመስራት እንደምንችል እምነት ስላለኝ ይህንን ለመፃፍ ተነሳሁኝ። ትልቁና ዋናው ችግራችን የተለያ የፖለቲካ አመለካከታችን ቢሆንም እንኳን፤ በመደራደር እና በመቻቻል ለመስራት በተለይ በአዲሱ ትውልድ ዘመን ይችላል የሚል እምነት አለኝ። በተለይም ነባራዊውን ታላቅ የልዩነት መጋረጃ ለመቀየር፤ ሁሉንም ወገን ሊያስማማ የሚችል፤ ሁሉም የሚሳተፍበት ብሄራዊ መግባባትን የሚያመጣ ታላላቅ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን ለማውጣት፤ እንደምንችል ማመኔ አንዱ ምክንያቴ ነው።

                                      2/ አፍራሽ አመለካከት

አፍራሽ ብቻ ከሆነው የፖለቲካ አመለካከት ችግራችን ነፃ መውጣት እንደምንችል ማመኔ ሁለተኛው ምክንያቴ ነው። ባገራችን ስር እየሰደደ፤ ፖለቲካዊ ባህል እየሆነ ከመጣው፤ ያለፉትንም ሆነ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ፤ ክፉ ስራዎችን ብቻ ነቅሶ በማውጣት፤ መልካም ስራዎችን ግን በመጣል ላይ በተመሰረተውና ሁላችንንም ከሚያጠፋው አፍራሽ ፖለቲካዊ የአመለካከት በሽታ ነፃ በመውጣት፤ “መልካም ስራ”ን እንደመልካምነቱ፤ “ክፉ ስራንም”፤ እንደ ክፋቱ መጠን፤ ለትምህርታችንና ለተሞክሮአችን እንዲሆነን በመገምገም፤ በእውነትና በመረጃ ላይም ተመስርቶ፤ መፃፍም ሆነ መናገር ስላቃተን፤ ይህንን ችግር መፍታት ሁሉም ዜጋ የሞራል ግዴታ አለበት። ይህንንም በማድረጋችን እኛም ተጠቃሚ ነን። መጭው ትውልድም፤ ክፉ ታሪካችንን ብቻ እያጋነነ ከመቆራቆዝ ከሚመጣ የመጠፋፋት አባዜ ወይም ባህል ሳይላቀቅ፤ በደምሳሳው የመጠፋፋት ወይም የማፈራረስ ተልእኮ ላይ ተመስርቶ ራእዩን እንዳይተልም ማሳሰብ የሁላችንም ግዴታ ስለሆነ ነው። ይኸውም ክፉም ሆኑ መልካም ስራዎቻችን ለቀጣይ ስራዎቻችን እንደ ማዳበሪያ በመጠቀም ለመስራት መቻል፤ አብሮ የመኖር ጥበብ በመሆኑ ነው።

                                  3/ እውነት አርነት መውጣት

እውነት አርነት ልታወጣን እንደምትችል ማመኔ ሌላው ምክንያቴ ነው። ብናምንበትም ባናምንበትም በታላቁና ጊዜ በማይሽረው መንፈሳዊ መፅሀፍ፤ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ “እርስበርሳቸሁ እውነትን ተነጋገሩ” “እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም አርነት ያወጣችሁዋል” የሚለውን ጥቅስ ለሰው ልጆች ሁሉ በተለይም ለሀገር መሪዎች የሚጠቅም መርህ ስለሆነ፤ በሸፍጥ ላይ ሳይሆን በእውነትን ላይ ተመርኩዞ መስራት ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሚገባን ሞራላዊም እንበለው ስነምግባሪዊ ግዴታችን በመሆኑ ነው። የሞራል ጉዳይ ካላስጨነቀንና ለስነምግባር ወይም ለህሊናችን የማንገዛና ማንታመን ከሆንን፤ ለልጆቻችንና ለመጭው ትውልድ እንዴት ልንታመን እንችላለን? ብለን ማሰብ አእምሮ ያልጎደለው ሰው ሁሉ የሚያደርገው ጉዳይ ነው። እውነት በሌለበት በመነጋገር የሚመጣ አንዳችም መልካም ነገር በህብረተሰባችን ውስጥ ለመስራት አንችልምና ነው። ይህም ሀይማኖተኛ ከመምሰልም በላይ እውነተኛ ሰው መሆንን የሚጠይቅ ታላቅ ጉዳይ ነው።

