ተስፋና ተስፈኝነት (በዮሴፍ ወርቁ ደግፌ)

ከተስፋም የተባረከውን ሰማያዊና ዘላለማዊውን ተስፋ፤ ተስፋ የምናደርግ እኛ፤ በዚህችም ምድር አጭር ዘመናችንም በነገር ሁሉ እግዚአImageብሄርን ተስፋ በማድረግ የምንኖር እኛ፤ ተስፋንና ተስፈኛነት በክርስትና ህይወት ካልመዘንነው በስተቀር፤ ኑሮአችን ባዘመመ ቁጥር፤ በስጋት ብዛት እና በተስፋ መራቅ ነፍሳችን ዝላ በኑሮአችንም ደስታና ሰላም በማጣት፤ በእግዚአብሄር ላይም ልናጉረመርም እንችላለን። እግዚአብሄርንና የተስፋውን ቃል በመጠራጠር ወይም በመርሳት ተስፋ የቆረጠ ህይወት ወይም የጥርጣሬ ህይወትን የምንኖር ከሆነ ደግሞ፤ ከሰዎች ሁሉ እጅግ ጎስቋሎች እንደሆንም መዕሀፍ ቅዱስ አስተምሮናል። እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሀይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይበራሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ አይደክሙም፤ በማለት ተስፋችንን እያለመለምን እንድንኖር ብቻ ነውና ፈቃዱ።

ያለ-ምግብ ለ…ቀናት ያህል፤ ያለ-ውሃ ለ…ቀናት፤ ያለ-አየር ደግሞ ለ…ሰከንዶች ያህል ብቻ የሰው ልጅ ለመቆየት እንደሚችል የሚናገሩት ሰዎች፤ ያለ-ተስፋ ለምን ያህል ጊዜ ለመቆየት እንደሚቻል ግን ሲናገሩ አልሰማሁም። ምክንያት ሊሆን የሚችለው ራዕያቸውም ሆነ ዕቅዳቸውም ተግባራቸውም ጭምር ምድራዊና ጊዜያዊ ብቻ ስለሆነና ከምድር በላይ ሌላ ተስፋ ስለማይታያቸው ብቻ ነው። የምድር ላይ ተስፈኞች ከምድራዊ ነገር በላይ ስለ ተስፋ ማሰብ፤ መንፈሳዊውና የእግዚአብሄርን ነገር ማሰብ ስለሚሆንባቸው፤ በጉድለታቸው፤ እየታበዩ መኖርን ይመርጣሉ። ነፍሳቸውም አምላክቢስነታቸውን ስለምታንዐባርቅ ዘላለማዊው ተስፋ ተሰውሮባቸዋል፤ ምድራዊነትና  ስጋዊነትም እየጎተታቸው ለአጭር ዘመንም ቢሆን ምድርን የሙጥኝ ብለው ይኖራሉ። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በአንድ ነገር ላይ (በምድር) ሙሉ በሙሉ ተስፋ ማድረጋቸውን ልብ እንበል።

ተስፋ ግን ምንድነች? በሃገር ቤት እያለሁ በተመለከትኩት አንድ ኢ-መንፈሳዊ ቲአትር ላይ ተስፋ ርቆ የተሰቀለ ዳቦ ነው በማለት አንደኛው ተዋናይ እንደተናገረው ተስፋ አስቆራጭ አባባል፤ ተስፋ የማይደረስባትና የማትጨበጥም አይደለችም። ተሰፋ ከእምነት ጋር በእጅጉ ይዛመዳል። ይኸውም ተስፋ ማለት የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ሳይሆን፤ በርግጥ የሚያስፈልገንን፤ ነገርግን አሁን ለማግኘት ያልቻልነውን፤ አንድ ቀን ግን በተጨባጭ ልናገኘው እንደምንችል፤ በሙሉ ልብ በእምነት ያለጥርጣሬ መጠበቅ ማለት ነው። በእንዲህ አይነቱ ተስፋ መኖር፤ ወይም ተስፋን በትዕግስት የመጠበቅ ስጦታና ችሎታ ግን በእውቀት ወይም በገንዘብ ብዛት ወይም እንዲሁ ዝም ብላ የምትገኝ ሳትሆን፤ ከፅኑ ዕምነት የተነሳ በሁሉ ላይ ጌታና ገዢ ከሆነው ከእግዚአብሄር ብቻ የምትመጣ ናት።

እግዚአብሄርን አምላካቸው ላደረጉ ሁሉ፤ ተስፋ ተስፋ ብቻ አይደለችም። ሀይልና ጉልበትም ጭምር እንጂ። እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሀይላቸውን ያድሳሉ…ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ አይደክሙም በማለት ህያው ቃሉ ሲያስተምረን ማዕከል ያደረገው እኮ በዋናነት ተስፋን ቢሆንም፤ ተስፋ ጉልበትም፤ ሀይልም እንዲሁም ትዕግስትም፤ ፅናትም እነደሆነችም ያሰየናልና። በመሆኑም ተስፋችን ሙሉና (ፍፁም) ትርጉም ያለው  የሚሆነው በእግዚአብሄር ላይ ታምነን ስንጠብቅ ብቻ እንደሆነ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ማመንም አለብን።

