ኢትዮጵያ ያመለጣት ታላቅ የእግር ኳስ እድል

 (በዮሴፍ ደግፌ)

በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ዳሰሳህ….ዳዊት ጥሩ ታዝበሃል…ማለፊያ አባባልም ተጠቅመሃል። ታዲያ የ”ውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ይሁን” እንዲሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ነገር ሲነሳ ውሾ የሚኮን ይመስለኛል.. የዘወትር ሽንፈታችንን ሳስበው ማለት ነው። በነገራችን ላይ ይሄ “…ከ31 አመታት በሁዋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ደረስን…” የሚባለው አባባል በቂ መስሎ አልታየኝም። ‘ከ31 አመት በፊት’ የሚባለው እኔ እንኳን የትላንትና ያህል የማስታውሰውና ታዋቂው የቀድሞ ብሄራዊ ቡድናችን ተጫዋችም ዋና አሰልጣኝም በመሆን ያገለገለው መንግስቱ ወርቁ ያሰለጠናቸው እንደነ ንጉሴ ገብሬ ለማ ክብረትና አፈወርቅ ጠናጋሻው ያሉ ተጫዋቾችን ያካተተ በ1974 ዓ.ም በሊቢያ በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ እግር ኳስ ጨዋታ ላይ የተካፈለ ቡድናችን ነው። የአሁኑ የ2005 ዓ.ም ቡድናችን እነ ሳላዲንንና እነ አዳነን በፊት አውራሪነት ይዞ ከ31 አመታት በፊት የነበሩትን ለማ ክብረትንና አፈወርቅ ጠናጋሻውን በበረኛነት ሊያሰልፍ የሚችል ቢሆን ኖሮ ምናልባት 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለ2ኛ ጊዜ የኛ የሚሆን ነበር…የአሁኑ የ2005 ብሄራዊ ቡድናችን ዋና ችግር የበረኛ ችግር ይመስለኛል ። በ1974 አፍሪካ ዋንጫ ወቅት High school ተማሪ ስነበርኩኝ የልጅነት ስሜቴን በሚገባ አስታውሰዋለሁ። እንደ 2005ቱ ቡድናችን ሁሉ የ1974ቱ ቡድናችንም በጥዋት ነበር የተሸነፈውና አብዛኛዎቹ ተጫዋቾችም እንደተለመደው በዚያው በስደት የኮበለሉት። ለማለት የፈለግሁት የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ መድረስ ከ31 አመታት በላይ የሆነው መሆኑን ነው። ባልሳሳት ከ31 አመታት በፊት የብሄራዊ ቡድናችን ዋና አሰልጣኝ የነበረው ታዋቂው መንግስቱ ወርቁ ከ50 አመታት በፊት (እ.ኤ.አ. 1962) ለቡድናችን በዋና አጥቂነት ቦታ በመጫወት በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ እግር ኳስ ጨዋታ ዋንጫ ካስገኙልን ውድና ምርጥ ተጫዋቾቻችን አንዱ ነበር።  (የእነ መንግስቱ ወርቁ አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን አላየሁም ዜናውን የነገረኝ የጋዜጣ የመፅሄትና የመፅሃፍት ወዳጅ የነበረው ወላጅ አባቴ ነበር) ስለዚህ ከ50 አመታት በፊት ኢትዮጵያ  የአፍሪካን ዋንጫ “የበላች” ሀገር ተብሎ መጠቀስ አለበት እንጂ “ከ31 አመት በፊት” የሚለውን ብቻ እየደጋገሙ መጠቀስ ሰነፍ ያስብላልና-ጠንቀቅ። ነው ወይስ ወደ ሁዋላ ሄዶ ታሪክ ለመፈተሽ…?

ወደ አሁኑ ጨዋታ ስመጣ ዋልያዎቹ ዋንጫ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚበጅ እጅግ ብዙ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ድሎችን ያጣንም ይመስለኛል።….እንዴት? ማለት ደግ ነው።…እንዲህ ነው….ዋልያዎቹ ለሩብ ፍፃሜ….ደግሞም….ለግማሽ ፍፃሜ…ተጠናክረውም ለዋንጫ ቢደርሱ (playoff) ከተሳካም ደግሞ ዋንጫ ቢያነሱ….የኳሱ ብቻ ሳይሆን የብዙ አለምአቀፋዊ ድሎች ባለቤት ለመሆን እንችል እንደነበረ እኔ ብቻ ሳልሆን በርካታዎች ወይ ነዶ! ያላለ ሰው አልነበረም። …ነገሩ ቀላል እንዳይመስላችሁ…የምናይበት መነፅር… በርግጥ ትልቅ ነገር ዳዊት ያየኸውና ያነሳኸው አለ… ይኸውም…በአንድነት ዙሪያ…በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ…በአጠቃላይ ፍቅር ዙሪያ ኳስ በጣም ሊያስተሳስረን እንደሚችል። ማለፊያና መልካም…እውነትም ነው። በተጨማሪ ደግሞ በውጭ ሆኖ ለሚያይና ለሚመዝን …. የኳስ ዋንጫ ከማግኘት እጅግ በበለጠ በርካታ ጉዳዮችን (በፖለቲካውም በማህበራዊውም በኢኮኖሚያዊውም) ለመጎናፀፍ የምንችልበትን እድል በደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ፍፃሜ ባለመድረሳችን ያጣን ይመስላል።