                     4/ ሁሉም ነገር በፍቅር ይቻላል

እርስበራሳችን “ፍቅር ቢኖረን” ቀርቶ እርስበራሳችን በጠላትነት አለመፈላለግ ብንችልና፤ በሰለጠነ ፖለቲካዊ ልዩነት ድርድርና መቻቻል ብናምን፤ ይህ በራሱ ነፃ ሊያወጣን እንደሚችል ማመኔ ሌላው ታላቅ ምክንያቴ ነው። ይኸውም ለአንድ ቡድን በስሜታዊነትም ይሁን ከግል አቋም አንፃር፤ በወገንተኛነት በመደገፍ ሌላውን ወገን ግን ለመጥላት አለመቻሌ አራተኛው ምክንያቴ ነው። ከወገናዊነትና ከስሜታዊነት የፀዳ አመለካከት ካለን፤ ሰላማዊ ተቃዋሚያችንን ቀርቶ ሊገድለን የሚያሳድደንን ጠላታችንን እንኳን ላለመጥላት እንችላለን ብዬ አምናለሁ። “The best way to prevent an enemy is to make him a friend” የምትለዋ የነጮች ብሂል ተቃዋሚዎቻቸውን ሁሉ እንደ መርዘኛ ጠላት እያዩ ለሚያሳድዱ ለእኛ ሀገር ፖለቲከኞች ትምህርት ሰጭ ስለመሰለችኝ ጥቅስዋን እናዳለች አስቀምጬአታለሁ። በመሆኑም ለተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይሁን ወይም ለገዢው ፓርቲ ልሳን፤ ወይም ወገንተኛ ባለመሆንና፤ ለፖለቲካ ፍጆታም ለሚሆን የፕሮፓጋንዳ ስራዎችን ባለመስራት (የየፓርቲው አባላት ካልሆንን በስተቀር) የፓርቲዎቻችንንም ልዩነቶቻቸውን ባለማስፋት፤ ባጠቃላይ ማንንም የማያገልል ፖሊሲ ባለመከተል በገለልተኛነትና ለሁሉም በእኩልነት ላይ በመቆምና በመስራት፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ማእከላዊ በማድረግ በነፃነት፤ በግልፅነትና በተጠያቂነት ለማገልገል እንዲችሉ ማገዝ አንዱ ግዴታዬ ሆኖ ስለሚሰማኝ ነው። በመሆኑም በእኔ እይታ ካለፉት የኢትዮጵያ የቅርብ ዘመን መሪዎች ውስጥ ዋነኛውና ጦሰኛው ሊባሉ የሚችሉት አቶ መለስ ዜናዊ በዘመናቸው ከሰሩዋቸውና በጎ ከምላቸው ስራዎቻቸው በመጠቃቀስ ስጀምር፤ እነዚህን ተግባራት እንደ በጎ ስራዎች የማትቆጥሩ ወገኖቼን ትእግስታችሁንና በጎ ህሊናችሁን እየጠየቅሁ፤ ከጥላቻ ስሜትም ውጭ ሆናችሁ ባግባቡ እንድትተቹበት እጠይቃለሁ አመሰግናለሁ።

danruth2000@gmail.com

ኢትዮጵያ ያመለጣት ታላቅ እድል

ኢትዮጵያ ያመለጣት ታላቅ የእግር ኳስ እድል

 (በዮሴፍ ደግፌ)

በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ዳሰሳህ….ዳዊት ጥሩ ታዝበሃል…ማለፊያ አባባልም ተጠቅመሃል። ታዲያ የ”ውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን” እንዲሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ነገር ሲነሳ ውሾ የሚኮን ይመስለኛል.. የዘወትር ሽንፈታችንን ሳስበው ማለት ነው። በነገራችን ላይ ይሄ “…ከ31 አመታት በሁዋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ደረስን…” የሚባለው አባባል በቂ መስሎ አልታየኝም። ‘ከ31 አመት በፊት’ የሚባለው እኔ እንኳን የትላንትና ያህል የማስታውሰውና ታዋቂው የቀድሞ ብሄራዊ ቡድናችን ተጫዋችም ዋና አሰልጣኝም በመሆን ያገለገለው መንግስቱ ወርቁ ያሰለጠናቸው እንደነ ንጉሴ ገብሬ ለማ ክብረትና አፈወርቅ ጠናጋሻው ያሉ ተጫዋቾችን ያካተተ በ1974 ዓ.ም በሊቢያ በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ እግር ኳስ ጨዋታ ላይ የተካፈለ ቡድናችን ነው። የአሁኑ የ2005 ዓ.ም ቡድናችን እነ ሳላዲንንና እነ አዳነን በፊት አውራሪነት ይዞ ከ31 አመታት በፊት የነበሩትን ለማ ክብረትንና አፈወርቅ ጠናጋሻውን በበረኛነት ሊያሰልፍ የሚችል ቢሆን ኖሮ ምናልባት 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለ2ኛ ጊዜ የኛ የሚሆን ነበር…የአሁኑ የ2005 ብሄራዊ ቡድናችን ዋና ችግር የበረኛ ችግር ይመስለኛል ። በ1974 አፍሪካ ዋንጫ ወቅት High school ተማሪ ስነበርኩኝ የልጅነት ስሜቴን በሚገባ አስታውሰዋለሁ። እንደ 2005ቱ ቡድናችን ሁሉ የ1974ቱ ቡድናችንም በጥዋት ነበር የተሸነፈውና አብዛኛዎቹ ተጫዋቾችም እንደተለመደው በዚያው በስደት የኮበለሉት። ለማለት የፈለግሁት የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ መድረስ ከ31 አመታት በላይ የሆነው መሆኑን ነው። ባልሳሳት ከ31 አመታት በፊት የብሄራዊ ቡድናችን ዋና አሰልጣኝ የነበረው ታዋቂው መንግስቱ ወርቁ ከ50 አመታት በፊት (እ.ኤ.አ. 1962) ለቡድናችን በዋና አጥቂነት ቦታ በመጫወት በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ እግር ኳስ ጨዋታ ዋንጫ ካስገኙልን ውድና ምርጥ ተጫዋቾቻችን አንዱ ነበር።  (የእነ መንግስቱ ወርቁ አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን አላየሁም ዜናውን የነገረኝ የጋዜጣ የመፅሄትና የመፅሃፍት ወዳጅ የነበረው ወላጅ አባቴ ነበር) ስለዚህ ከ50 አመታት በፊት ኢትዮጵያ  የአፍሪካን ዋንጫ “የበላች” ሀገር ተብሎ መጠቀስ አለበት እንጂ “ከ31 አመት በፊት” የሚለውን ብቻ እየደጋገሙ መጠቀስ ሰነፍ ያስብላልና-ጠንቀቅ። ነው ወይስ ወደ ሁዋላ ሄዶ ታሪክ ለመፈተሽ…?

ወደ አሁኑ ጨዋታ ስመጣ ዋልያዎቹ ዋንጫ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚበጅ እጅግ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ድሎችን ያጣንም ይመስለኛል።….እንዴት? ማለት ደግ ነው።…እንዲህ ነው….ዋልያዎቹ ለሩብ ፍፃሜ….ደግሞም….ለግማሽ ፍፃሜ…ተጠናክረውም ለዋንጫ ቢደርሱ (playoff) ከተሳካም ደግሞ ዋንጫ ቢያነሱ….የኳሱ ብቻ ሳይሆን የብዙ አለምአቀፋዊ ድሎች ባለቤት ለመሆን እንችል እንደነበረ እኔ ብቻ ሳልሆን በርካታዎች ወይ ነዶ! ያላለ ሰው አልነበረም። …ነገሩ ቀላል እንዳይመስላችሁ…የምናይበት መነፅር… በርግጥ ትልቅ ነገር ዳዊት ያየኸውና ያነሳኸው አለ… ይኸውም…በአንድነት ዙሪያ…በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ…በአጠቃላይ ፍቅር ዙሪያ ኳስ በጣም ሊያስተሳስረን እንደሚችል። ማለፊያና መልካም…እውነትም ነው። በተጨማሪ ደግሞ በውጭ ሆኖ ለሚያይና ለሚመዝን …. የኳስ ዋንጫ ከማግኘት እጅግ በበለጠ በርካታ ጉዳዮችን (በፖለቲካውም በማህበራዊውም በኢኮኖሚያዊውም) ለመጎናፀፍ የምንችልበትን እድል በደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ፍፃሜ ባለመድረሳችን ያጣን ይመስላል።