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገትና ሰማይ በወጣው የኑሮ ውድነት ሳቢያ ከቄሱ ትንቢታዊ መጣጥፍ ጋር አያይዤ ስዕፍ፤ ተጠራጣሪ (pessimist) በመሆን፤ ሌሎች  ተጠራጣሪ እንዲሆኑ በመፈለግም አይደለም። ነገርግን ተስፋችንን ለመውረስ ግብታዊና ስሜታዊ እንዲሁም ደግሞ ተአምር ብቻ ጠባቂ ሳንሆን፤ እውነትንና መሰረታዊ ችግራችን አስቀድመን ብናውቅ ችግሩ በምንና እንዴት እንደሚፈታ መንገዱን በማቅለል ይጠቅመናል፤ ከስሜታዊነትና ከግብታዊነትም ያርቀናል ለማለት ያህል ብቻ ነው። መንግስታትም እየሰራን ነው እንጂ እያጠፋን ነው መቸም ቢሆን ሊሉ አይችሉም፤ ምክንያቱም መቸም ቢሆን ስልጣን የሚይዙት እንሰራለን እንጂ እናጠፋለን በማለት ስላይደለ። እኛ ግን ሁሉንም የምናይበትና የምንለካበት የእግዚአብሄር መነዕር (መንፋሳዊ ዕይታ) ስላለን ሁሉን የምንመረምርበት ጥበብ ተሰጥቶናል። ደግሞም በሁሉ ላይ ስልጣን ያላት የእግዚአብሄር መንግስትም በግልም ይሁን በህብረት በሀገርም ይሁን በአህጉር ወይም በአለምአቀፍ ተስፋችን ላይ ከመስራትም ተአምርም ቢያስፈልግ ከማድረግም መቸም ቢሆን ሊያቅባት የሚችል ነገር እንደሌለም እናምናለን ።

ተስፋን እንዴት እንመለከታታለን? ስለተስፋ፤ ሰላአካሄጅዋ ትግሰት፤ እያንዳንዳችን ምን አይነት አመለካከት እንዳለን ማወቅ፤ የሌሎችን ሀሳብ በጭፍኑና በደምሳሳው እንዳንጠላና እንዳንገፋፋ ሲረዳን፤ አመለካከታችንም በእግዚእሄር ቃል በማረቅም ተስማምተንም አብረን እንድንሰራ ይረዳናል። ይኸውም አንዳንዳችን ተስፈኞች ወይም መልካም ነገር ይሆናል የምንል (optimist) ስንሆን፤ አንዳንዶቻችን ደግሞ ተጠራጣሪዎች (pessimist) ወይም ተሰፋ ቆራጮች (ጨለምተኞች) ነን። ቀሪዎቻችን ደግሞ በድርጊት (realist) በተጨባጭ የምናም ልንሆን እንችላለን። ነገር ግን ስለተስፋ ወይም ስለመጭው ሕይወት፤ እድል፤ ፈንታ የተለያየ ስሜትና አመለካከት ቢኖረንም ቅሉ አብረን ለመስራትና ለመኖር ግን ሊያቅተን አይገባም። እንዲያውም የተለያየ የአመለካከት ተስፋ መኖር ጤናማ እድገትን ሲያመጣና ሲያለማ እንጂ፤ ሲያፈርስ እንዳልታየ የሰለጠነው የአለም ክፍል ጥሩ ማስረጃችን ነው። ክርስትናም ይህንን ያስተምራል፤ በክርስቶስ አንድ የሆንን ሁሉ በነገር ሁሉ አንድ አይነት አመለካከት ሊኖረን አይችልም፤ የተለያዩ ብልቶች ነንና።

ከኢትዮጵያ የኖሮ ውድነት የተነሳ በኑሮ ተስፋ ለመቁረጥ የሚዳዳው ክርስቲያን ካለ፤ ይህ ከክርስቲያናዊ ህይወት የሚመነጭ ባህርይ አለመሆኑን በርግጠኛነት መናገር አለብን። ይኸውም “ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም” ከሚባለው ልማዳዊ አባባል በመነሳት ሳይሆን፤ መሰረቱን በአለቱ በክርስቶስ ላይ ያደረገው ሰው ሁሉ ተስፋቢስ ወይም ተስፋ ቆራጭ ባለመሆኑ ብቻ ነው። የክርስቲያን ሕይወት ስኬት የሚለካውም በምድር ኑሮ መሳካትም አለመሆኑን የምንዘነጋ አይመስለኝም። እናም እኛ ከዚያች ምድር የተፈጠርንና ከህዝቡም 99.99% ያህል የምንሆነው በሙሉ ራሳችንን እንደ የምድር ጎስቋሎች/መከረኞች አድርገን የምናይና በዚያም ያለተስፋ የምንኖር ከሆነ የቱጋ ነው እምነታችን? የኛ መመሪያ መሆን ያለበት መዕሀፍ ቅዱስ ከሆነ፤ መዕሀፍ ቅዱስ ደግሞ የሚለንን ነን ካልን፤ መዕሀፉ የሚለን ከብዙ በጥቂቱ እንደሚከተለው ነው።

  • እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሀይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይበራሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ አይደክሙም፤
  • በምድር ተቀመጥ ታምነህም ተሰማራ የልብህን መሻት ሁሉ እግዚአብሄር ይሰጥሀል፤
  • ያለአለ እግዚአብሄር ፈቃድ የበላ ደስ ብሎትም ተድላን የቀመስ ማነው?
  • ጎለመስሁ አረጀሁም ፃድቅ ሲጣል ዘሩም ተርቦ እህል ሲለምን አላየሁም፤
  • ፃድቅ ግን በእምነት በህይወት ይኖራል፤
  • በእሳት መካከል እንኳን ብራመድ አንተ ከእኔ ጋራ ነህና ክፉን አልፈራም፤
  • በሰው ልብ ብዙ ሃሳብ አለች የእግዚአብሄር ሐሳብ ግን ትፀናለች፤

በሌላ በኩል ደግሞ ተስፋችንን ለመጨበጥ ወይም ከእግዚአብሄር ዘንድ የተስፋ ቃልኪዳን ለመቀበል ከፈለግን፤ እኛም የህብረት ቃልኪዳንም ከእርሱ ጋር ማድረግ እንዳለብን ማወቅ ብቻ ሳይሆን ማድረግም አለብን። ይኸውም–የተስፋ ቃልኪዳንና የህብረት ቃልኪዳንን የተያያዙና የማይነጣጠሉ በመሆናቸው ነው። ምሳሌ–“የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል” የሚለው የተስፋ ቃልኪዳን ሲሆን፤ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከአመዕ ይራቅ” የሚለው ደግሞ የህብረት ቃል ኪዳን ነው። በአመፅ የምንኖር ከሆነ ግን በመጀመሪያ ከእግዚአብሄር ጋር ፈፅሞ ህብረት ስለሌለን፤ ተስፋም ከእርሱ ዘንድ ሊኖረን አይችልም። ስለዚህ እንደ ተስፋ ቃልኪዳኑ የጌታን ስም በመጥራት ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ፤ ከአመዕ በመራቅ ከጌታ ጋር ህብረት ማድረግ አለበት እንጂ፤ በአመፃ ቀጥሎ ከጌታ ጋር ህብረት አለኝ በማለት የጌታን ስም ሲጣራ ቢውል ሊድን አይችልም።

ባጠቃላይ የልቡን መልካም መሻቶች ሁሉ እግዚአብሄር እንዲሰጠው የሚፈልግ ክርስቲያን፤ በምድር ላይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ ተስፋ ሳይቆርጥ በእግዚአብሄር ታምኖ እና ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት በማድረግ መኖር አለበት ማለት ነው። የመፅሀፍ ቅዱሶቹ ዳንኤልና ዮሴፍም ይህንን ያደረጉ ናቸው። ሰው አመፃ ቢያደረግባቸው እንኳን በማጉረምረም ወይም በአመፃ መልስ አልሰጡም። በመሆኑም ዳንኤልና ዮሴፍ ከእግዚአብሄር ጋር የህብረት ቃልኪዳናቸውን ጠብቀው ስለኖሩ የተስፋ ቃልኪዳናቸውን ለመጨበጥ ችለዋል። እናም የኢትዮጵያ ኑሮ ሰማይ ቢወጣ እግዚአብሄር ስለማያውቅና ህዝቡን ስለረሳ አይደለም። በዚያም የኑሮ መከራ ውስጥ ቢሆን ሊያኖርና ሊያሳልፍስ እንደሚችል ስለሚያውቅ፤ ወይም ደግሞ ታሪክን ሊገለብጥ እንደሚችል በራሱ ስለሚተማመን ብቻ ነው። በእርሱ በእግዚአብሄር ሁሉን ችሎ ሁሉን በሚያስችል፤ በማይለወጠውና ፀንቶ በሚያኖረው ተስፋ በማድረግ መኖር ስንጀምር፤ ያንዜ ተስፋንና ተስፈኞችን ማገናኘት እርሱ ያውቅበታል። የህብረት ቃልኪዳናችንን ከእርሱ ጋር  በማድረግ የተስፋ ቃልኪዳናችንን እንድንወርስ ጌታ በምህረቱና በፍቅሩ ይርዳን።

አሜን

 

2 thoughts on “ተስፋና ተስፈኝነት (በዮሴፍ ወርቁ ደግፌ)

    1. Hi Dawit thank you for your comment yea, you’re Right…I need to change the background to custom or natural setting. I’ve got no time to focus on my Blogs at all. Never got time. I wish I could have time and write whatever I want whenever I want. What makes me busy? Full time job, two per time schools and full time kids. And yet, not enough making to survive. I would say I am just living/ surviving now by the Almighty, God grace and Mercy.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s