ነገሩ…ባጭሩ እንዲህ ነው…የአለም ሁሉ አይኖች በደቡብ አፍሪካ ዋንጫ ላይ ነበሩ።…እንደ የአለም ፕሬዜዳንት ከሚቆጠረው ከባራክ ኦባማ ጀምሮ…ልእለ ሃያላኑ ሁሉ ማለት ነው… የአፍሪካን የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታን በሚመለከቱበት ወቅት የአፍሪካን ትንሳኤም አብረው እየተከታተሉም ጭምር መሆኑ ይታወቃል። ምክንያቱም አፍሪካ የአለምን 1/2 ፖቴንሻል (ሀብት) ስለያዘች ብቻ ሳይሆን… ነገርግን ለምስራቁም (እነቻይና) ለምእራባውያኑም…ደግሞም ለመካከለኛው ምስራቅ (አረብ-እስራኤል) አለምአቀፍ ጉዳይም ሁሉ የአፍሪካ ተሳትፎና ወሳኝነት እያየለ በመምጣቱ የግሎባላይዜሽን እይታቸው ሃያል በመሆኑ ነው። ማለትም ከዚህ በሁዋላ አፍሪካ የማትካፈልበትና የማትስማማበት አለምአቀፋዊ ጉዳይ ፋይዳ እንደሌለው የበለጠጉት ሀገሮች ገብቶአቸዋል…የልእለ ሃያላኑ አይን አንድ ጥቁር አፍሪካዊ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋች ኳስ መሀል ሜዳ ላይ ሲያሽሞነሙን/ሲያድቦለቡል…እመረብ ውስጥም ሲዶላት ከሚመጣው ስሜታዊ ደስታ በስጀርባ ያለውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እይታ መነጣጥረው ለማየት አቅምና ፍላጎትም አላቸውና ነው…..ስለሆነም እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያለ ሀገር በሩጫ ብቻ ሳይሆን በእግር ኳስም…በአለም ፊት አይሎ መውጣት የሚያመጣላት ሁለንተናዊ  (ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ) ትርፍ ቀላል አልነበረም። በአፍሪካ ዋንጫ አይለን መውጣታችን በሀገር ውስጥም በውጭም በነገር ሁሉ እያየልንና እያደግን መምጣታችንን አመላካች ስራ ነውና። የኢትዮጵያ እውቅና በአለም ፊት አሁንም ድረስ በእርስበርስ ጦርነት…በእርዛትና ደግሞም በስደት ብቻ እንደመሆኑ መጠን…የአፍሪካው ዋንጫ ድል ብዙ ውርደታችንን በአለም ፊት በመሸፈን እኛንም…የአለም ህዝብ በእኛ ላይ ያለውን እይታንም የሚያነቃቃ አንድ ታላቅ ጥሪ ይሆንልን ነበርና ነው። በርግጥ በሩጫው (አትሌቲክስ) ከብዙ በጥቂቱ ብንታወቅም…ርሀባችንንና ስደታችንን ደግሞም እርስበርስ አለመስማማታችንን ሊሸፍንልን ባለመቻሉ አሁንም ድረስ በውጭ ገንነን የምንታወቀው ያው በስደተኛ…በረሀብተኛ ምሳሌና በሁዋላቀርነት እንደሆነ ይበልጥ የሚገባን በስደት ስንኖር ብቻ ነው። አንድ ቻይና-አሜሪካዊ የኮሌጅ ፕሮፌሰር ኢንተርናሽናል ተማሪዎችን እያስነሳን እንድንተዋወቅ ሲያደርግ… እኔ ከኢትዮጵያ መሆኔን ከገለፀ በሁዋላ…ስለ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲሰጥ…በአለም ደሃ ርሀብተኛ አገሮች ውስጥ አንደኛዋ በማለቱ ለጊዜውም ቢሆን አንገቴን አስደፍቶኝ ነበር። እኔም ለመልስ በመጓጓት ከቆየሁ በሁዋላ በፕሮጀክት ባዘጋጀሁት ላይ የተከራከርኩት ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ሰው ሰራሽ ችግር እንጂ “ፖቴንሸል” ደሃ አይደለንም በማለትና በማስረጃ በማስረዳት ተማሪዎቹንም ፕሮፌሰሮቹንም ማሳመን ብቻ ሳይሆን ውጤት አግኝቻለሁ። እንደዚሁም በሌላ ‘ክላስ ቴስት’ ላይም…የኢትዮጵያ ታሪክ ዳቦ ለመሆን ባይችልም ከበርካታ የበለጠጉ አገሮች ቀደምትና ታሪካዊ መሆንዋን በዝርዝር በማስረዳት አፋቸውን ነበር ያሲያዝኩዋቸው።…ከንግግሬ በሁዋላ ግን ተማሪዎቹ በግል አግኝተውኝ “So why you are here?” በማለት ሊያሸማቅቁኝ (ውጭ የወጣሁት ዳቦ ፍለጋ መሆኑን ሊነግሩኝ)… ይሁንና እንዲህ አይነት በራስ መተማመንስ ከየት አመጣህ እስኪሉም ድረስ ተገርመውም ነበር…የኔም መልስ ባጭሩ “በቅኝ ግዛት ባለመገዛቴ ነው” ነበር።