ነገሩ…ባጭሩ እንዲህ ነው…የአለም ሁሉ አይኖች በደቡብ አፍሪካ ዋንጫ ላይ ነበሩ።…እንደ የአለም ፕሬዜዳንት ከሚቆጠረው ከባራክ ኦባማ ጀምሮ…ልእለ ሃያላኑ ሁሉ ማለት ነው… የአፍሪካን የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታን በሚመለከቱበት ወቅት የአፍሪካን ትንሳኤም አብረው እየተከታተሉም ጭምር መሆኑ ይታወቃል። ምክንያቱም አፍሪካ የአለምን 1/2 ፖቴንሻል (ሀብት) ስለያዘች ብቻ ሳይሆን… ነገርግን ለምስራቁም (እነቻይና) ለምእራባውያኑም…ደግሞም ለመካከለኛው ምስራቅ (አረብ-እስራኤል) አለምአቀፍ ጉዳይም ሁሉ የአፍሪካ ተሳትፎና ወሳኝነት እያየለ በመምጣቱ የግሎባላይዜሽን እይታቸው ሃያል በመሆኑ ነው። ማለትም ከዚህ በሁዋላ አፍሪካ የማትካፈልበትና የማትስማማበት አለምአቀፋዊ ጉዳይ ፋይዳ እንደሌለው የበለጠጉት ሀገሮች ገብቶአቸዋል…የልእለ ሃያላኑ አይን አንድ ጥቁር አፍሪካዊ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋች ኳስ መሀል ሜዳ ላይ ሲያሽሞነሙን/ሲያድቦለቡል…እመረብ ውስጥም ሲዶላት ከሚመጣው ስሜታዊ ደስታ በስጀርባ ያለውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እይታ መነጣጥረው ለማየት አቅምና ፍላጎትም አላቸውና ነው…..ስለሆነም እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያለ ሀገር በሩጫ ብቻ ሳይሆን በእግር ኳስም…በአለም ፊት አይሎ መውጣት የሚያመጣላት ሁለንተናዊ  (ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ) ትርፍ ቀላል አልነበረም። በአፍሪካ ዋንጫ አይለን መውጣታችን በሀገር ውስጥም በውጭም በነገር ሁሉ እያየልንና እያደግን መምጣታችንን አመላካች ስራ ነውና። የኢትዮጵያ እውቅና በአለም ፊት አሁንም ድረስ በእርስበርስ ጦርነት…በእርዛትና ደግሞም በስደት ብቻ እንደመሆኑ መጠን…የአፍሪካው ዋንጫ ድል ብዙ ውርደታችንን በአለም ፊት በመሸፈን እኛንም…የአለም ህዝብ በእኛ ላይ ያለውን እይታንም የሚያነቃቃ አንድ ታላቅ ጥሪ ይሆንልን ነበርና ነው። በርግጥ በሩጫው (አትሌቲክስ) ከብዙ በጥቂቱ ብንታወቅም…ርሀባችንንና ስደታችንን ደግሞም እርስበርስ አለመስማማታችንን ሊሸፍንልን ባለመቻሉ አሁንም ድረስ በውጭ ገንነን የምንታወቀው ያው በስደተኛ…በረሀብተኛ ምሳሌና በሁዋላቀርነት እንደሆነ ይበልጥ የሚገባን በስደት ስንኖር ብቻ ነው። አንድ ቻይና-አሜሪካዊ የኮሌጅ ፕሮፌሰር ኢንተርናሽናል ተማሪዎችን እያስነሳን እንድንተዋወቅ ሲያደርግ… እኔ ከኢትዮጵያ መሆኔን ከገለፀ በሁዋላ…ስለ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲሰጥ…በአለም ደሃ ርሀብተኛ አገሮች ውስጥ አንደኛዋ በማለቱ ለጊዜውም ቢሆን አንገቴን አስደፍቶኝ ነበር። እኔም ለመልስ በመጓጓት ከቆየሁ በሁዋላ በፕሮጀክት ባዘጋጀሁት ላይ የተከራከርኩት ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ሰው ሰራሽ ችግር እንጂ “ፖቴንሸል” ደሃ አይደለንም በማለትና በማስረጃ በማስረዳት ተማሪዎቹንም ፕሮፌሰሮቹንም ማሳመን ብቻ ሳይሆን ውጤት አግኝቻለሁ። እንደዚሁም በሌላ ‘ክላስ ቴስት’ ላይም…የኢትዮጵያ ታሪክ ዳቦ ለመሆን ባይችልም ከበርካታ የበለጠጉ አገሮች ቀደምትና ታሪካዊ መሆንዋን በዝርዝር በማስረዳት አፋቸውን ነበር ያሲያዝኩዋቸው።…ከንግግሬ በሁዋላ ግን ተማሪዎቹ በግል አግኝተውኝ “So why you are here?” በማለት ሊያሸማቅቁኝ (ውጭ የወጣሁት ዳቦ ፍለጋ መሆኑን ሊነግሩኝ)… ይሁንና እንዲህ አይነት በራስ መተማመንስ ከየት አመጣህ እስኪሉም ድረስ ተገርመውም ነበር…የኔም መልስ ባጭሩ “በቅኝ ግዛት ባለመገዛቴ ነው” ነበር።