ዳዊት ይህን ሁሉ ያነሳሁልህ ኳስ ብናሸንፍ ወይም እስከ ዋንጫው ድረስ እንኳን ተጫዋቾቻችን ለመጓዝ ቢችሉ ኖሮ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ገጥታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በእጅጉ ይለወጥና ለእድገት በር ሊከፍትልን ይችል ነበረ ለማለት ብቻ ነው። ደግሞም ኳስ ራሱ ፖለቲካም ስፖርትም ስለሆነ እንጂ… ኳሱን ትቼ ፖለቲካ ውስጥ ዘልዬ መግባቴም እንዳይመስልህ…ብገባም ፖለቲካ የማይገባበት ጉዳይ ስለሌለ ምንም አይደለም።….ነገርን ነገር ያነሳዋልና ፖለቲካና አፍሪካ ከተነሱ አይቀር ይህንን ልጥቀስ። አንድ የማንክደውን ጉዳይ ግን አቶ መለስ ዜናዊ የአፍሪካ ቁጥር አንድ Spokesman መሆናቸውን ይመስለኛል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ በበለጠ ለአፍሪካችን ይጠቅሙ እንደነበር ማህደርና ነገር በመምዘዝ እንዲሁ መከራከሪያ ፅሁፍ አዘጋጅቼ ተቀባይነት ያገኘ ንግግር አድርጌ ነበር። ይህንን የምለውም የእኔን ስራ ለመግለጥ ፈልጌ ሳይሆን ፖለቲካውም እንደ ኳስ እየተዟዟረ እየገባብኝ ተቸግሬ ስለሆነ አንባቢዎቼን ይቅርታ እጠይቃለሁ… እናም ወንድሜ የአፍሪካ ዋንጫን ማሸነፍ መቻል በኢትዮጵያ ላይ ትልቅ አንድምታ ነበረው ዋልያዎቹ እስከመጨረሻው ለመጫወት ቢችሉ ኖሮ  ለማለት ፈልጌ  ነው ብዙ ቦታ የረገጥኩት። ከዚህ ከአፍሪካ ዋንጫ ጋር ስለሚያያዝ ለአባይ ግድብ መስሪያ የፋይናንስ ምንጭ ከየት ይገኛል የሚል ጥያቄ ሲነሳ በጣም የሚገርመኝን ልናገር…በአሜሪካ ሀገር ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቢሮ አመታዊ በጀት የማይበልጠውና… ለኢትዮጵያ ግን የሰማይ ያህል የራቃት የአባይ መገደቢያ 5 በሊዮን ዶላር የአፍሪካ ዋንጫ ድልን ብናገኝ ኖሮ ገንዘቡን በስጦታም ይሁን በብድር ለማግኘት ማንም አለም አቀፋዊ ድርጅት አያሾፍብንም ነበር።…እንዴት ቢባል የኢትዮጵያ ፖቴንሻል በአለም የታወቀ ሲሆን…በተጨማሪም እያደገች መሆንዋን በአፍሪካም በአለምም በስፖርቱም በፖለቲካውም በኢኮኖሚውም መድረክ በሚገባ ለማረጋገጥዋ ከቻለች… የተረጋጋች ሀገር መሆንዋን… መሪዎቻችን መብሰላቸውን… ህዝብዋ ጠንካራና አንድነት ያለው መሆኑን ወዘተ ስለሚያሳይ…ይህ ደግሞ በአለም ደረጃም ሆነ በአፍሪካም ሁነኛ ቦታ/ትልቅ ሚና ትኩረትም ስለሚያሰጣት…አባይን መገደብ ቀርቶ ሌላም ታላቅ ፕሮጀክት ለመስራት እንኳን የሚያግዳት ነገር ሊኖር አይችልምና ነው።

ባጭር አባባል ግብፅ በአለም ፊት ካላት ተቀባይነትና ተደማጭነት ባላነሰ ደረጃ ኢትዮጵያም ሊኖራት ስለሚችል ለግድብ መስሪያ ገንዘብ ብድር ማጣት ቀርቶ አለም አቀፍ ድጋፍም እናገኝ ነበረ…ማንም እንደማይረባ ሀገር ቆጥሮ በጥርጣሬ ሊያየን አይችልም ነበር ለማለት ነው። በሌላ በኩልም በደቡብ አፍሪካ እስከ ዋንጫ ፍፃሜ ድረስ ብንቆይ ኖሮ የእግር ኳስ ተጫዋቾቻችን በአለም የእግር ኳስ ገበያ የመሸጥ እድል ቦግ ብሎ  አይጠፋም ነበር። …በእድልም ተባለ በችሎታ እስከ ዋንጫው ፍፃሜ ለመጫወት ቢችሉ ኖሮ… ወይም ዋንጫ ማንሳት ቢሳካላቸው ኖሮ ስንት ተጫዋቾቻችን በሚሊዮን ዶላር ይሸጡ እንደነበር መገምት አያዳግትም…በነሱም ዘውግ ባንድ ጊዜ በመጣው መልካም እድልና ታዋቂነት ቀጣዩ ትውልድም ኳስ ለመጫወት በመሸጥ ብቻ እራሱንም ሀገሩንም ያለማ እንደነበረ ለመገመት አያስቸግርም። ከዚህም በተጨማሪም አንተም እንደገለፅከው እስከ ዋንጫው ጨዋታ ድረስ ብንቆይ ኖሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ መልክ (image) ይለወጥም ነበር። ይኸውምበአለም ሁሉ በቴሌቪዥን መስኮት በተሰራው “ ኑና እዩን ” በሚለው የውብ ኢትዮጵያውያን የማስታወቂያ ስራ መሰረት… ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ሀገሪትዋ በቱሪስቶች መጨናነቅዋ አይቀርም ነበርና ነው። በዚህች በሶስት ጨዋታ ብቻ በታዩት ደጋፊዎች የተነሳ ኢትዮጵያውያን እንዲህ ውብ ናችሁ እንዴ!….መስህብ ያላቸው ሰዎች አላችሁ…ርሀብተኛ….ስደተኛ ብቻ አይደላችሁም…. ያሉኝ ብዙ አሜሪካውያን ናቸው። እስከ ዋንጫው ብንደርስማ ኖሮ የአለም ዕይታ በጣም እንደሚለወጥ ለመገመት አያቅትም። ስለሆነም በርካታ ገንዘባቸውን ማድረሻ ያጡ ቱጃሮች ወደ ኢትዮጵያ በመጉረፍ… ከፍተኛ የቱሪስት ገቢ በማስግኘት… በጭስ አልባ እንዱስትሪ ሀገሪትዋ ለማደግና ለመመንደግ ትችል የነበረበት እድል በኳስ ሜዳው ድል እጦት የተነሳ ጨፍግጎአል። ሌላም ሌላም ለማለት ይቻል ነበር.. ወሬ ቢበዛ….እንዲሉ በዚህ ላብቃ። በመጨረሻም ስፖርትና ቦተሊካ እንደማይጣረሱ ልብ አላችሁልኝ? መልካም እድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን። Let God help the Country.

2 thoughts on “ኢትዮጵያ ያመለጣት ታላቅ እድል

  1. Yosef it is so interesting. you observed well. the 2013 African nations cup was an opportunity, we never get it back. However, the 2014 African Cup of nations is tomorrow; I think we may do a miracle if the Waliyas can’t be shaken.

    <>

    Yeah I quite agree with you; we lost a lot of opportunities because of lack of experience and good sport manner. Nevertheless, the 2013 African Cup of Nations can be a good lesson for the Waliyas, particularly for the goalkeepers. I think they can evaluate themselves and get ready for the next cup. However, as a first opportunity after three decades, the Waliyas should be appreciated and encouraged.

    Thank you and God bless you Yosef.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s