ዳዊት ይህን ሁሉ ያነሳሁልህ ኳስ ብናሸንፍ ወይም እስከ ዋንጫው ድረስ እንኳን ተጫዋቾቻችን ለመጓዝ ቢችሉ ኖሮ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ገጥታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በእጅጉ ይለወጥና ለእድገት በር ሊከፍትልን ይችል ነበረ ለማለት ብቻ ነው። ደግሞም ኳስ ራሱ ፖለቲካም ስፖርትም ስለሆነ እንጂ… ኳሱን ትቼ ፖለቲካ ውስጥ ዘልዬ መግባቴም እንዳይመስልህ…ብገባም ፖለቲካ የማይገባበት ጉዳይ ስለሌለ ምንም አይደለም።….ነገርን ነገር ያነሳዋልና ፖለቲካና አፍሪካ ከተነሱ አይቀር ይህንን ልጥቀስ። አንድ የማንክደውን ጉዳይ ግን አቶ መለስ ዜናዊ የአፍሪካ ቁጥር አንድ Spokesman መሆናቸውን ይመስለኛል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ በበለጠ ለአፍሪካችን ይጠቅሙ እንደነበር ማህደርና ነገር በመምዘዝ እንዲሁ መከራከሪያ ፅሁፍ አዘጋጅቼ ተቀባይነት ያገኘ ንግግር አድርጌ ነበር። ይህንን የምለውም የእኔን ስራ ለመግለጥ ፈልጌ ሳይሆን ፖለቲካውም እንደ ኳስ እየተዟዟረ እየገባብኝ ተቸግሬ ስለሆነ አንባቢዎቼን ይቅርታ እጠይቃለሁ… እናም ወንድሜ የአፍሪካ ዋንጫን ማሸነፍ መቻል በኢትዮጵያ ላይ ትልቅ አንድምታ ነበረው ዋልያዎቹ እስከመጨረሻው ለመጫወት ቢችሉ ኖሮ  ለማለት ፈልጌ  ነው ብዙ ቦታ የረገጥኩት። ከዚህ ከአፍሪካ ዋንጫ ጋር ስለሚያያዝ ለአባይ ግድብ መስሪያ የፋይናንስ ምንጭ ከየት ይገኛል የሚል ጥያቄ ሲነሳ በጣም የሚገርመኝን ልናገር…በአሜሪካ ሀገር ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቢሮ አመታዊ በጀት የማይበልጠውና… ለኢትዮጵያ ግን የሰማይ ያህል የራቃት የአባይ መገደቢያ 5 በሊዮን ዶላር የአፍሪካ ዋንጫ ድልን ብናገኝ ኖሮ ገንዘቡን በስጦታም ይሁን በብድር ለማግኘት ማንም አለም አቀፋዊ ድርጅት አያሾፍብንም ነበር።…እንዴት ቢባል የኢትዮጵያ ፖቴንሻል በአለም የታወቀ ሲሆን…በተጨማሪም እያደገች መሆንዋን በአፍሪካም በአለምም በስፖርቱም በፖለቲካውም በኢኮኖሚውም መድረክ በሚገባ ለማረጋገጥዋ ከቻለች… የተረጋጋች ሀገር መሆንዋን… መሪዎቻችን መብሰላቸውን… ህዝብዋ ጠንካራና አንድነት ያለው መሆኑን ወዘተ ስለሚያሳይ…ይህ ደግሞ በአለም ደረጃም ሆነ በአፍሪካም ሁነኛ ቦታ/ትልቅ ሚና ትኩረትም ስለሚያሰጣት…አባይን መገደብ ቀርቶ ሌላም ታላቅ ፕሮጀክት ለመስራት እንኳን የሚያግዳት ነገር ሊኖር አይችልምና ነው።

ባጭር አባባል ግብፅ በአለም ፊት ካላት ተቀባይነትና ተደማጭነት ባላነሰ ደረጃ ኢትዮጵያም ሊኖራት ስለሚችል ለግድብ መስሪያ ገንዘብ ብድር ማጣት ቀርቶ አለም አቀፍ ድጋፍም እናገኝ ነበረ…ማንም እንደማይረባ ሀገር ቆጥሮ በጥርጣሬ ሊያየን አይችልም ነበር ለማለት ነው። በሌላ በኩልም በደቡብ አፍሪካ እስከ ዋንጫ ፍፃሜ ድረስ ብንቆይ ኖሮ የእግር ኳስ ተጫዋቾቻችን በአለም የእግር ኳስ ገበያ የመሸጥ እድል ቦግ ብሎ  አይጠፋም ነበር። …በእድልም ተባለ በችሎታ እስከ ዋንጫው ፍፃሜ ለመጫወት ቢችሉ ኖሮ… ወይም ዋንጫ ማንሳት ቢሳካላቸው ኖሮ ስንት ተጫዋቾቻችን በሚሊዮን ዶላር ይሸጡ እንደነበር መገምት አያዳግትም…በነሱም ዘውግ ባንድ ጊዜ በመጣው መልካም እድልና ታዋቂነት ቀጣዩ ትውልድም ኳስ ለመጫወት በመሸጥ ብቻ እራሱንም ሀገሩንም ያለማ እንደነበረ ለመገመት አያስቸግርም። ከዚህም በተጨማሪም አንተም እንደገለፅከው እስከ ዋንጫው ጨዋታ ድረስ ብንቆይ ኖሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ መልክ (image) ይለወጥም ነበር። ይኸውምበአለም ሁሉ በቴሌቪዥን መስኮት በተሰራው “ ኑና እዩን ” በሚለው የውብ ኢትዮጵያውያን የማስታወቂያ ስራ መሰረት… ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ሀገሪትዋ በቱሪስቶች መጨናነቅዋ አይቀርም ነበርና ነው። በዚህች በሶስት ጨዋታ ብቻ በታዩት ደጋፊዎች የተነሳ ኢትዮጵያውያን እንዲህ ውብ ናችሁ እንዴ!….መስህብ ያላቸው ሰዎች አላችሁ…ርሀብተኛ….ስደተኛ ብቻ አይደላችሁም…. ያሉኝ ብዙ አሜሪካውያን ናቸው። እስከ ዋንጫው ብንደርስማ ኖሮ የአለም ዕይታ በጣም እንደሚለወጥ ለመገመት አያቅትም። ስለሆነም በርካታ ገንዘባቸውን ማድረሻ ያጡ ቱጃሮች ወደ ኢትዮጵያ በመጉረፍ… ከፍተኛ የቱሪስት ገቢ በማስግኘት… በጭስ አልባ እንዱስትሪ ሀገሪትዋ ለማደግና ለመመንደግ ትችል የነበረበት እድል በኳስ ሜዳው ድል እጦት የተነሳ ጨፍግጎአል። ሌላም ሌላም ለማለት ይቻል ነበር.. ወሬ ቢበዛ….እንዲሉ በዚህ ላብቃ። በመጨረሻም ስፖርትና ቦተሊካ እንደማይጣረሱ ልብ አላችሁልኝ? መልካም እድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን። Let God help the Country.